# am/Amharic.xml.gz
# chr/Cherokee-NT.xml.gz


(src)="b.MAT.1.1.1"> የዳዊት ልጅ የአብርሃም ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ትውልድ መጽሐፍ ።
(trg)="b.MAT.1.1.1"> ᎯᎠ ᎪᏪᎵ ᎧᏃᎮᎭ ᏧᏁᏢᏔᏅᏒ ᏥᏌ ᎦᎶᏁᏛ , ᏕᏫ ᎤᏪᏥ , ᎡᏆᎭᎻ ᎤᏪᏥ .

(src)="b.MAT.1.2.1"> አብርሃም ይስሐቅን ወለደ ፤ ይስሐቅም ያዕቆብን ወለደ ፤ ያዕቆብም ይሁዳንና ወንድሞቹን ወለደ ፤
(trg)="b.MAT.1.2.1"> ᎡᏆᎭᎻ ᎡᏏᎩ ᎤᏕᏁᎴᎢ ; ᎡᏏᎩᏃ ᏤᎦᏈ ᎤᏕᏁᎴᎢ , ᏤᎦᏈᏃ ᏧᏓ ᎠᎴ ᎾᏍᎩ ᎠᎾᏓᏅᏟ ᎬᏩᏕᏁᎴᎢ ;

(src)="b.MAT.1.3.1"> ይሁዳም ከትዕማር ፋሬስንና ዛራን ወለደ ፤ ፋሬስም ኤስሮምን ወለደ ፤
(trg)="b.MAT.1.3.1"> ᏧᏓᏃ ᏇᎵᏏ ᎠᎴ ᏎᎳ ᎬᏩᏕᏁᎴᎢ ᏖᎹ ᏚᎾᏄᎪᏫᏎᎢ ; ᏇᎵᏏᏃ ᎢᏏᎳᎻ ᎤᏕᏁᎴᎢ ; ᎢᏏᎳᎻᏃ ᎡᎵᎻ ᎤᏕᏁᎴᎢ ;

(src)="b.MAT.1.4.1"> ኤስሮምም አራምን ወለደ ፤ አራምም አሚናዳብን ወለደ ፤ አሚናዳብም ነአሶንን ወለደ ፤ ነአሶንም ሰልሞንን ወለደ ፤
(trg)="b.MAT.1.4.1"> ᎡᎵᎻᏃ ᎡᎻᏂᏓᏈ ᎤᏕᏁᎴᎢ ; ᎡᎻᏂᏓᏈᏃ ᎾᏐᏂ ᎤᏕᏁᎴᎢ ; ᎾᏐᏂᏃ ᏌᎵᎹ ᎤᏕᏁᎴᎢ ;

(src)="b.MAT.1.5.1"> ሰልሞንም ከራኬብ ቦኤዝን ወለደ ፤ ቦኤዝም ከሩት ኢዮቤድን ወለደ ፤ ኢዮቤድም እሴይን ወለደ ፤
(trg)="b.MAT.1.5.1"> ᏌᎵᎹᏃ ᏉᏏ ᎤᏕᏁᎴᎢ ᎴᎭᏫ ᎤᎾᎸᎪᏫᏎᎢ ; ᏉᏏᏃ ᎣᏇᏗ ᎤᏕᏁᎴᎢ ᎷᏏ ᎤᎾᏄᎪᏫᏎᎢ ; ᎣᏇᏗᏃ ᏤᏏ ᎤᏕᏁᎴᎢ ;

(src)="b.MAT.1.6.1"> እሴይም ንጉሥ ዳዊትን ወለደ ።
(trg)="b.MAT.1.6.1"> ᏤᏏᏃ ᏕᏫ ᎤᎬᏫᏳᎯ ᎤᏕᏁᎴᎢ ; ᏕᏫᏃ ᎤᎬᏫᏳᎯ ᏐᎵᎹᏅ ᎤᏕᏁᎴᎢ ᏳᎳᏯ ᎤᏓᏴᏛ ᎤᎾᏄᎪᏫᏎᎢ ;

(src)="b.MAT.1.7.1"> ሰሎሞንም ሮብዓምን ወለደ ፤ ሮብዓምም አቢያን ወለደ ፤ አቢያም አሣፍን ወለደ ፤
(trg)="b.MAT.1.7.1"> ᏐᎵᎹᏅᏃ ᎶᏉᎹ ᎤᏕᏁᎴᎢ ; ᎶᏉᎹᏃ ᎡᏆᏯ ᎤᏕᏁᎴᎢ ; ᎡᏆᏯᏃ ᎡᏏ ᎤᏕᏁᎴᎢ ;

(src)="b.MAT.1.8.1"> አሣፍም ኢዮሣፍጥን ወለደ ፤ ኢዮሣፍጥም ኢዮራምን ወለደ ፤ ኢዮራምም ዖዝያንን ወለደ ፤
(trg)="b.MAT.1.8.1"> ᎡᏏᏃ ᏦᏏᏆ ᎤᏕᏁᎴᎢ . ᏦᏏᏆᏃ ᏦᎳᎻ ᎤᏕᏁᎴᎢ ; ᏦᎳᎻᏃ ᎣᏌᏯ ᎤᏕᏁᎴᎢ ;

(src)="b.MAT.1.9.1"> ዖዝያንም ኢዮአታምን ወለደ ፤ ኢዮአታምም አካዝን ወለደ ፤
(trg)="b.MAT.1.9.1"> ᎣᏌᏯᏃ ᏦᏓᎻ ᎤᏕᏁᎴᎢ ; ᏦᏓᎻᏃ ᎡᎭᏏ ᎤᏕᏁᎴᎢ ; ᎡᎭᏏᏃ ᎮᏏᎦᏯ ᎤᏕᏁᎴᎢ ;

(src)="b.MAT.1.10.1"> አካዝም ሕዝቅያስን ወለደ ፤ ሕዝቅያስም ምናሴን ወለደ ፤ ምናሴም አሞፅን ወለደ ፤
(trg)="b.MAT.1.10.1"> ᎮᏏᎦᏯᏃ ᎹᎾᏏ ᎤᏕᏁᎴᎢ ; ᎹᎾᏏᏃ ᎠᎼᏂ ᎤᏕᏁᎴᎢ ; ᎠᎼᏂᏃ ᏦᏌᏯ ᎤᏕᏁᎴᎢ ;

(src)="b.MAT.1.11.1"> አሞፅም ኢዮስያስን ወለደ ፤ ኢዮስያስም በባቢሎን ምርኮ ጊዜ ኢኮንያንንና ወንድሞቹን ወለደ ።
(trg)="b.MAT.1.11.1"> ᏦᏌᏯᏃ ᏤᎪᎾᏯ ᎠᎴ ᎠᎾᏓᏅᏟ ᎬᏩᏕᏁᎴᎢ ; ᎾᎯᏳ ᏓᏗᎶᏂ ᏥᏫᏗᎨᎦᏘᏅᏍᏔᏁᎢ ;

(src)="b.MAT.1.12.1"> ከባቢሎንም ምርኮ በኋላ ኢኮንያን ሰላትያልን ወለደ ፤ ሰላትያልም ዘሩባቤልን ወለደ ፤
(trg)="b.MAT.1.12.1"> ᏓᏗᎶᏂᏃ ᏫᏗᎨᎦᏘᏃᎸ ᏤᎪᎾᏯ ᏌᎳᏓᏱᎵ ᎤᏕᏁᎴᎢ ; ᏌᎳᏓᏱᎵᏃ ᏥᎳᏇᎵ ᎤᏕᏁᎴᎢ ;

(src)="b.MAT.1.13.1"> ዘሩባቤልም አብዩድን ወለደ ፤ አብዩድም ኤልያቄምን ወለደ ፤ ኤልያቄምም አዛርን ወለደ ፤
(trg)="b.MAT.1.13.1"> ᏥᎳᏇᎵᏃ ᎠᏆᏯᏗ ᎤᏕᏁᎴᎢ , ᎠᏆᏯᏗᏃ ᎢᎳᏯᎩᎻ ᎤᏕᏁᎴᎢ ; ᎢᎳᏯᎩᎻᏃ ᎡᏐ ᎤᏕᏁᎴᎢ ;

(src)="b.MAT.1.14.1"> አዛርም ሳዶቅን ወለደ ፤ ሳዶቅም አኪምን ወለደ ፤ አኪምም ኤልዩድን ወለደ ፤
(trg)="b.MAT.1.14.1"> ᎡᏐᏃ ᏎᏙᎩ ᎤᏕᏁᎴᎢ ; ᏎᏙᎩᏃ ᎡᎩᎻ ᎤᏕᏁᎴᎢ ; ᎡᎩᎻᏃ ᎢᎳᏯᏗ ᎤᏕᏁᎴᎢ ;

(src)="b.MAT.1.15.1"> ኤልዩድም አልዓዛርን ወለደ ፤ አልዓዛርም ማታንን ወለደ ፤ ማታንም ያዕቆብን ወለደ ፤
(trg)="b.MAT.1.15.1"> ᎢᎳᏯᏗᏃ ᎢᎵᎡᏌ ᎤᏕᏁᎴᎢ ; ᎢᎵᎡᏌᏃ ᎹᏓᏂ ᎤᏕᏁᎴᎢ ; ᎹᏓᏂᏃ ᏤᎦᏈ ᎤᏕᏁᎴᎢ ;

(src)="b.MAT.1.16.1"> ያዕቆብም ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን የወለደች የማርያምን እጮኛ ዮሴፍን ወለደ ።
(trg)="b.MAT.1.16.1"> ᏤᎦᏈᏃ ᏦᏩ ᎤᏕᏁᎴᎢ , ᎾᏍᎩ ᎺᎵ ᎤᏰᎯ ᎾᏍᎩ ᏧᎾᏄᎪᏫᏎ ᏥᏌ ᎦᎶᏁᏛ ᏣᏃᎭᎰᎢ .

(src)="b.MAT.1.17.1"> እንግዲህ ትውልድ ሁሉ ከአብርሃም እስከ ዳዊት አሥራ አራት ትውልድ ፥ ከዳዊትም እስከ ባቢሎን ምርኮ አሥራ አራት ትውልድ ፥ ከባቢሎንም ምርኮ እስከ ክርስቶስ አሥራ አራት ትውልድ ነው ።
(trg)="b.MAT.1.17.1"> ᎾᏍᎩᏃ ᏂᎦᏛ ᏄᎾᏓᏁᏟᏴᏒ ᎡᏆᎭᎻ ᏤᎮ ᎾᎯᏳ ᏅᏓᎬᏩᏓᎴᏅᏛ ᏕᏫᏃ ᏤᎮ ᏅᏛᏍᏘ ᏂᎦᏚ ᏄᎾᏓᏁᏟᏴᏎᎢ ; ᏕᏫᏃ ᏤᎮ ᎾᎯᏳ ᏅᎵᎬᏩᏓᎴᏅᏛ ᏓᏗᎶᏂᏃ ᏥᏫᏗᎨᎦᏘᏅᏍᏔᏁ ᎾᎯᏳ ᏅᏛᏍᏘ ᏂᎦᏚ ᏄᎾᏓᏁᏟᏴᏎᎢ ; ᏓᏗᎶᏂᏃ ᎾᎯᏳ ᏥᏫᏗᎨᎦᏘᏅᏍᏔᏁ ᎤᏓᏳᏓᎴᏅᏛ ᏥᏌᏃ ᏧᏕᏁ ᎾᎯᏳ ᏅᏛᏍᏘ ᏂᎦᏚ ᏄᎾᏓᏁᏟᏴᏎᎢ .

(src)="b.MAT.1.18.1"> የኢየሱስ ክርስቶስም ልደት እንዲህ ነበረ ። እናቱ ማርያም ለዮሴፍ በታጨች ጊዜ ሳይገናኙ ከመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች ።
(trg)="b.MAT.1.18.1"> ᎾᏍᎩᏃ ᎯᎠ ᏄᎵᏍᏔᏂᏙᎴ ᎤᏕᏅᏥᏌ ᎦᎶᏁᏛ . ᎾᏍᎩ ᎺᎵ ᏥᏌ ᎤᏥ ᏦᏩ ᎤᏓᏴᏍᏗ , ᎠᏏᏉ ᏂᏓᎾᏤᎬᎾ ᎨᏎᎢ , ᎤᏁᎵᏤ ᎦᎸᏉᏗᏳ ᎠᏓᏅᏙ ᎤᏓᏅᏖᎸᎯ .

(src)="b.MAT.1.19.1"> እጮኛዋ ዮሴፍም ጻድቅ ሆኖ ሊገልጣት ስላልወደደ በስውር ሊተዋት አሰበ ።
(trg)="b.MAT.1.19.1"> ᏦᏩ ᎾᏍᎩ Ꮎ ᏧᎾᏨᏍᏗ ᎤᏓᏅᏘᏳ ᎨᏒ ᎢᏳᏍᏗ , ᎠᎴ ᏄᏚᎵᏍᎬᎾ ᎨᏒ ᎢᏳᏍᏗ ᎬᏂᎨᏒ ᎤᏕᎰᎯᏍᏙᏗᏱ , ᎤᏕᎵᏛᏉ ᎢᏴᏛ ᏮᏓᏥᏯᎧᏂ , ᎤᏪᎵᏎᎢ .

(src)="b.MAT.1.20.1"> እርሱ ግን ይህን ሲያስብ ፥ እነሆ የጌታ መልአክ በሕልም ታየው ፥ እንዲህም አለ ። የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ ፥ ከእርስዋ የተፀነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ ።
(trg)="b.MAT.1.20.1"> ᎠᏎᏃ ᎠᏏᏉ ᎯᎠ ᎾᏍᎩ ᏄᏍᏕᎠᏓᏅᏖᏍᎨᎢ , ᎬᏂᏳᏉ ᏗᎧᎿᏩᏗᏙᎯ ᏱᎰᏩ ᎤᏅᏏᏛ ᎬᏂᎨᏒ ᏄᏛᏁᎴ ᎠᏍᎩᏓᏍᎬᎢ , ᎯᎠ ᏂᎦᏪᏍᎨᎢ ; ᏦᏩ , ᏕᏫ ᎤᏪᏥ , ᏞᏍᏗ ᏣᏍᎦᎸ ᎯᏯᏅᏗᏱ ᎺᎵ ᏣᏓᏴᏍᏗ , ᎾᏍᎩᏰᏃ Ꮎ ᏥᎦᏁᎵ ᎦᎸᏉᏗᏳ ᎠᏓᏅᏙ ᎤᏓᏅᏖᎸᎯ ;

(src)="b.MAT.1.21.1"> ልጅም ትወልዳለች ፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ ።
(trg)="b.MAT.1.21.1"> ᎠᎴ ᏓᎦᎾᏄᎪᏫᏏ ᎠᏧᏣ , ᎾᏍᎩᏃ ᏥᏌ ᏕᎯᏲᎥᎭ , ᏧᏤᎵᏰᏃ ᏴᏫ ᏙᏛᏍᏕᎸᎯ ᏙᏓᎫᏓᎴᏏ ᎤᏂᏍᎦᏅᏨᎢ .

(src)="b.MAT.1.22.1"> በነቢይ ከጌታ ዘንድ ።
(trg)="b.MAT.1.22.1"> ᎾᏍᎩᏃ ᎯᎠ ᏂᎦᏗᏳ ᏄᎵᏍᏔᏂᏙᎴ ᎤᏙᎯᏳᏗᏱ ᎠᏰᎸᏒᎢ ᎯᎠ ᏥᏄᏪᏎ ᏱᎰᏩ ᎠᏙᎴᎰᏍᎩ ᎠᎬᏗᏍᎬᎢ ;

(src)="b.MAT.1.23.1"> እነሆ ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች ፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል ፥ ትርጓሜውም ። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው ።
(trg)="b.MAT.1.23.1"> ᎬᏂᏳᏉ ᎠᏛ ᎾᏥᏰᎲᎾ ᎦᏁᎵᏛ ᎨᏎᏍᏗ , ᎠᎴ ᏓᎦᎾᏄᎪᏫᏏ ᎠᏧᏣ , ᎾᏍᎩᏃ ᎢᎹᏄᎡᎵ ᎠᏃᏎᎮᏍᏗ , ᎾᏍᎩ ᎠᏁᏢᏔᏅᎯ ᎨᏒ ᎯᎠ ᏄᏍᏗ ᎦᏛᎦ , ᎤᏁᎳᏅᎯ ᎢᎨᎳᏗᏙᎭ .

(src)="b.MAT.1.24.1"> ዮሴፍም ከእንቅልፉ ነቅቶ የጌታ መልአክ እንዳዘዘው አደረገ ፤ እጮኛውንም ወሰደ ፤
(trg)="b.MAT.1.24.1"> ᏦᏩᏃ ᎤᏰᏨ ᎤᎸᏅᎢ ᏗᎧᎿᏩᏗᏙᎯ ᏱᎰᏩ ᏅᏓᏳᏅᏏᏛ ᏄᏪᏎᎸ ᏄᏛᏁᎴᎢ , ᎤᏯᏅᎨᏉ ᎤᏓᏴᏍᏗ .

(src)="b.MAT.1.25.1"> የበኩር ልጅዋንም እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም ፤ ስሙንም ኢየሱስ አለው ።
(trg)="b.MAT.1.25.1"> ᎠᎴ ᎥᏝ ᏳᎦᏙᎥᏎᎢ ᎬᏂ ᎤᎾᏄᎪᏫᏒ ᎢᎬᏱ ᎡᎯ ᎤᏪᏥ ᎠᏧᏣ , ᏥᏌᏃ ᏑᏬᎡᎢ .

(src)="b.MAT.2.1.1"> ኢየሱስም በይሁዳ ቤተ ልሔም በንጉሡ በሄሮድስ ዘመን በተወለደ ጊዜ ፥ እነሆ ፥ ሰብአ ሰገል ። የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው ? ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና እያሉ ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ ።
(trg)="b.MAT.2.1.1"> ᏥᏌᏃ ᎤᏕᏅ ᎦᏚᏱ ᎦᏚᎲ ᏧᏗᏱ , ᎾᎯᏳ ᏤᎮ ᎡᎶᏛ ᎤᎬᏫᏳᎯ , ᎬᏂᏳᏉ ᎤᏂᎷᏤ ᏥᎷᏏᎵᎻ ᎠᏂᎦᏔᎿᎢ ᏅᏙ ᏗᎧᎸᎬ ᎢᏗᏢ ᏧᏂᎶᏎᎢ ,

(src)="b.MAT.2.3.1"> ንጉሡ ሄሮድስም ሰምቶ ደነገጠ ፥ ኢየሩሳሌምም ሁሉ ከእርሱ ጋር ፤
(trg)="b.MAT.2.3.1"> ᎡᎶᏛᏃ ᎤᎬᏫᏳᎯ ᎤᏛᎦᏅ ᎾᏍᎩ , ᎤᏪᎵᎯᏍᏗ ᎤᏓᏅᏓᏕᎢ , ᎠᎴ ᏂᎦᏛ ᏥᎷᏏᎵᎻ ᎠᏁᎯ .

(src)="b.MAT.2.4.1"> የካህናትንም አለቆች የሕዝቡንም ጻፎች ሁሉ ሰብስቦ ክርስቶስ ወዴት እንዲወለድ ጠየቃቸው ።
(trg)="b.MAT.2.4.1"> ᏚᎳᏫᏛᏃ ᏂᎦᏛ ᏄᏂᎬᏫᏳᏒ ᎠᏥᎸ ᎠᏁᎶᎯ , ᎠᎴ ᏴᏫ ᏗᏃᏪᎳᏁᎯ , ᏚᏛᏛᏁᎢ , ᎾᎿ ᎤᏕᏗ ᎨᏒ ᎦᎶᏁᏛ .

(src)="b.MAT.2.5.1"> እነርሱም ። አንቺ ቤተ ልሔም ፥ የይሁዳ ምድር ፥ ከይሁዳ ገዢዎች ከቶ አታንሽም ፤ ሕዝቤን እስራኤልን የሚጠብቅ መስፍን ከአንቺ ይወጣልና ተብሎ በነቢይ እንዲህ ተጽፎአልና በይሁዳ ቤተ ልሔም ነው አሉት ።
(trg)="b.MAT.2.5.1"> ᎯᎠᏃ ᏂᎬᏩᏪᏎᎴᎢ ; ᏧᏗᏱ ᎦᏚᏱ ᎦᏚᎲᎢ ; ᎯᎠᏰᏃ ᏄᏩᏅ ᎤᏬᏪᎳ ᎠᏙᎴᎰᏍᎩ ;

(src)="b.MAT.2.7.1"> ከዚህ በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገልን በስውር ጠርቶ ኮከቡ የታየበትን ዘመን ከእነርሱ በጥንቃቄ ተረዳ ፥
(trg)="b.MAT.2.7.1"> ᎿᏉᏃ ᎡᎶᏛ ᎤᏕᎵᏛ ᏫᏚᏯᏅᎲ ᎾᏍᎩ ᎠᏂᎦᏔᎿᎢ , ᎣᏍᏛ ᏚᏛᏘᏌᏁ ᎢᏳᏉ ᎾᏍᎩ ᏃᏈᏏ ᎤᎾᏄᎪᏨᎢ .

(src)="b.MAT.2.8.1"> ወደ ቤተ ልሔምም እነርሱን ሰድዶ ። ሂዱ ፥ ስለ ሕፃኑ በጥንቃቄ መርምሩ ፤ ባገኛችሁትም ጊዜ እኔ ደግሞ መጥቼ እንድሰግድለት ንገሩኝ አላቸው ።
(trg)="b.MAT.2.8.1"> ᎠᎴ ᏚᏅᏎ ᎦᏚᏱ , ᎯᎠ ᏄᏪᏎᎢ ; ᎢᏤᎾ ᎣᏍᏛ ᏪᏥᏲᎦ ᎾᏍᎩ ᎤᏍᏗ ᎠᏲᎵ , ᎢᏳᏃ ᎡᏥᏩᏛᎲᎭ , ᎢᏍᎩᏃᏁᎵᎸᎭ , ᎠᏴᏃ ᎾᏍᏉ ᏫᏥᎷᏨᎭ , ᎠᎴ ᏥᏯᏓᏙᎵᏍᏓᏁᎸᎭ .

(src)="b.MAT.2.9.1"> እነርሱም ንጉሡን ሰምተው ሄዱ ፤ እነሆም ፥ በምሥራቅ ያዩት ኮከብ ሕፃኑ ባለበት ላይ መጥቶ እስኪቆም ድረስ ይመራቸው ነበር ።
(trg)="b.MAT.2.9.1"> ᎤᎾᏛᎦᏃᏁᎸᏃ ᎤᎬᏫᏳᎯ ᎤᎾᏂᎩᏎᎢ , ᎬᏂᏳᏉᏃ ᏃᏈᏏ , ᎾᏍᎩ ᎤᏂᎪᎲᎯ ᏗᎧᎸᎬ ᎢᏗᏢ , ᎢᎬᏱ ᎤᏁᏅᎡᎴᎢ , ᎬᏂ ᏭᎷᏥᎸ ᎠᎴ ᎤᎴᏫᏍᏔᏅ ᎦᎸᎳᏗᏢ ᎾᎿ ᎠᏥᎵ ᎡᎲᎢ .

(src)="b.MAT.2.10.1"> ኮከቡንም ባዩ ጊዜ በታላቅ ደስታ እጅግ ደስ አላቸው ።
(trg)="b.MAT.2.10.1"> ᎤᏂᎪᎲᏃ ᎾᏍᎩ ᏃᏈᏏ , ᎤᎶᏔᏅᎯ ᎤᎾᎵᎮᎵᏤᎢ .

(src)="b.MAT.2.11.1"> ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት ፥ ወድቀውም ሰገዱለት ፥ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤም አቀረቡለት ።
(trg)="b.MAT.2.11.1"> ᎠᏓᏁᎸᏃ ᎤᏂᏴᎸ ᎤᏂᎪᎮ ᎠᏲᏝ ᎠᎴ ᎤᏥ ᎺᎵ , ᎠᎴ ᎡᎳᏗ ᏚᎾᏓᏅᏁᎢ , ᎤᎾᏓᏙᎵᏍᏓᏁᎴᎢ , ᎠᎴ ᏧᎬᏩᎶᏗ ᎤᏂᎳᏅᏛ ᏚᏂᏍᏚᎢᏒ ᎤᏂᏁᎸᏁ ᏅᎾᎵᏍᎪᎸᏔᏅᎯ , ᎠᏕᎸ-ᏓᎶᏂᏛ , ᎠᎴ ᎤᎦᎾᏍᏛ ᎦᏩᏒᎩ ᎠᏜ , ᎠᎴ ᎻᎳ .

(src)="b.MAT.2.12.1"> ወደ ሄሮድስም እንዳይመለሱ በሕልም ተረድተው በሌላ መንገድ ወደ አገራቸው ሄዱ ።
(trg)="b.MAT.2.12.1"> ᎠᎾᏍᎩᏓᏍᎬᏃ ᎤᏁᎳᏅᎯ ᏚᏁᏤᎸ ᎡᎶᏛᏱ ᏭᏂᎶᎯᏍᏗᏱ ᏂᎨᏒᎾ , ᎤᎾᏂᎩᏒ ᎤᏣᏘᏂᏉ ᎢᏗᏢ ᏭᏂᎶᏎ ᎢᎤᏁᏅ ᎤᎾᏤᎵᎪᎯ .

(src)="b.MAT.2.13.1"> እነርሱም ከሄዱ በኋላ እነሆ ፥ የጌታ መልአክ በሕልም ለዮሴፍ ታይቶ ። ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይፈልገዋልና ተነሣ ፥ ሕፃኑንና እናቱንም ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ ፥ እስክነግርህም ድረስ በዚያ ተቀመጥ አለው ።
(trg)="b.MAT.2.13.1"> ᎤᎾᏂᎩᏒᏃ ᎬᏂᏳᏉ ᏗᎧᎿᏩᏗᏙᎯ ᎤᏅᏏᏛ ᏱᎰᏩ ᎬᏂᎨᏒ ᏄᏛᏁᎴ ᏦᏩ ᎠᏍᎩᏓᏍᎬᎢ , ᎯᎠ ᏄᏪᏎᎴᎢ ; ᏔᎴᎲᎦ , ᎠᎴ ᏔᏘᏄᎦ ᎠᏲᎵ ᎠᎴ ᎤᏥ ᎠᎴ ᎭᎵᏘ , ᎢᏥᏈ ᏫᎶᎯ , ᎾᎿᏃ ᏪᎮᏍᏗ ᎬᏂ ᏫᎬᏁᏤᎸᎭ , ᎡᎶᏛᏰᏃ ᎠᏎ ᏛᏲᎵ ᎤᏍᏗ ᎠᏲᎵ ᎤᎯᏍᏗᏱ .

(src)="b.MAT.2.14.1"> እርሱም ተነሥቶ ሕፃኑንና እናቱን በሌሊት ያዘና ከጌታ ዘንድ በነቢይ ። ልጄን ከግብፅ ጠራሁት የተባለው እንዲፈጸም ወደ ግብፅ ሄደ ፥ ሄሮድስም እስኪሞት ድረስ በዚያ ኖረ ።
(trg)="b.MAT.2.14.1"> ᎿᏉᏃ ᏚᎴᏅ ᎤᏘᏅᏎ ᎠᏲᎵ ᎠᎴ ᏅᏥ ᏒᏃᏱ , ᎠᎴ ᎢᏥᏈᏱ ᏭᎶᏎᎢ .

(src)="b.MAT.2.16.1"> ከዚህ በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገል እንደ ተሣለቁበት ባየ ጊዜ እጅግ ተቆጣና ልኮ ከሰብአ ሰገል እንደ ተረዳው ዘመን በቤተ ልሔምና በአውራጃዋ የነበሩትን ፥ ሁለት ዓመት የሆናቸውን ከዚያም የሚያንሱትን ሕፃናት ሁሉ አስገደለ ።
(trg)="b.MAT.2.16.1"> ᎿᏉᏃ ᎡᎶᏛ ᎤᏙᎴᎰᏒ ᎠᏂᎦᏔᎿᎢ ᎬᏩᎵᏓᏍᏔᏅᎢ , ᎤᏣᏔᏅᎯ ᎤᏔᎳᏬᏎᎢ , ᎠᎴ ᎤᏓᏅᏎ ᏫᏚᏂᎰᏁ ᏂᎦᏛ ᏗᏂᏲᎵ ᎦᏚᏱ ᎠᏁᎯ , ᎠᎴ ᏂᎦᏛ ᏂᎬᎾᏛ ᎾᎿᏂ , ᏔᎵ ᎢᏳᎾᏕᏘᏴᏛ ᏩᏍᏘ , ᎾᎯᏳ ᏅᏓᏳᏓᎴᏅᏛ ᏥᏓᎵᏏᎾᎯᏍᏓᏁᎮ ᏥᏓᏛᏛᎮᎸᎥᏍᎨ ᎠᏂᎦᏔᎿᎢ .

(src)="b.MAT.2.17.1"> ያን ጊዜ በነቢዩ በኤርምያስ ፥ ድምፅ በራማ ተሰማ ፥ ልቅሶና ብዙ ዋይታ ፤ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች ፥ መጽናናትም አልወደደችም ፥ የሉምና የተባለው ተፈጸመ ።
(trg)="b.MAT.2.17.1"> ᎿᏉᏃ ᎤᏙᎯᏳᏁ ᏤᎵᎹᏯ ᎠᏙᎴᎰᏍᎩ ᎤᏁᏨᎯ , ᎠᎴ ᏥᏄᏪᏎᎢ ;

(src)="b.MAT.2.19.1"> ሄሮድስም ከሞተ በኋላ ፥ እነሆ ፥ የጌታ መልአክ በግብፅ ለዮሴፍ በሕልም ታይቶ ።
(trg)="b.MAT.2.19.1"> ᎿᏉᏃ ᎡᎶᏛ ᎤᏲᎱᏒ , ᎬᏂᏳᏉ ᏗᎧᎿᏩᏗᏙᎯ ᏱᎰᏩ ᎤᏤᎵᎦ ᎬᏂᎨᏒ ᏄᏛᏁᎴ ᏦᏩ ᎠᏍᎩᏓᏍᎬ ᎢᏥᏈᏱ ,

(src)="b.MAT.2.20.1"> የሕፃኑን ነፍስ የፈለጉት ሞተዋልና ተነሣ ፥ ሕፃኑን እናቱንም ይዘህ ወደ እስራኤል አገር ሂድ አለ ።
(trg)="b.MAT.2.20.1"> ᎯᎠ ᏄᏪᏎᎴᎢ ; ᏔᎴᎲᎦ ᎠᎴ ᎭᏘᏄᎦ ᎠᏲᎵ ᎠᎴ ᎤᏥ , ᎠᎴ ᎮᎾ ᎢᏏᎵᏱ , ᎿᏉᏰᏃ ᏚᏂᏲᎱᏒ ᎠᏲᎵ ᎬᏅ ᏧᏂᏲᎲᎩ .

(src)="b.MAT.2.21.1"> እርሱም ተነሥቶ ሕፃኑንና እናቱን ያዘና ወደ እስራኤል አገር ገባ ።
(trg)="b.MAT.2.21.1"> ᏚᎴᏅᏃ ᎤᏘᏅᏎ ᎠᏲᎵ ᎠᎴ ᎤᏥ , ᎠᎴ ᎢᏏᎵᏱ ᏭᎷᏤᎢ .

(src)="b.MAT.2.22.1"> በአባቱም በሄሮድስ ፈንታ አርኬላዎስ በይሁዳ እንደ ነገሠ በሰማ ጊዜ ፥ ወደዚያ መሄድን ፈራ ፤ በሕልምም ተረድቶ ወደ ገሊላ አገር ሄደ ፤
(trg)="b.MAT.2.22.1"> ᎠᏎᏃ ᎤᏛᎦᏅ ᎠᏥᎳ ᎤᎬᏫᏳᎯ ᎨᏒ ᏧᏗᏱ ᎤᏙᏓ ᎡᎶᏛ ᎤᏓᏁᏟᏴᏍᏓᏁᎸᎢ , ᎤᏍᎦᎴ ᎾᎿ ᏭᎶᎯᏍᏗᏱ ; ᎠᏎᏃ ᎤᏁᎳᏅᎯ ᎤᏪᏯᏔᏅᎯ ᎨᏒ ᎠᏍᎩᏓᏍᎬᎢ , ᎨᎵᎵ ᏭᎪᎸᏍᏔᏁᎢ ;

(src)="b.MAT.2.23.1"> በነቢያት ። ናዝራዊ ይባላል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ፥ ናዝሬት ወደምትባል ከተማ መጥቶ ኖረ ።
(trg)="b.MAT.2.23.1"> ᎦᏚᎲᏃ ᎾᏎᎵᏗ ᏧᏙᎢᏛ ᏭᎷᏨ ᎾᎿ ᎡᎮᎢ . ᎾᏍᎩᏃ ᎤᏙᎯᏳᏁ ᎠᎾᏙᎴᎰᏍᎩ ᏧᏂᏁᏤᎢ , ᎾᏎᎵᏗ ᎡᎯ ᎠᎪᏎᎮᏍᏗ , ᏧᎾᏛᏁᎢ .

(src)="b.MAT.3.1.1"> በዚያም ወራት መጥምቁ ዮሐንስ ። መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ ብሎ በይሁዳ ምድረ በዳ እየሰበከ መጣ ።
(trg)="b.MAT.3.1.1"> ᎾᎯᏳ ᎤᎷᏤ ᏣᏂ ᏗᏓᏬᏍᎩ ᎠᎵᏥᏙᎲᏍᎨ ᎢᎾᎨ ᏧᏗᏱ ,

(src)="b.MAT.3.3.1"> በነቢዩ በኢሳይያስ ። የጌታን መንገድ አዘጋጁ ጥርጊያውንም አቅኑ እያለ በምድረ በዳ የሚጮህ ሰው ድምፅ የተባለለት ይህ ነውና ።
(trg)="b.MAT.3.3.1"> ᎾᏍᎩ ᎯᎠ Ꮎ ᏥᎧᏁᎢᏍᏗᏍᎨ ᎠᏙᎴᎰᏍᎩ ᎢᏌᏯ , ᎯᎠ ᏥᏂᎦᏪᏍᎨᎢ ; ᎤᏪᎷᎦ ᎩᎶ ᎢᎾᎨᎢ , ᎯᎠ ᏂᎦᏪᎭ ; ᎣᏍᏛ ᏂᏨᎦ ᏱᎰᏩ ᎤᎶᎯᏍᏗᏱ , ᏚᏅᏅ ᏗᏥᏥᏃᎯᏍᏓ .

(src)="b.MAT.3.4.1"> ራሱም ዮሐንስ የግመል ጠጉር ልብስ ነበረው ፥ በወገቡም ጠፍር ይታጠቅ ነበር ፤ ምግቡም አንበጣና የበረሀ ማር ነበረ ።
(trg)="b.MAT.3.4.1"> ᎾᏍᎩᏃ ᎯᎠ ᏣᏂ ᎤᏄᏪ ᎨᎻᎵ ᎤᏍᏘᏰᏅᎯ , ᎦᏃᏥᏃ ᎤᏓᏠᏍᏕᎢ , ᎤᎵᏍᏓᏴᏗᏃ ᎥᎴ ᎨᏎ ᎢᎾᎨᏃ ᎡᎯ ᏩᏚᎵᏏ .

(src)="b.MAT.3.5.1"> ያን ጊዜ ኢየሩሳሌም ይሁዳም ሁሉ በዮርዳኖስም ዙሪያ ያለ አገር ሁሉ ወደ እርሱ ይወጡ ነበር ፤
(trg)="b.MAT.3.5.1"> ᎾᏉᏃ ᏫᎬᏩᎷᏤᎴ ᏥᎷᏏᎵᎻ ᎠᎴ ᏂᎦᏛ ᏧᏗᏱ , ᎠᎴ ᏂᎦᏛ ᎾᏅᎾᏛ ᏦᏓᏂ ,

(src)="b.MAT.3.6.1"> ኃጢአታቸውንም እየተናዘዙ በዮርዳኖስ ወንዝ ከእርሱ ይጠመቁ ነበር ።
(trg)="b.MAT.3.6.1"> ᏦᏓᏂᏃ ᏕᎤᏬᎡᎢ , ᎠᏂᏃᎲᏍᎨ ᎤᏂᏍᎦᏅᏨᎢ .

(src)="b.MAT.3.7.1"> ዳሩ ግን ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ብዙዎች ወደ ጥምቀቱ ሲመጡ ባየ ጊዜ ፥ እንዲህ አላቸው ። እናንተ የእፉኝት ልጆች ፥ ከሚመጣው ቍጣ እንድትሸሹ ማን አመለከታችሁ ?
(trg)="b.MAT.3.7.1"> ᎠᏎᏃ ᏚᎪᎲ ᎤᏂᏣᏘ ᎠᏂᏆᎵᏏ ᎠᎴ ᎠᏂᏌᏚᏏ ᎠᏂᎷᎬ ᏓᏓᏬᏍᎬᎢ , ᎯᎠ ᏂᏚᏪᎭᎴᎢ ; Ꮵ ! ᎢᎾᏛ ᏧᏁᏥ ᏂᎯ ! ᎦᎪ ᎢᏤᏯᏔᏅ ᎡᏣᎵᎡᏗᏱ ᎤᏔᎳᏬᎯᏍᏗ ᏨᏣᎢ ?

(src)="b.MAT.3.8.1"> እንግዲህ ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ ፤
(trg)="b.MAT.3.8.1"> ᎢᏥᎾᏄᎪᏩᏲᎪ ᎠᏙᎴᎰᎯᏍᏙᏗ ᏕᏥᏁᏟᏴᏒ ᏕᏣᏓᏅᏛᎢ ;

(src)="b.MAT.3.9.1"> በልባችሁም ። አብርሃም አባት አለን እንደምትሉ አይምሰላችሁ ፤ እላችኋለሁና ። ከነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆች ሊያስነሣለት እግዚአብሔር ይችላል ።
(trg)="b.MAT.3.9.1"> ᎠᎴ ᏝᏍᏗ ᎯᎠ ᏅᏓᏲᏥᏪᏏ ᎢᏤᎵᏒᎩ ᏙᏗᏣᏓᏅᏛᎢ ; ᎡᏆᎭᎻ ᎣᎩᏙᏓ ; ᎢᏨᏲᏎᏰᏃ ᎤᏁᎳᏅᎯ ᏰᎵᏉ ᎯᎠ ᏅᏯ ᏱᏕᎬᏓ ᏱᏕᎪᏢᎾ ᎡᏆᎭᎻ ᏧᏪᏥ .

(src)="b.MAT.3.10.1"> አሁንስ ምሳር በዛፎች ሥር ተቀምጦአል ፤ እንግዲህ መልካም ፍሬ የማያደርግ ዛፍ ሁሉ ይቈረጣል ወደ እሳትም ይጣላል ።
(trg)="b.MAT.3.10.1"> ᎠᎴ ᎾᏍᏉ ᎦᏳᎳ ᎦᎷᏯᏍᏗ ᎠᎭ ᏚᎿᏍᏕᏢ ᏕᏡᎬᎢ ; ᎾᏍᎩᏃ ᏂᎦᏛ ᏕᏡᎬ ᎠᏃᏍᏛ ᎾᎾᏓᏛᏍᎬᎾ ᏗᎦᎴᏴᏍᏙᏗ ᎠᎴ ᎠᏥᎸᏱ ᏫᏓᏗᏅᏗ ᎨᏎᏍᏗ .

(src)="b.MAT.3.11.1"> እኔስ ለንስሐ በውኃ አጠምቃችኋለሁ ፤ ጫማውን እሸከም ዘንድ የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይልቅ ይበረታል ፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስ በእሳትም ያጠምቃችኋል ፤
(trg)="b.MAT.3.11.1"> ᎠᏴ ᎤᏙᎯᏳᎯ ᎠᎹ ᏕᏨᏯᏬᏍᏗᎭ ᏗᏥᏁᏟᏴᏍᏗᏱ ᏕᏣᏓᏅᏛ ᎤᎬᏩᎵ ; ᎠᏎᏃ ᎾᏍᎩ Ꮎ ᎣᏂ ᏨᏓᏯᎢ ᎤᏟᎯᏳ ᎤᎵᏂᎩᏗᏳ ᎡᏍᎦᏉ ᎠᏴ , ᏧᎳᏑᎶ ᎥᏝ ᏰᎵ ᏱᏂᎪᎢ ᏗᎩᏂᏓᏍᏗᏱ ; ᎾᏍᎩᏍᎩᏂ ᎦᎸᏉᏗᏳ ᎠᏓᏅᏙ ᎠᎴ ᎠᏥᎸ ᏙᏓᏣᏬᏍᏔᏂ .

(src)="b.MAT.3.12.1"> መንሹም በእጁ ነው ፥ አውድማውንም ፈጽሞ ያጠራል ፥ ስንዴውንም በጎተራው ይከታል ፥ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል ።
(trg)="b.MAT.3.12.1"> ᎾᏍᎩ ᎦᎳᏐᏫᏍᏗ ᎤᏤᎵᎦ ᎠᏰᎭ , ᎠᎴ ᏂᎦᏛ ᏓᎦᎳᏐᏫᏏ , ᎤᏤᎵᏃ ᎤᎦᏔᏔᏅᎯ ᏓᎦᏟᏌᏂ ᏛᏂ ᎠᏓᎾᏅᏗᏱ ᎤᏘᏴᎯᏍᎩᏂ ᏛᎪᎲᏍᏔᏂ ᏂᎬᏠᏍᎬᎾ ᎠᏥᎸᏱ .

(src)="b.MAT.3.13.1"> ያን ጊዜ ኢየሱስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ ።
(trg)="b.MAT.3.13.1"> ᎿᏉᏃ ᏥᏌ ᎨᎵᎵ ᏧᎶᏎᎢ , ᏦᏓᏂ ᎤᎷᏤ ᏣᏂ ᎡᏙᎲᎢ ᎠᎦᏬᏍᏗᏱ ᎤᏰᎸᏎᎢ .

(src)="b.MAT.3.14.1"> ዮሐንስ ግን ። እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን ? ብሎ ይከለክለው ነበር ።
(trg)="b.MAT.3.14.1"> ᎠᏎᏃ ᏣᏂ ᏚᏢᏫᏎᎴᏉ , ᎯᎠ ᏄᏪᏎᎢ ; ᎠᏴᏍᎩᏂ ᏱᏍᏆᏬᎥ ; ᏥᎪᏃ ᎢᏍᎩᎷᏤᎭ ?

(src)="b.MAT.3.15.1"> ኢየሱስም መልሶ ። አሁንስ ፍቀድልኝ ፤ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና አለው ። ያን ጊዜ ፈቀደለት ።
(trg)="b.MAT.3.15.1"> ᏥᏌᏃ ᏧᏁᏨ ᎯᎠ ᏄᏪᏎᎴᎢ ; ᎤᏁᎳᎩ ᎮᎳ ᎪᎯ ᎨᏒᎢ , ᎣᏏᏳᏰᏃ ᎾᏍᎩ ᎢᎩᎾᏛᏁᏗᏱ ᎩᏂᏍᏆᏗᏍᏗᏱ ᏂᎦᎥ ᏚᏳᎪᏛ ᎨᏒᎢ . ᎩᎳ ᎤᏁᎳᎩ ᎤᏪᎵᏎᎴᎢ .

(src)="b.MAT.3.16.1"> ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኃ ወጣ ፤ እነሆም ፥ ሰማያት ተከፈቱ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ ፤
(trg)="b.MAT.3.16.1"> ᏥᏌᏃ ᎠᎦᏬᎥ , ᎩᎳᏉ ᎢᏴᏛ ᎤᎿᎷᏎᎢ , ᎠᎹᏱ ᎤᏓᏅᏎᎢ , ᎠᎴ ᎬᏂᏳᏉ ᎦᎸᎳᏗ ᏣᏥᏍᏚᎩᎡᎴᎢ , ᎠᎴ ᏭᎪᎮ ᎤᏁᎳᏅᎯ ᎤᏓᏅᏙ ᎡᎳᏗ ᏅᏧᏛᎿᏗᏎ ᎫᎴ-ᏗᏍᎪᏂᎯ ᏗᏤᎵᏛ ; ᎠᎴ ᎤᏪᏯᎸᏤᎢ .

(src)="b.MAT.3.17.1"> እነሆም ፥ ድምፅ ከሰማያት መጥቶ ። በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ ።
(trg)="b.MAT.3.17.1"> ᎠᎴ ᎬᏂᏳᏉ ᎯᎠ ᏅᏧᏪᏎ ᎦᎸᎳᏗ ; ᎯᎠ ᏥᎨᏳᎢ ᎠᏇᏥ , ᎾᏍᎩ ᎣᏏᏳ ᏥᏥᏰᎸᎠ .

(src)="b.MAT.4.1.1"> ከዚያ ወዲያ ኢየሱስ ከዲያብሎስ ይፈተን ዘንድ መንፈስ ወደ ምድረ በዳ ወሰደው ፥
(trg)="b.MAT.4.1.1"> ᎿᏉᏃ ᎠᏓᏅᏙ ᎢᎾᎨ ᏭᏘᏅᏍᏔᏁ ᏥᏌ , ᎠᏍᎩᎾ ᎤᎪᎵᏰᏗᏱ ᎠᏰᎸᏎᎢ .

(src)="b.MAT.4.2.1"> አርባ ቀንና አርባ ሌሊትም ከጦመ በኋላ ተራበ ።
(trg)="b.MAT.4.2.1"> ᏅᎦᏍᎪᎯᏃ ᏧᏙᏓᏆᏛ ᎠᎴ ᏅᎦᏍᎪᎯ ᏧᏒᎯᏛ ᎠᎹᏟ ᎤᏩᏅ ᎩᎳ ᎤᏲᏏᏌᏁᎢ

(src)="b.MAT.4.3.1"> ፈታኝም ቀርቦ ። የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ ፥ እነዚህ ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆኑ በል አለው ።
(trg)="b.MAT.4.3.1"> ᎿᏉᏃ ᎤᎪᎵᏰᏍᎩ ᎤᎷᏤᎸ ᎯᎠ ᏄᏪᏎᎢ ; ᎢᏳᏃ ᏂᎯ ᎤᏁᎳᏅᎯ ᎤᏪᏥ ᎨᏎᏍᏗ , ᎯᎠ ᏅᏯ ᎦᏚ ᎤᎾᏙᏢᏗᏱ ᎯᏁᎩ .

(src)="b.MAT.4.4.1"> እርሱም መልሶ ። ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል አለው ።
(trg)="b.MAT.4.4.1"> ᎠᏎᏃ ᎤᏁᏨ , ᎯᎠ ᏄᏪᏎᎢ ; ᎯᎠ ᏂᎬᏅ ᎪᏪᎳ , ᏴᏫ ᎥᏝ ᎦᏚᏉ ᎤᏩᏒ ᏱᎬᎿᏗᏍᏗ , ᏂᎦᎥᏍᎩᏂ ᎧᏃᎮᏛ ᎤᏁᎳᏅᎯ ᎠᎰᎵ ᏅᏓᏳᎾᏄᎪᏨᎯ .

(src)="b.MAT.4.5.1"> ከዚህ በኋላ ዲያቢሎስ ወደ ቅድስት ከተማ ወሰደውና እርሱን በመቅደስ ጫፍ ላይ አቁሞ ።
(trg)="b.MAT.4.5.1"> ᎿᏉᏃ ᎠᏍᎩᎾ ᎦᎸᏉᏗᏳ ᏗᎦᏚᎲ ᏭᏘᏅᏍᏔᏁᎢ , ᎠᎴ ᏭᎩᎸᏔᏁ ᎤᏍᎪᎵ ᎤᏛᏅ-ᏗᎦᎳᏫᎢᏍᏗᏱ ;

(src)="b.MAT.4.6.1"> መላእክቱን ስለ አንተ ያዝልሃል እግርህንም በድንጋይ ከቶ እንዳትሰናከል በእጃቸው ያነሡሃል ተብሎ ተጽፎአልና የእግዚአብሔር ልጅስ ከሆንህ ፥ ወደ ታች ራስህን ወርውር አለው ።
(trg)="b.MAT.4.6.1"> ᎯᎠᏃ ᏄᏪᏎᎴᎢ ; ᎢᏳᏃ ᏂᎯ ᎤᏁᎳᏅᎯ ᎤᏪᏥ ᎨᏎᏍᏗ , ᎭᏓᎶᎥᏓ ᏨᏒ ; ᎯᎠᏰᏃ ᏂᎬᏅ ᎢᎪᏪᎳ ; ᎠᏎ ᏙᏓᎧᏁᏤᎵ ᎫᏤᎵ ᏗᏂᎧᎿᏩᏗᏙᎯ ᏂᏌ ᎨᏒ ᎤᎬᏩᎵ , ᎠᎴ ᏧᏃᏰᏂ ᎨᏣᏌᎳᏙᏕᏍᏗ ᎾᏍᎩ ᎢᎸᎯᏳ ᏅᏲᎯ ᏣᎾᏍᏆᎶᏍᏙᏗᏱ ᏂᎨᏒᎾ .

(src)="b.MAT.4.7.1"> ኢየሱስም ። ጌታን አምላክህን አትፈታተነው ተብሎ ደግሞ ተጽፎአል አለው ።
(trg)="b.MAT.4.7.1"> ᏥᏌ ᎯᎠ ᏄᏪᏎᎴᎢ ; ᎯᎠ ᎾᏍᏉ ᏂᎬᏅ ᎢᎪᏪᎳ ; ᏞᏍᏗ ᎯᎪᎵᏰᎥᎩ ᏱᎰᏩ ᏣᏁᎳᏅᎯ .

(src)="b.MAT.4.8.1"> ደግሞ ዲያቢሎስ እጅግ ረጅም ወደ ሆነ ተራራ ወሰደው ፥ የዓለምንም መንግሥታት ሁሉ ክብራቸውንም አሳይቶ ።
(trg)="b.MAT.4.8.1"> ᎿᏆᎴ ᎠᏍᎩᎾ ᎤᏣᏘ ᎢᏅ-ᎢᎦᏘ ᎣᏓᎸ ᏫᎤᏘᏅᏍᏔᏁᎢ , ᎠᎴ ᏚᏎᎮᎴ ᏂᎦᎥ ᎠᏰᎵ ᏕᎪᏢᏩᏗᏒ ᎡᎳᏂᎬᎢ , ᎠᎴ ᎾᏍᎩ ᏂᏚᏬᏚᏒᎢ ;

(src)="b.MAT.4.9.1"> ወድቀህ ብትሰግድልኝ ይህን ሁሉ እሰጥሃለሁ አለው ።
(trg)="b.MAT.4.9.1"> ᎠᎴ ᎯᎠ ᏄᏪᏎᎴᎢ ; ᎯᎠ ᏂᎦᏛ ᏱᏕᎬᏲᎯᏏ , ᎢᏳᏃ ᏱᏣᏓᏅᏅ , ᎠᎴ ᏱᏍᏆᏓᏙᎵᏍᏓᏁᎸ .

(src)="b.MAT.4.10.1"> ያን ጊዜ ኢየሱስ ። ሂድ ፥ አንተ ሰይጣን ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፎአልና አለው ።
(trg)="b.MAT.4.10.1"> ᎿᏉᏃ ᏥᏌ ᎯᎠ ᏄᏪᏎᎴᎢ ; ᎤᏟ ᏫᎶᎯ , ᏎᏓᏂ , ᎯᎠᏰᏃ ᏂᎬᏅ ᎢᎪᏪᎳ ; ᎠᏎ ᎯᏯᏓᏙᎵᏍᏓᏁᎮᏍᏗ ᏱᎰᏩ ᏣᏁᎳᏅᎯ , ᎠᎴ ᎾᏍᎩᏉ ᎤᏩᏒᎯᏳ ᏕᎯᏯᏁᎶᏕᏍᏗ .

(src)="b.MAT.4.11.1"> ያን ጊዜ ዲያቢሎስ ተወው ፥ እነሆም ፥ መላእክት ቀርበው ያገለግሉት ነበር ።
(trg)="b.MAT.4.11.1"> ᎩᎳᏃ ᎠᏍᎩᎾ ᎤᏓᏅᎡᎴᎢ , ᎬᏂᏳᏉᏃ ᏗᏂᎧᎿᏩᏗᏙᎯ ᎤᏂᎷᏤᎢ , ᎠᎴ ᎬᏩᏍᏕᎸᎯᏙᎴᎢ .

(src)="b.MAT.4.12.1"> ኢየሱስም ዮሐንስ አልፎ እንደ ተሰጠ በሰማ ጊዜ ወደ ገሊላ ፈቀቅ ብሎ ሄደ ።
(trg)="b.MAT.4.12.1"> ᏥᏌᏃ ᎤᏛᎦᏅ ᏣᏂ ᎠᏥᏍᏚᎲᎢ , ᎨᎵᎵ ᏭᎶᏎᎢ .

(src)="b.MAT.4.13.1"> ናዝሬትንም ትቶ በዛብሎንና በንፍታሌም አገር በባሕር አጠገብ ወደ አለችው ወደ ቅፍርናሆም መጥቶ ኖረ ።
(trg)="b.MAT.4.13.1"> ᎾᏎᎵᏗᏃ ᎤᏓᏅᏒ ᎨᏆᏂ ᎨᎷᏤ ᎾᎿ ᏭᏕᏁᎢ , ᎾᏍᎩ ᎥᏓᎵ ᎠᎹᏳᎶᏗ ᏥᎦᏚᎭ , ᏤᏆᎳᏂ ᎠᎴ ᏁᏩᏔᎵ ᎤᎾᏤᎵᎪᎯ ,

(src)="b.MAT.4.14.1"> በነቢዩም በኢሳይያስ ። የዛብሎን ምድርና የንፍታሌም ምድር ፥ የባሕር መንገድ ፥ በዮርዳኖስ ማዶ ፥ የአሕዛብ ገሊላ ፤ በጨለማ የተቀመጠው ሕዝብ ታላቅ ብርሃን አየ ፥ በሞት አገርና ጥላ ለተቀመጡትም ብርሃን ወጣላቸው
(trg)="b.MAT.4.14.1"> ᎤᏙᎯᏳᏗᏱ ᎠᏙᎴᎰᏍᎩ ᎢᏌᏯ ᏧᏁᏤᎢ , ᎯᎠ ᏥᏄᏪᏎᎢ ;

(src)="b.MAT.4.17.1"> የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሆነ ። ከዚያ ዘመን ጀምሮ ኢየሱስ ። መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ እያለ ይሰብክ ጀመር ።
(trg)="b.MAT.4.17.1"> ᎾᎯᏳ ᏥᏌ ᎤᎴᏅᎮ ᎠᎵᏥᏙᎲᏍᎨᎢ , ᎯᎠ ᏂᎦᏪᏍᎨᎢ ; ᏗᏥᏁᏟᏴᎾ ᏕᏣᏓᏅᏛᎢ , ᎿᏉᏰᏃ ᎦᎸᎳᏗ ᎡᎯ ᎤᎬᏫᏳᎯ ᎨᏒ ᎡᏍᎦᏂᏳ ᏓᏯᎢ .

(src)="b.MAT.4.18.1"> በገሊላ ባሕር አጠገብ ሲመላለስም ሁለት ወንድማማች ጴጥሮስ የሚሉትን ስምዖንን ወንድሙንም እንድርያስን መረባቸውን ወደ ባሕር ሲጥሉ አየ ፥ ዓሣ አጥማጆች ነበሩና ።
(trg)="b.MAT.4.18.1"> ᏥᏌᏃ ᎠᎢᏒ ᎨᎵᎵ ᎥᏓᎷᎶᏗ ᏚᎪᎮ ᎠᏂᏔᎵ ᎠᎾᎵᏅᏟ , ᏌᏩᏂ ᏈᏓ ᏣᏃᏎᎰᎢ ᎤᏅᏟᏃ ᎡᏂᏗ , ᎥᏓᎵ ᎠᏂᎦᏯᎷᎥᏍᎨᎢ-ᎠᏂᎦᏯᎷᎥᏍᎩᏰᏃ ᎨᏎᎢ .

(src)="b.MAT.4.19.1"> እርሱም ። በኋላዬ ኑና ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ አላቸው ።
(trg)="b.MAT.4.19.1"> ᎯᎠᏃ ᏂᏚᏪᏎᎴᎢ ; ᏍᎩᏂᏍᏓᏩᏚᎦ , ᏴᏫᏃ ᎢᏍᏗᎦᏯᎷᎥᏍᎩ ᏅᏓᏍᏛᏴᏁᎵ .

(src)="b.MAT.4.20.1"> ወዲያውም መረባቸውን ትተው ተከተሉት ።
(trg)="b.MAT.4.20.1"> ᎩᎳᏉᏃ ᎢᏴᏛ ᏚᏂᏲᏎ ᏗᎦᏯᎷᏗ ᎠᎴ ᎬᏩᏍᏓᏩᏛᏎᎢ .

(src)="b.MAT.4.21.1"> ከዚያም እልፍ ብሎ ሌሎችን ሁለት ወንድማማች የዘብዴዎስን ልጅ ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ከአባታቸው ከዘብዴዎስ ጋር በታንኳ መረባቸውን ሲያበጁ አየ ፤ ጠራቸውም ።
(trg)="b.MAT.4.21.1"> ᎾᎿᏃ ᏫᎤᏪᏅ , ᎠᏂᏔᎵ ᏅᏩᎾᏓᎴ ᎠᎾᎵᏅᏟ ᏚᎪᎮᎢ , ᏥᎻ ᏤᏈᏗ ᎤᏪᏥ ᎤᏅᏟᏃ ᏣᏂ , ᏤᏈᏗ ᎤᏂᏙᏓ ᏥᏳᎯ ᎤᎾᏣᎡᎢ , ᏓᏃᏢᎯᏏᏍᎨ ᏧᏂᎦᏯᎷᏗ ; ᏫᏚᏯᏅᎮᏃ .

(src)="b.MAT.4.22.1"> እነርሱም ወዲያው ታንኳይቱንና አባታቸውን ትተው ተከተሉት ።
(trg)="b.MAT.4.22.1"> ᎩᎳᏉᏃ ᎢᏴᏛ ᏚᏂᏲᏎ ᏥᏳ ᎠᎴ ᎤᏂᏙᏓ , ᎠᎴ ᎬᏩᏍᏓᏩᏛᏎᎢ .

(src)="b.MAT.4.23.1"> ኢየሱስም በምኩራቦቻቸው እያስተማረ የመንግሥትንም ወንጌል እየሰበከ በሕዝብም ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ በገሊላ ሁሉ ይዞር ነበር ።
(trg)="b.MAT.4.23.1"> ᏥᏌᏃ ᏂᎬᎾᏛ ᎨᎵᎵ ᎡᏙᎮᎢ ᏓᏕᏲᎲᏍᎨ ᏧᏂᎳᏫᎢᏍᏗᏱ , ᎠᎴ ᎠᎵᏥᏙᎲᏍᎨ ᎣᏍᏛ ᎧᏃᎮᏛ , ᎤᏁᎳᏅᎯ ᎤᎬᏫᏳᎯ ᎨᏒ ᎧᏃᎮᏍᎨᎢ , ᎠᎴ ᏕᎧᏅᏫᏍᎨ ᏧᎵᎴᏅᏛ ᏚᏂᏢᎬᎢ , ᎠᎴ ᏧᏓᎴᏅᏛ ᎥᏳᎩ ᏴᏫ ᎤᏁᎲᎢ .

(src)="b.MAT.4.24.1"> ዝናውም ወደ ሶርያ ሁሉ ወጣ ፤ በልዩ ልዩ ደዌና ሥቃይም ተይዘው የታመሙትን ሁሉ አጋንንትም ያደሩባቸውን በጨረቃም የሚነሣባቸውን ሽባዎችንም ወደ እርሱ አመጡ ፥ ፈወሳቸውም ።
(trg)="b.MAT.4.24.1"> ᏕᎦᏃᏣᎸᏃ ᏂᎬᎾᏛ ᏏᎵᏱ ᎤᏰᎵᏎᎢ ; ᏕᎬᏩᏘᏃᎮᎴᏃ ᏂᎦᏛ ᏧᏂᏢᎩ , ᏧᏓᎴᏅᏛ ᎥᏳᎩ ᎠᎴ ᎡᎯᏍᏗ ᎤᏂᏱᎵᏙᎯ , ᎠᎴ ᎾᏍᏉ ᎠᏂᏍᎩᎾ ᏗᎬᏩᏂᏯᎢ , ᎠᎴ ᎾᏍᏉ ᏧᏂᎸᏃᏘᏍᎩ , ᎠᎴ ᎾᏍᏉ ᏧᏂᎾᏫᏍᎩ ; ᏚᏅᏩᏁᏃ .

(src)="b.MAT.4.25.1"> ከገሊላም ከአሥሩ ከተማም ከኢየሩሳሌምም ከይሁዳም ከዮርዳኖስም ማዶ ብዙ ሕዝብ ተከተሉት ።
(trg)="b.MAT.4.25.1"> ᎤᏂᏣᏘᏃ ᏴᏫ ᎬᏩᏍᏓᏩᏛᏎᎢ ᏅᏓᏳᏂᎶᏒᎯ ᎨᎵᎵ , ᎠᏍᎪᎯᏃ-ᎦᏚᎩᏱ , ᎠᎴ ᏥᎷᏏᎵᎻ , ᎠᎴ ᏧᏗᏱ , ᎠᎴ ᏦᏓᏂ ᏍᎪᏂᏗᏢ .

(src)="b.MAT.5.1.1"> ሕዝቡንም አይቶ ወደ ተራራ ወጣ ፤ በተቀመጠም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ወደ እርሱ ቀረቡ ፤
(trg)="b.MAT.5.1.1"> ᎤᏂᏣᏘᏃ ᏫᏚᎪᎲ ᎤᏌᎯᎸ ᎤᎿᎷᏎᎢ , ᎤᏪᏅᏃ ᎬᏩᏍᏓᏩᏗᏙᎯ ᎬᏩᎷᏤᎴᎢ .

(src)="b.MAT.5.2.1"> አፉንም ከፍቶ አስተማራቸው እንዲህም አለ ።
(trg)="b.MAT.5.2.1"> ᎠᎰᎵᏃ ᎤᏍᏚᎢᏒ ᏚᏪᏲᏁ ᎯᎠ ᏄᏪᏎᎢ ;

(src)="b.MAT.5.3.1"> በመንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው ፥ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና ።
(trg)="b.MAT.5.3.1"> ᎣᏏᏳ ᎢᏳᎾᎵᏍᏓᏁᏗ ᎤᏲ ᎢᏳᎾᏛᎿᏕᎩ ᏚᎾᏓᏅᏛᎢ ; ᎤᎾᏤᎵᏰᏃ ᎦᎸᎳᏗ ᎡᎯ ᎤᎬᏫᏳᎯ ᎨᏒᎢ .

(src)="b.MAT.5.4.1"> የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው ፥ መፅናናትን ያገኛሉና ።
(trg)="b.MAT.5.4.1"> ᎣᏏᏳ ᎢᏳᎾᎵᏍᏓᏁᏗ ᎤᏲ ᎤᎾᏓᏅᏔᏩᏕᎩ , ᏛᎨᏥᏄᏬᎯᏍᏔᏂᏰᏃ .

(src)="b.MAT.5.5.1"> የዋሆች ብፁዓን ናቸው ፥ ምድርን ይወርሳሉና ።
(trg)="b.MAT.5.5.1"> ᎣᏏᏳ ᎢᏳᎾᎵᏍᏓᏁᏗ ᎤᎾᏓᏅᏘ , ᎦᏙᎯᏰᏃ ᎤᎾᏤᎵ ᎢᏳᎵᏍᏙᏗ .

(src)="b.MAT.5.6.1"> ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው ፥ ይጠግባሉና ።
(trg)="b.MAT.5.6.1"> ᎣᏏᏳ ᎢᏳᎾᎵᏍᏓᏁᏗ ᎤᏂᏲᏏᏍᎩ ᎠᎴ ᎤᏂᏔᏕᎩᏍᎩ ᎤᎾᏓᏅᏘ ᎢᏳᎾᎵᏍᏙᏗᏱ ; ᏛᎨᏥᎧᎵᎵᏰᏃ .

(src)="b.MAT.5.7.1"> የሚምሩ ብፁዓን ናቸው ፥ ይማራሉና ።
(trg)="b.MAT.5.7.1"> ᎣᏏᏳ ᎢᏳᎾᎵᏍᏓᏁᏗ ᎤᎾᏓᏙᎵᏣᏘ , ᏛᎨᏥᏙᎵᏥᏰᏃ .

(src)="b.MAT.5.8.1"> ልበ ንጹሖች ብፁዓን ናቸው ፥ እግዚአብሔርን ያዩታልና ።
(trg)="b.MAT.5.8.1"> ᎣᏏᏳ ᎢᏳᎾᎵᏍᏓᏁᏗ ᏧᏓᏅᎦᎸᏛ ᏧᏂᎾᏫ , ᎤᏁᎳᏅᎯᏰᏃ ᎤᏂᎪᏩᏛᏗ ;

(src)="b.MAT.5.9.1"> የሚያስተራርቁ ብፁዓን ናቸው ፥ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና ።
(trg)="b.MAT.5.9.1"> ᎣᏏᏳ ᎢᏳᎾᎵᏍᏓᏁᏗ ᎠᏃᎯᏍᏗᏍᎩ , ᎤᏁᎳᏅᎯᏰᏃ ᏧᏪᏥ ᏛᎨᎪᏎᎵ .

(src)="b.MAT.5.10.1"> ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው ፥ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና ።
(trg)="b.MAT.5.10.1"> ᎣᏏᏳ ᎢᏳᎾᎵᏍᏓᏁᏗ ᎤᏲ ᎢᎨᎬᎾᏕᎩ ᏚᏳᎪᏛ ᎨᏒ ᎤᏂᏍᏛᏗᏍᎩ , ᎤᎾᏤᎵᏰᏃ ᎦᎸᎳᏗ ᎡᎯ ᎤᎬᏫᏳᎯ ᎨᏒᎢ .

(src)="b.MAT.5.11.1"> ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ ።
(trg)="b.MAT.5.11.1"> ᎣᏏᏳ ᎢᏣᎵᏍᏓᏁᏗ ᎢᏳᏃ ᏴᏫ ᎤᏐᏅ ᏂᎨᏥᏪᏎᎮᏍᏗ ᎠᎴ ᎤᏲ ᏂᎨᏨᏁᎮᏍᏗ , ᎠᎴ ᏂᎦᎥ ᏧᏓᎴᏅᏛ ᎤᏐᏅ ᎦᏰᎪᎩ ᎨᏥᏃᎮᏍᎨᏍᏗ ᎠᏴ ᎨᏒ ᎢᏥᏍᏛᏗᏍᎨᏍᏗ .

(src)="b.MAT.5.12.1"> ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ ፥ ሐሴትም አድርጉ ፤ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያትን እንዲሁ አሳድደዋቸዋልና ።
(trg)="b.MAT.5.12.1"> ᎢᏣᎵᎮᎵᎨᏍᏗ ᎠᎴ ᎤᏣᏔᏅᎯ ᎣᏍᏛ ᎢᏣᏓᏅᏖᏍᏗ , ᎤᏣᏘᏰᏃ ᎡᏣᎫᏴᎡᏗ ᎦᎸᎳᏗ ; ᎾᏍᎩᏯᏰᏃ ᎤᏥ ᏂᏚᏅᏁᎸᎩ ᎠᎾᏙᎴᎰᏍᎩ ᎢᎬᏱ ᏥᏂᎨᏤᏅᎡᎸ .

(src)="b.MAT.5.13.1"> እናንተ የምድር ጨው ናችሁ ፤ ጨው አልጫ ቢሆን ግን በምን ይጣፍጣል ? ወደ ውጭ ተጥሎ በሰው ከመረገጥ በቀር ወደ ፊት ለምንም አይጠቅምም ።
(trg)="b.MAT.5.13.1"> ᏂᎯ ᎠᎹ ᎡᎶᎯ ᎤᏤᎵᎦ ; ᎢᏳᏍᎩᏂ ᎠᎹ ᏳᏥᏍᎪᎸ ᎦᏙ ᏱᎦᎵᏍᏙᏓ ᎠᎹ ᏯᏙᏢᎾ ; ᎥᏝ ᎿᏉ ᎪᎱᏍᏗ ᎬᏙᏗ ᏱᎦᎩ , ᎠᏗᏅᏗᏉ ᎤᏩᏒ , ᎠᎴ ᏴᏫᏉ ᎤᎾᎳᏍᏓᎡᏗ .

(src)="b.MAT.5.14.1"> እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም ።
(trg)="b.MAT.5.14.1"> ᏂᎯ ᎢᎦ ᎢᏣᏘᏍᏗᏍᎩ ᎡᎶᎯ . ᎦᏚᎲ ᎤᏌᎯᎸ ᏥᎦᎧᎰᎢ ᎥᏝ ᏰᎵ ᏴᎦᏰᎬᏍᎦᎸᎦ .

(src)="b.MAT.5.15.1"> መብራትንም አብርተው ከዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል ።
(trg)="b.MAT.5.15.1"> ᎥᏝ ᎠᎴ ᏴᏫ ᎠᏂᏨᏍᏛᎦ ᎠᏨᏍᏙᏗ ᎠᏟᎶᏍᏗ ᏯᏄᏢᏗᏍᎪᎢ , ᎦᎪᏗᏱᏍᎩᏂ ᎠᏂᎧᎲᏍᎪᎢ , ᎢᎦᏃ ᎤᎾᏘᏍᏓᏁᎰ ᏂᎦᏛ ᎦᎵᏦᏕ ᎠᏂᏯᎢ .

(src)="b.MAT.5.16.1"> መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ ።
(trg)="b.MAT.5.16.1"> ᎢᎦ ᎢᏣᏘᏍᏗᏍᎬ ᏚᏂᎸᏌᏓᏕᎮᏍᏗ ᏴᏫ , ᎾᏍᎩᏃ ᎣᏍᏛ ᏕᏥᎸᏫᏍᏓᏁᎲ ᎠᏂᎪᏩᏘᏍᎨᏍᏗ , ᎠᎴ ᎠᏂᎸᏉᏗᏍᎨᏍᏗ ᎢᏥᏙᏓ ᎦᎸᎳᏗ ᎡᎯ .

(src)="b.MAT.5.17.1"> እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ ፤ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም ።
(trg)="b.MAT.5.17.1"> ᏞᏍᏗ ᏗᎧᎿᏩᏛᏍᏗ ᎠᎴ ᎠᎾᏙᎴᎰᏍᎩ ᏚᏲᏍᏔᏂᎸ ᏱᏍᎩᏰᎵᏎᎮᏍᏗ ; ᎥᏝᏍᎩᏂ ᏱᏓᎩᏲᏍᏔᏂᎸ , ᏓᎩᎧᎵᎵᎸᏍᎩᏂ .