# am/Amharic.xml.gz
# he/Hebrew.xml.gz


(src)="b.GEN.1.1.1"> በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ ።
(trg)="b.GEN.1.1.1"> בראשית ברא אלהים את השמים ואת הארץ ׃

(src)="b.GEN.1.2.1"> ምድርም ባዶ ነበረች ፥ አንዳችም አልነበረባትም ፤ ጨለማም በጥልቁ ላይ ነበረ ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በውኃ ላይ ሰፍፎ ነበር ።
(trg)="b.GEN.1.2.1"> והארץ היתה תהו ובהו וחשך על פני תהום ורוח אלהים מרחפת על פני המים ׃

(src)="b.GEN.1.3.1"> እግዚአብሔርም ። ብርሃን ይሁን ኣለ ፤ ብርሃንም ሆነ ።
(trg)="b.GEN.1.3.1"> ויאמר אלהים יהי אור ויהי אור ׃

(src)="b.GEN.1.4.1"> እግዚአብሔርም ብርሃኑ መልካም እንደ ሆነ አየ ፤ እግዚብሔርም ብርሃንንና ጨለማን ለየ ።
(trg)="b.GEN.1.4.1"> וירא אלהים את האור כי טוב ויבדל אלהים בין האור ובין החשך ׃

(src)="b.GEN.1.5.1"> እግዚአብሔርም ብርሃኑን ቀን ብሎ ጠራው ፥ ጨለማውንም ሌሊት አለው ። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ ፥ አንድ ቀን ።
(trg)="b.GEN.1.5.1"> ויקרא אלהים לאור יום ולחשך קרא לילה ויהי ערב ויהי בקר יום אחד ׃

(src)="b.GEN.1.6.1"> እግዚአብሔርም ። በውኆች መካከል ጠፈር ይሁን ፥ በውኃና በውኃ መካከልም ይክፈል አለ ።
(trg)="b.GEN.1.6.1"> ויאמר אלהים יהי רקיע בתוך המים ויהי מבדיל בין מים למים ׃

(src)="b.GEN.1.7.1"> እግዚአብሔርም ጠፈርን አደረገ ፥ ከጠፈር በታችና ከጠፈር በላይ ያሉትንም ውኆች ለየ ፤ እንዲሁም ሆነ ።
(trg)="b.GEN.1.7.1"> ויעש אלהים את הרקיע ויבדל בין המים אשר מתחת לרקיע ובין המים אשר מעל לרקיע ויהי כן ׃

(src)="b.GEN.1.8.1"> እግዚአብሔር ጠፈርን ሰማይ ብሎ ጠራው ። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ ፥ ሁለተኛ ቀን ።
(trg)="b.GEN.1.8.1"> ויקרא אלהים לרקיע שמים ויהי ערב ויהי בקר יום שני ׃

(src)="b.GEN.1.9.1"> እግዚአብሔርም ። ከሰማይ በታች ያለው ውኃ በአንድ ስፍራ ይሰብሰብ ፥ የብሱም ይገለጥ አለ እንዲሁም ሆነ ።
(trg)="b.GEN.1.9.1"> ויאמר אלהים יקוו המים מתחת השמים אל מקום אחד ותראה היבשה ויהי כן ׃

(src)="b.GEN.1.10.1"> እግዚአብሔርም የብሱን ምድር ብሎ ጠራው ፤ የውኃ መከማቻውንም ባሕር አለው ፤ እግዚእብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ ።
(trg)="b.GEN.1.10.1"> ויקרא אלהים ליבשה ארץ ולמקוה המים קרא ימים וירא אלהים כי טוב ׃

(src)="b.GEN.1.11.1"> እግዚአብሔርም ። ምድር ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን በምድርም ላይ እንደ ወገኑ ዘሩ ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን ታብቅል አለ ፤ እንዲሁም ሆነ ።
(trg)="b.GEN.1.11.1"> ויאמר אלהים תדשא הארץ דשא עשב מזריע זרע עץ פרי עשה פרי למינו אשר זרעו בו על הארץ ויהי כן ׃

(src)="b.GEN.1.12.1"> ምድርም ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን እንደ ወገኑ ዘሩም ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን እንደ ወገኑ አበቀለች ። እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ ።
(trg)="b.GEN.1.12.1"> ותוצא הארץ דשא עשב מזריע זרע למינהו ועץ עשה פרי אשר זרעו בו למינהו וירא אלהים כי טוב ׃

(src)="b.GEN.1.13.1"> ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ ፥ ሦስተኛ ቀን ።
(trg)="b.GEN.1.13.1"> ויהי ערב ויהי בקר יום שלישי ׃

(src)="b.GEN.1.14.1"> እግዚአብሔርም አለ ። ቀንና ሌሊትን ይለዩ ዘንድ ብርሃናት በሰማይ ጠፈር ይሁኑ ፤ ለምልክቶች ለዘመኖች ለዕለታት ለዓመታትም ይሁኑ ፤
(trg)="b.GEN.1.14.1"> ויאמר אלהים יהי מארת ברקיע השמים להבדיל בין היום ובין הלילה והיו לאתת ולמועדים ולימים ושנים ׃

(src)="b.GEN.1.15.1"> በምድር ላይ ያበሩ ዘንድ በሰማይ ጠፈር ብርሃናት ይሁኑ ፤ እንዲሁም ሆነ ።
(trg)="b.GEN.1.15.1"> והיו למאורת ברקיע השמים להאיר על הארץ ויהי כן ׃

(src)="b.GEN.1.16.1"> እግዚአብሔርም ሁለት ታላላቆች ብርሃናትን አደረገ ፤ ትልቁ ብርሃን በቀን እንዲሠለጥን ፥ ትንሹም ብርሃን በሌሊት እንዲሰለጥን ፤ ከዋክብትንም ደግሞ አደረገ ።
(trg)="b.GEN.1.16.1"> ויעש אלהים את שני המארת הגדלים את המאור הגדל לממשלת היום ואת המאור הקטן לממשלת הלילה ואת הכוכבים ׃

(src)="b.GEN.1.17.1"> እግዚአብሔርም በምድር ላይ ያበሩ ዘንድ በሰማይ ጠፈር አኖራቸው ፤
(trg)="b.GEN.1.17.1"> ויתן אתם אלהים ברקיע השמים להאיר על הארץ ׃

(src)="b.GEN.1.18.1"> በቀንም በሌሊትም እንዲሠለጥኑ ፥ ብርሃንንና ጨለማንም እንዲለዩ ፤ እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ ።
(trg)="b.GEN.1.18.1"> ולמשל ביום ובלילה ולהבדיל בין האור ובין החשך וירא אלהים כי טוב ׃

(src)="b.GEN.1.19.1"> ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ ፥ አራተኛ ቀን ።
(trg)="b.GEN.1.19.1"> ויהי ערב ויהי בקר יום רביעי ׃

(src)="b.GEN.1.20.1"> እግዚአብሔርም አለ ። ውኃ ሕያው ነፍስ ያላቸውን ተንቀሳቃሾች ታስገኝ ፥ ወፎችም ከምድር በላይ ከሰማይ ጠፈር በታች ይብረሩ ።
(trg)="b.GEN.1.20.1"> ויאמר אלהים ישרצו המים שרץ נפש חיה ועוף יעופף על הארץ על פני רקיע השמים ׃

(src)="b.GEN.1.21.1"> እግዚአብሔርም ታላላቆች አንበሪዎችን ፥ ውኃይቱ እንደ ወገኑ ያስገኘቻቸውንም ተንቀሳቃሾቹን ሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ ፥ እንደ ወገኑ የሚበሩትንም ወፎች ሁሉ ፈጠረ ፤ እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ ።
(trg)="b.GEN.1.21.1"> ויברא אלהים את התנינם הגדלים ואת כל נפש החיה הרמשת אשר שרצו המים למינהם ואת כל עוף כנף למינהו וירא אלהים כי טוב ׃

(src)="b.GEN.1.22.1"> እግዚአብሔርም እንዲህ ብሎ ባረካቸው ። ብዙ ተባዙም የባሕርንም ውኃ ሙሉአት ፤ ወፎችም በምድር ላይ ይብዙ ።
(trg)="b.GEN.1.22.1"> ויברך אתם אלהים לאמר פרו ורבו ומלאו את המים בימים והעוף ירב בארץ ׃

(src)="b.GEN.1.23.1"> ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ ፥ አምስተኛ ቀን ።
(trg)="b.GEN.1.23.1"> ויהי ערב ויהי בקר יום חמישי ׃

(src)="b.GEN.1.24.1"> እግዚአብሔርም አለ ። ምድር ሕያዋን ፍጥረታትን እንደ ወገኑ ፥ እንስሳትንና ተንቀሳቃሾችን የምድር አራዊትንም እንደ ወገኑ ፥ ታውጣ ፤ እንዲሁም ሆነ ።
(trg)="b.GEN.1.24.1"> ויאמר אלהים תוצא הארץ נפש חיה למינה בהמה ורמש וחיתו ארץ למינה ויהי כן ׃

(src)="b.GEN.1.25.1"> እግዚአብሔር የምድር አራዊትን እንደ ወገኑ አደረገ ፥ እንስሳውንም እንደ ወገኑ ፥ የመሬት ተንቀሳቃሾችንም እንደ ወገኑ አደረገ ፤ እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ ።
(trg)="b.GEN.1.25.1"> ויעש אלהים את חית הארץ למינה ואת הבהמה למינה ואת כל רמש האדמה למינהו וירא אלהים כי טוב ׃

(src)="b.GEN.1.26.1"> እግዚአብሔርም አለ ። ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር ፤ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን ፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ ።
(trg)="b.GEN.1.26.1"> ויאמר אלהים נעשה אדם בצלמנו כדמותנו וירדו בדגת הים ובעוף השמים ובבהמה ובכל הארץ ובכל הרמש הרמש על הארץ ׃

(src)="b.GEN.1.27.1"> እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው ፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው ።
(trg)="b.GEN.1.27.1"> ויברא אלהים את האדם בצלמו בצלם אלהים ברא אתו זכר ונקבה ברא אתם ׃

(src)="b.GEN.1.28.1"> እግዚአብሔርም ባረካቸው ፥ እንዲህም አላቸው ። ብዙ ፥ ተባዙ ፥ ምድርንም ሙሉአት ፥ ግዙአትም ፤ የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዙአቸው ።
(trg)="b.GEN.1.28.1"> ויברך אתם אלהים ויאמר להם אלהים פרו ורבו ומלאו את הארץ וכבשה ורדו בדגת הים ובעוף השמים ובכל חיה הרמשת על הארץ ׃

(src)="b.GEN.1.29.1"> እግዚአብሔርም አለ ። እነሆ መብል ይሆናችሁ ዘንድ በምድር ፊት ሁሉ ላይ ዘሩ በእርሱ ያለውን ሐመልማል ሁሉ ፥ የዛፍን ፍሬ የሚያፈራውንና ዘር ያለውንም ዛፍ ሁሉ ሰጠኋችሁ ፤
(trg)="b.GEN.1.29.1"> ויאמר אלהים הנה נתתי לכם את כל עשב זרע זרע אשר על פני כל הארץ ואת כל העץ אשר בו פרי עץ זרע זרע לכם יהיה לאכלה ׃

(src)="b.GEN.1.30.1"> ለምድርም አራዊት ሁሉ ፥ ለሰማይም ወፎች ሁሉ ፥ ሕያው ነፍስ ላላቸው ለምድር ተንቀሳቃሾችም ሁሉ የሚበቅለው ሐመልማል ሁሉ መብል ይሁንላቸው ፤ እንዲሁም ሆነ ።
(trg)="b.GEN.1.30.1"> ולכל חית הארץ ולכל עוף השמים ולכל רומש על הארץ אשר בו נפש חיה את כל ירק עשב לאכלה ויהי כן ׃

(src)="b.GEN.1.31.1"> እግዚአብሔርም ያደረገውን ሁሉ አየ ፥ እነሆም እጅግ መልካም ነበረ ። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ ፥ ስድስተኛ ቀን ።
(trg)="b.GEN.1.31.1"> וירא אלהים את כל אשר עשה והנה טוב מאד ויהי ערב ויהי בקר יום הששי ׃

(src)="b.GEN.2.1.1"> ሰማይና ምድር ሠራዊታቸውም ሁሉ ተፈጸሙ ።
(trg)="b.GEN.2.1.1"> ויכלו השמים והארץ וכל צבאם ׃

(src)="b.GEN.2.2.1"> እግዚአብሔርም የሠራውን ሥራ በሰባተኛው ቀን ፈጸመ ፤ በሰባተኛውም ቀን ከሠራው ሥራ ሁሉ ዐረፈ ።
(trg)="b.GEN.2.2.1"> ויכל אלהים ביום השביעי מלאכתו אשר עשה וישבת ביום השביעי מכל מלאכתו אשר עשה ׃

(src)="b.GEN.2.3.1"> እግዚአብሔርም ሰባተኛውን ቀን ባረከው ቀደሰውም ፤ እግዚአብሔር ሊያደርገው ከፈጠረው ሥራ ሁሉ በእርሱ ዐርፎአልና ።
(trg)="b.GEN.2.3.1"> ויברך אלהים את יום השביעי ויקדש אתו כי בו שבת מכל מלאכתו אשר ברא אלהים לעשות ׃

(src)="b.GEN.2.4.1"> እግዚአብሔር አምላክ ሰማይንና ምድርን ባደረገ አምላክ ሰማይንና ምድርን ቀን ፥ በተፈጠሩ ጊዜ የሰማይና የምድር ልደት ይህ ነው ።
(trg)="b.GEN.2.4.1"> אלה תולדות השמים והארץ בהבראם ביום עשות יהוה אלהים ארץ ושמים ׃

(src)="b.GEN.2.5.1"> የሜዳ ቁጥቋጦ ሁሉ በምድር ላይ ገና አልነበረም ፤ የሜዳውም ቡቃያ ሁሉ ገና አልበቀለም ነበር ፤ እግዚአብሔር አምላክ ምድር ላይ አላዘነበም ነበርና ፥ ምድርንም የሚሠራባት ሰው አልነበረም ፤
(trg)="b.GEN.2.5.1"> וכל שיח השדה טרם יהיה בארץ וכל עשב השדה טרם יצמח כי לא המטיר יהוה אלהים על הארץ ואדם אין לעבד את האדמה ׃

(src)="b.GEN.2.6.1"> ነገር ግን ጉም ከምድር ትወጣ ነበር ፥ የምድርንም ፊት ሁሉ ታጠጣ ነበር ።
(trg)="b.GEN.2.6.1"> ואד יעלה מן הארץ והשקה את כל פני האדמה ׃

(src)="b.GEN.2.7.1"> እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ከምድር አፈር አበጀው ፤ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት ፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ ።
(trg)="b.GEN.2.7.1"> וייצר יהוה אלהים את האדם עפר מן האדמה ויפח באפיו נשמת חיים ויהי האדם לנפש חיה ׃

(src)="b.GEN.2.8.1"> እግዚአብሔር አምላክም በምሥራቅ በዔድን ገነትን ተከለ የፈጠረውንም ሰው ከዚያው አኖረው ።
(trg)="b.GEN.2.8.1"> ויטע יהוה אלהים גן בעדן מקדם וישם שם את האדם אשר יצר ׃

(src)="b.GEN.2.9.1"> እግዚአብሔር አምላክም ለማየት ደስ የሚያሰኘውን ፥ ለመብላትም መልካም የሆነውን ዛፍ ሁሉ ከምድር አበቀለ ፤ በገነትም መካከል የሕይወትን ዛፍ ፥ መልካምንና ክፉን የሚያስታውቀውንም ዛፍ አበቀለ ።
(trg)="b.GEN.2.9.1"> ויצמח יהוה אלהים מן האדמה כל עץ נחמד למראה וטוב למאכל ועץ החיים בתוך הגן ועץ הדעת טוב ורע ׃

(src)="b.GEN.2.10.1"> ወንዝም ገነትን ያጠጣ ዘንድ ከዔድን ይወጣ ነበር ፤ ከዚያም ለአራት ክፍል ይከፈል ነበር ።
(trg)="b.GEN.2.10.1"> ונהר יצא מעדן להשקות את הגן ומשם יפרד והיה לארבעה ראשים ׃

(src)="b.GEN.2.11.1"> የአንደኛው ወንዝ ስም ፊሶን ነው ፤ እርሱም ወርቅ የሚገኝበትን የኤውላጥ ምድርን ይከብባል ፤ የዚያም ምድር ወርቅ ጥሩ ነው ፤
(trg)="b.GEN.2.11.1"> שם האחד פישון הוא הסבב את כל ארץ החוילה אשר שם הזהב ׃

(src)="b.GEN.2.12.1"> ከዚያም ሉልና የከበረ ድንጋይ ይገኛል ።
(trg)="b.GEN.2.12.1"> וזהב הארץ ההוא טוב שם הבדלח ואבן השהם ׃

(src)="b.GEN.2.13.1"> የሁለተኛውም ወንዝ ስም ግዮን ነው ፤ እርሱም የኢትዮጵያን ምድር ሁሉ ይከብባል ።
(trg)="b.GEN.2.13.1"> ושם הנהר השני גיחון הוא הסובב את כל ארץ כוש ׃

(src)="b.GEN.2.14.1"> የሦስተኛውም ወንዝ ስም ጤግሮስ ነው ፤ እርሱም በአሦር ምሥራቅ የሚሄድ ነው ።
(trg)="b.GEN.2.14.1"> ושם הנהר השלישי חדקל הוא ההלך קדמת אשור והנהר הרביעי הוא פרת ׃

(src)="b.GEN.2.15.1"> አራተኛውም ወንዝ ኤፍራጥስ ነው ። እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ወስዶ ያበጃትም ይጠብቃትም ዘንድ በዔድን ገነት አኖረው ።
(trg)="b.GEN.2.15.1"> ויקח יהוה אלהים את האדם וינחהו בגן עדן לעבדה ולשמרה ׃

(src)="b.GEN.2.16.1"> እግዚአብሔር አምላክም ሰውን እንዲህ ብሎ አዘዘው ። ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ ፤
(trg)="b.GEN.2.16.1"> ויצו יהוה אלהים על האדם לאמר מכל עץ הגן אכל תאכל ׃

(src)="b.GEN.2.17.1"> ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና ።
(trg)="b.GEN.2.17.1"> ומעץ הדעת טוב ורע לא תאכל ממנו כי ביום אכלך ממנו מות תמות ׃

(src)="b.GEN.2.18.1"> እግዚአብሔር አምላክም አለ ። ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም ፤ የሚመቸውን ረዳት እንፍጠርለት ።
(trg)="b.GEN.2.18.1"> ויאמר יהוה אלהים לא טוב היות האדם לבדו אעשה לו עזר כנגדו ׃

(src)="b.GEN.2.19.1"> እግዚአብሔር አምላክም የምድር አራዊትንና የሰማይ ወፎችን ሁሉ ከመሬት አደረገ ፤ በምን ስም እንደሚጠራቸውም ያይ ዘንድ ወደ አዳም አመጣቸው ፤ አዳምም ሕያው ነፍስ ላለው ሁሉ በስሙ እንደ ጠራው ስሙ ያው ሆነ ።
(trg)="b.GEN.2.19.1"> ויצר יהוה אלהים מן האדמה כל חית השדה ואת כל עוף השמים ויבא אל האדם לראות מה יקרא לו וכל אשר יקרא לו האדם נפש חיה הוא שמו ׃

(src)="b.GEN.2.20.1"> አዳምም ለእንስሳት ሁሉ ፥ ለሰማይ ወፎችም ሁሉ ፥ ለምድር አራዊትም ሁሉ ስም አወጣላቸው ፤ ነገር ግን ለአዳም እንደ እርሱ ያለ ረዳት አልተገኘለትም ነበር ።
(trg)="b.GEN.2.20.1"> ויקרא האדם שמות לכל הבהמה ולעוף השמים ולכל חית השדה ולאדם לא מצא עזר כנגדו ׃

(src)="b.GEN.2.21.1"> እግዚአብሔር አምላክም በአዳም ከባድ እንቅልፍን ጣለበት ፥ አንቀላፋም ፤ ከጎኑም አንዲት አጥንትን ወስዶ ስፍራውን በሥጋ ዘጋው ።
(trg)="b.GEN.2.21.1"> ויפל יהוה אלהים תרדמה על האדם ויישן ויקח אחת מצלעתיו ויסגר בשר תחתנה ׃

(src)="b.GEN.2.22.1"> እግዚአብሔር አምላክም ከአዳም የወሰዳትን አጥንት ሴት አድርጎ ሠራት ፤ ወደ አዳምም አመጣት ።
(trg)="b.GEN.2.22.1"> ויבן יהוה אלהים את הצלע אשר לקח מן האדם לאשה ויבאה אל האדם ׃

(src)="b.GEN.2.23.1"> አዳምም አለ ። ይህች አጥንት ከአጥንቴ ናት ፥ ሥጋም ከሥጋዬ ናት ፤ እርስዋ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል ።
(trg)="b.GEN.2.23.1"> ויאמר האדם זאת הפעם עצם מעצמי ובשר מבשרי לזאת יקרא אשה כי מאיש לקחה זאת ׃

(src)="b.GEN.2.24.1"> ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል ፥ በሚስቱም ይጣበቃል ፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ ።
(trg)="b.GEN.2.24.1"> על כן יעזב איש את אביו ואת אמו ודבק באשתו והיו לבשר אחד ׃

(src)="b.GEN.2.25.1"> አዳምና ሚስቱ ሁለቱም ዕራቁታቸውን ነበሩ ፥ አይተፋፈሩም ነበር ።
(trg)="b.GEN.2.25.1"> ויהיו שניהם ערומים האדם ואשתו ולא יתבששו ׃

(src)="b.GEN.3.1.1"> እባብም እግዚአብሔር አምላክ ከፈጠረው ከምድር አውሬ ሁሉ ይልቅ ተንኰለኛ ነበረ ። ሴቲቱንም ። በውኑ እግዚአብሔር ከገነት ዛፍ ሁሉ እንዳትበሉ አዝዞአልን ? አላት ።
(trg)="b.GEN.3.1.1"> והנחש היה ערום מכל חית השדה אשר עשה יהוה אלהים ויאמר אל האשה אף כי אמר אלהים לא תאכלו מכל עץ הגן ׃

(src)="b.GEN.3.2.1"> ሴቲቱም ለእባቡ አለችው ። በገነት ካለው ከዛፍ ፍሬ እንበላለን ፤
(trg)="b.GEN.3.2.1"> ותאמר האשה אל הנחש מפרי עץ הגן נאכל ׃

(src)="b.GEN.3.3.1"> ነገር ግን በገነት መካከል ካለው ከዛፉ ፍሬ ፥ እግዚአብሔር አለ ። እንዳትሞቱ ከእርሱ አትብሉ አትንኩትም ።
(trg)="b.GEN.3.3.1"> ומפרי העץ אשר בתוך הגן אמר אלהים לא תאכלו ממנו ולא תגעו בו פן תמתון ׃

(src)="b.GEN.3.4.1"> እባብም ለሴቲቱ አላት ። ሞትን አትሞቱም ፤
(trg)="b.GEN.3.4.1"> ויאמר הנחש אל האשה לא מות תמתון ׃

(src)="b.GEN.3.5.1"> ከእርስዋ በበላችሁ ቀን ዓይኖቻችሁ እንዲከፈቱ እንደ እግዚአብሔርም መልካምንና ክፉን የምታውቁ እንድትሆኑ እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ነው እንጂ ።
(trg)="b.GEN.3.5.1"> כי ידע אלהים כי ביום אכלכם ממנו ונפקחו עיניכם והייתם כאלהים ידעי טוב ורע ׃

(src)="b.GEN.3.6.1"> ሴቲቱም ዛፉ ለመብላት ያማረ እንደ ሆነ ፥ ለዓይንም እንደሚያስጎመጅ ፥ ለጥበብም መልካም እንደ ሆነ አየች ፤ ከፍሬውም ወሰደችና በላች ፤ ለባልዋም ደግሞ ሰጠችው እርሱም ከእርስዋ ጋር በላ ።
(trg)="b.GEN.3.6.1"> ותרא האשה כי טוב העץ למאכל וכי תאוה הוא לעינים ונחמד העץ להשכיל ותקח מפריו ותאכל ותתן גם לאישה עמה ויאכל ׃

(src)="b.GEN.3.7.1"> የሁለቱም ዓይኖች ተከፈቱ ፥ እነርሱም ዕራቁታቸውን እንደ ሆኑ አወቁ ፤ የበለስንም ቅጠሎች ሰፍተው ለእነርሱ ለራሳቸው ግልድም አደረጉ ።
(trg)="b.GEN.3.7.1"> ותפקחנה עיני שניהם וידעו כי עירמם הם ויתפרו עלה תאנה ויעשו להם חגרת ׃

(src)="b.GEN.3.8.1"> እነርሱም ቀኑ በመሸ ጊዜ የእግዚአብሔርን የአምላክን ድምፅ ከገነት ውስጥ ሲመላለስ ሰሙ ፤ አዳምና ሚስቱም ከእግዚአብሔር ከአምላክ ፊት በገነት ዛፎች መካከል ተሸሸጉ ።
(trg)="b.GEN.3.8.1"> וישמעו את קול יהוה אלהים מתהלך בגן לרוח היום ויתחבא האדם ואשתו מפני יהוה אלהים בתוך עץ הגן ׃

(src)="b.GEN.3.9.1"> እግዚአብሔር አምላክም አዳምን ጠርቶ ። ወዴት ነህ ? አለው ።
(trg)="b.GEN.3.9.1"> ויקרא יהוה אלהים אל האדם ויאמר לו איכה ׃

(src)="b.GEN.3.10.1"> እርሱም አለ ። በገነት ድምፅህን ሰማሁ ፤ ዕራቁቴንም ስለ ሆንሁ ፈራሁ ፥ ተሸሸግሁም ።
(trg)="b.GEN.3.10.1"> ויאמר את קלך שמעתי בגן ואירא כי עירם אנכי ואחבא ׃

(src)="b.GEN.3.11.1"> እግዚአብሔርም አለው ። ዕራቁትህን እንደ ሆንህ ማን ነገረህ ? ከእርሱ እንዳትበላ ካዘዝሁህ ዛፍ በውኑ በላህን ?
(trg)="b.GEN.3.11.1"> ויאמר מי הגיד לך כי עירם אתה המן העץ אשר צויתיך לבלתי אכל ממנו אכלת ׃

(src)="b.GEN.3.12.1"> አዳምም አለ ። ከእኔ ጋር እንድትሆን የሰጠኸኝ ሴት እርስዋ ከዛፉ ሰጠችኝና በላሁ ።
(trg)="b.GEN.3.12.1"> ויאמר האדם האשה אשר נתתה עמדי הוא נתנה לי מן העץ ואכל ׃

(src)="b.GEN.3.13.1"> እግዚአብሔር አምላክም ሴቲቱን ። ይህ ያደረግሽው ምንድር ነው ? አላት ። ሴቲቱም አለች ። እባብ አሳተኝና በላሁ ።
(trg)="b.GEN.3.13.1"> ויאמר יהוה אלהים לאשה מה זאת עשית ותאמר האשה הנחש השיאני ואכל ׃

(src)="b.GEN.3.14.1"> እግዚአብሔር አምላክም እባቡን አለው ። ይህን ስላደረግህ ከእንስሳት ከምድር አራዊትም ሁሉ ተለይተህ አንተ የተረገምህ ትሆናለህ ፤ በሆድህም ትሄዳለህ ፥ አፈርንም በሕይወትህ ዘመን ሁሉ ትበላለህ ።
(trg)="b.GEN.3.14.1"> ויאמר יהוה אלהים אל הנחש כי עשית זאת ארור אתה מכל הבהמה ומכל חית השדה על גחנך תלך ועפר תאכל כל ימי חייך ׃

(src)="b.GEN.3.15.1"> በአንተና በሴቲቱ መካከል ፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል ፥ አንተም ሰኰናውን ትቀጠቅጣለህ ።
(trg)="b.GEN.3.15.1"> ואיבה אשית בינך ובין האשה ובין זרעך ובין זרעה הוא ישופך ראש ואתה תשופנו עקב ׃

(src)="b.GEN.3.16.1"> ለሴቲቱም አለ ። በፀነስሽ ጊዜ ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ ፤ በጭንቅ ትወልጃለሽ ፤ ፈቃድሽም ወደ ባልሽ ይሆናል ፥ እርሱም ገዥሽ ይሆናል ።
(trg)="b.GEN.3.16.1"> אל האשה אמר הרבה ארבה עצבונך והרנך בעצב תלדי בנים ואל אישך תשוקתך והוא ימשל בך ׃

(src)="b.GEN.3.17.1"> አዳምንም አለው ። የሚስትህን ቃል ሰምተሃልና ፥ ከእርሱ እንዳትበላ ካዘዝሁህ ዛፍም በልተሃልና ምድር ከአንተ የተነሣ የተረገመች ትሁን ፤ በሕይወት ዘመንህም ሁሉ በድካም ከእርስዋ ትበላለህ ፤
(trg)="b.GEN.3.17.1"> ולאדם אמר כי שמעת לקול אשתך ותאכל מן העץ אשר צויתיך לאמר לא תאכל ממנו ארורה האדמה בעבורך בעצבון תאכלנה כל ימי חייך ׃

(src)="b.GEN.3.18.1"> እሾህንና አሜከላን ታበቅልብሃለች ፤ የምድርንም ቡቃያ ትበላለህ ።
(trg)="b.GEN.3.18.1"> וקוץ ודרדר תצמיח לך ואכלת את עשב השדה ׃

(src)="b.GEN.3.19.1"> ወደ ወጣህበት መሬት እስክትመለስ ድረስ በፊትህ ወዝ እንጀራን ትበላለህ ፤ አፈር ነህና ፥ ወደ አፈርም ትመለሳለህና ።
(trg)="b.GEN.3.19.1"> בזעת אפיך תאכל לחם עד שובך אל האדמה כי ממנה לקחת כי עפר אתה ואל עפר תשוב ׃

(src)="b.GEN.3.20.1"> አዳምም ለሚስቱ ሔዋን ብሎ ስም አወጣ ፥ የሕያዋን ሁሉ እናት ናትና ።
(trg)="b.GEN.3.20.1"> ויקרא האדם שם אשתו חוה כי הוא היתה אם כל חי ׃

(src)="b.GEN.3.21.1"> እግዚአብሔር አምላክም ለአዳምና ለሚስቱ የቁርበትን ልብስ አደረገላቸው ፥ አለበሳቸውም ።
(trg)="b.GEN.3.21.1"> ויעש יהוה אלהים לאדם ולאשתו כתנות עור וילבשם ׃

(src)="b.GEN.3.22.1"> እግዚአብሔር አምላክም አለ ። እነሆ አዳም መልካምንና ክፉን ለማወቅ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ ፤ አሁንም እጁን እንዳይዘረጋ ፥ ደግሞም ከሕይወት ዛፍ ወስዶ እንዳይበላ ፥ ለዘላለምም ሕያው ሆኖ እንዳይኖር ፤
(trg)="b.GEN.3.22.1"> ויאמר יהוה אלהים הן האדם היה כאחד ממנו לדעת טוב ורע ועתה פן ישלח ידו ולקח גם מעץ החיים ואכל וחי לעלם ׃

(src)="b.GEN.3.23.1"> ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክ ከዔድን ገነት አስወጣው ፥ የተገኘባትን መሬት ያርስ ዘንድ ።
(trg)="b.GEN.3.23.1"> וישלחהו יהוה אלהים מגן עדן לעבד את האדמה אשר לקח משם ׃

(src)="b.GEN.3.24.1"> አዳምንም አስወጣው ፥ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውንም መንገድ ለመጠበቅ ኪሩቤልንና የምትገለባበጥ የነበልባል ሰይፍን በዔድን ገነት ምሥራቅ አስቀመጠ ።
(trg)="b.GEN.3.24.1"> ויגרש את האדם וישכן מקדם לגן עדן את הכרבים ואת להט החרב המתהפכת לשמר את דרך עץ החיים ׃

(src)="b.GEN.4.1.1"> አዳምም ሚስቱን ሔዋንን አወቀ ፤ ፀነሰችም ፥ ቃየንንም ወለደች ። እርስዋም ። ወንድ ልጅ ከእግዚአብሔር አገኘሁ አለች ።
(trg)="b.GEN.4.1.1"> והאדם ידע את חוה אשתו ותהר ותלד את קין ותאמר קניתי איש את יהוה ׃

(src)="b.GEN.4.2.1"> ደግሞም ወንድሙን አቤልን ወለደች ። አቤልም በግ ጠባቂ ነበረ ፤ ቃየንም ምድርን የሚያርስ ነበረ ።
(trg)="b.GEN.4.2.1"> ותסף ללדת את אחיו את הבל ויהי הבל רעה צאן וקין היה עבד אדמה ׃

(src)="b.GEN.4.3.1"> ከብዙ ቀን በኋላም ቃየን ከምድር ፍሬ ለእግዚአብሔር መሥዋዕትን አቀረበ ፤
(trg)="b.GEN.4.3.1"> ויהי מקץ ימים ויבא קין מפרי האדמה מנחה ליהוה ׃

(src)="b.GEN.4.4.1"> አቤልም ደግሞ ከበጎቹ በኵራትና ከስቡ አቀረበ ። እግዚአብሔርም ወደ አቤልና ወደ መሥዋዕቱ ተመለከተ ፤
(trg)="b.GEN.4.4.1"> והבל הביא גם הוא מבכרות צאנו ומחלבהן וישע יהוה אל הבל ואל מנחתו ׃

(src)="b.GEN.4.5.1"> ወደ ቃየንና ወደ መሥዋዕቱ ግን አልተመለከተም ። ቃየንም እጅግ ተናደደ ፊቱም ጠቆረ ።
(trg)="b.GEN.4.5.1"> ואל קין ואל מנחתו לא שעה ויחר לקין מאד ויפלו פניו ׃

(src)="b.GEN.4.6.1"> እግዚአብሔርም ቃየንን አለው ። ለምን ተናደድህ ? ለምንስ ፊትህ ጠቆረ ?
(trg)="b.GEN.4.6.1"> ויאמר יהוה אל קין למה חרה לך ולמה נפלו פניך ׃

(src)="b.GEN.4.7.1"> መልካም ብታደርግ ፊትህ የሚበራ አይደለምን ? መልካም ባታደርግ ግን ኃጢአት በደጅ ታደባለች ፤ ፈቃድዋም ወደ አንተ ነው ፥ አንተ ግን በእርስዋ ንገሥባት ።
(trg)="b.GEN.4.7.1"> הלוא אם תיטיב שאת ואם לא תיטיב לפתח חטאת רבץ ואליך תשוקתו ואתה תמשל בו ׃

(src)="b.GEN.4.8.1"> ቃየንም ወንድሙን አቤልን ። ና ወደ ሜዳ እንሂድ አለው ። በሜዳም ሳሉ ቃየን በወንድሙ በአቤል ላይ ተነሣበት ፥ ገደለውም ።
(trg)="b.GEN.4.8.1"> ויאמר קין אל הבל אחיו ויהי בהיותם בשדה ויקם קין אל הבל אחיו ויהרגהו ׃

(src)="b.GEN.4.9.1"> እግዚአብሔርም ቃየንን አለው ። ወንድምህ አቤል ወዴት ነው ? እርሱም አለ ። አላውቅም ፤ የወንድሜ ጠባቂው እኔ ነኝን ?
(trg)="b.GEN.4.9.1"> ויאמר יהוה אל קין אי הבל אחיך ויאמר לא ידעתי השמר אחי אנכי ׃

(src)="b.GEN.4.10.1"> አለውም ። ምን አደረግህ ? የወንድምህ የደሙ ድምፅ ከምድር ወደ እኔ ይጮኻል ።
(trg)="b.GEN.4.10.1"> ויאמר מה עשית קול דמי אחיך צעקים אלי מן האדמה ׃

(src)="b.GEN.4.11.1"> አሁንም የወንድምህን ደም ከእጅህ ለመቀበል አፍዋን በከፈተች በምድር ላይ አንተ የተረገምህ ነህ ።
(trg)="b.GEN.4.11.1"> ועתה ארור אתה מן האדמה אשר פצתה את פיה לקחת את דמי אחיך מידך ׃

(src)="b.GEN.4.12.1"> ምድርንም ባረስህ ጊዜ እንግዲህ ኃይልዋን አትሰጥህም ፤ በምድርም ላይ ኰብላይና ተቅበዝባዥ ትሆናለህ ።
(trg)="b.GEN.4.12.1"> כי תעבד את האדמה לא תסף תת כחה לך נע ונד תהיה בארץ ׃

(src)="b.GEN.4.13.1"> ቃየንም እግዚአብሔርን አለው ። ኃጢአቴ ልሸከማት የማልችላት ታላቅ ናት ።
(trg)="b.GEN.4.13.1"> ויאמר קין אל יהוה גדול עוני מנשא ׃

(src)="b.GEN.4.14.1"> እነሆ ዛሬ ከምድር ፊት አሳደድኸኝ ፤ ከፊትህም እሰወራለሁ ፤ በምድርም ላይ ኰብላይና ተቅበዝባዥ እሆናለሁ ፤ የሚያገኘኝም ሁሉ ይገድለኛል ።
(trg)="b.GEN.4.14.1"> הן גרשת אתי היום מעל פני האדמה ומפניך אסתר והייתי נע ונד בארץ והיה כל מצאי יהרגני ׃

(src)="b.GEN.4.15.1"> እግዚአብሔርም እርሱን አለው ። እንግዲህ ቃየንን የገደለ ሁሉ ሰባት እጥፍ ይበቀልበታል ። እግዚአብሔርም ቃየንን ያገኘው ሁሉ እንዳይገድለው ምልክት አደረገለት ።
(trg)="b.GEN.4.15.1"> ויאמר לו יהוה לכן כל הרג קין שבעתים יקם וישם יהוה לקין אות לבלתי הכות אתו כל מצאו ׃

(src)="b.GEN.4.16.1"> ቃየንም ከእግዚአብሔር ፊት ወጣ ፤ ከዔድንም ወደ ምሥራቅ በኖድ ምድር ተቀመጠ ።
(trg)="b.GEN.4.16.1"> ויצא קין מלפני יהוה וישב בארץ נוד קדמת עדן ׃

(src)="b.GEN.4.17.1"> ቃየንም ሚስቱን አወቀ ፤ ፀነሰችም ፥ ሄኖሕንም ወለደች ። ከተማም ሠራ ፥ የከተማይቱንም ስም በልጁ ስም ሄኖሕ አላት ።
(trg)="b.GEN.4.17.1"> וידע קין את אשתו ותהר ותלד את חנוך ויהי בנה עיר ויקרא שם העיר כשם בנו חנוך ׃

(src)="b.GEN.4.18.1"> ሄኖሕም ጋይዳድን ወለደ ፤ ጋይዳድም ሜኤልን ወለደ ፤ ሜኤልም ማቱሣኤልን ወለደ ፤ ማቱሣኤልም ላሜሕን ወለደ ።
(trg)="b.GEN.4.18.1"> ויולד לחנוך את עירד ועירד ילד את מחויאל ומחייאל ילד את מתושאל ומתושאל ילד את למך ׃

(src)="b.GEN.4.19.1"> ላሜሕም ለራሱ ሁለት ሚስቶችን አገባ ፤ የአንዲቱ ስም ዓዳ ፥ የሁለተኛይቱ ስም ሴላ ነበረ ።
(trg)="b.GEN.4.19.1"> ויקח לו למך שתי נשים שם האחת עדה ושם השנית צלה ׃

(src)="b.GEN.4.20.1"> ዓዳም ያባልን ወለደች ፤ እርሱም በድንኳን የሚቀመጡት የዘላኖች አባት ነበረ ።
(trg)="b.GEN.4.20.1"> ותלד עדה את יבל הוא היה אבי ישב אהל ומקנה ׃