# am/sadiq.xml.gz
# ko/korean.xml.gz
(src)="s1.1"> በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው ፡ ፡
(trg)="s1.1"> 자비로우시고 자애로우신 하나님의 이름으로
(src)="s1.2"> ምስጋና ለአላህ ይገባው የዓለማት ጌታ ለኾነው ፤
(trg)="s1.2"> 온 우주의 주님이신 하나님께찬미를 드리나이다
(src)="s1.3"> እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ
(trg)="s1.3"> 그분은 자애로우시고 자비로 우시며
(src)="s1.4"> የፍርዱ ቀን ባለቤት ለኾነው ፡ ፡
(trg)="s1.4"> 심판의 날을 주관하시도다
(src)="s1.5"> አንተን ብቻ እንግገዛለን ፤ አንተንም ብቻ እርዳታን እንለምናለን ፡ ፡
(trg)="s1.5"> 우리는 당신만을 경배하오며 당신에게만 구원을 비노니
(src)="s1.6"> ቀጥተኛውን መንገድ ምራን ፡ ፡
(trg)="s1.6"> 저희들을 올바른 길로 인도하여 주시옵소서
(src)="s1.7"> የእነዚያን በነርሱ ላይ በጎ የዋልክላቸውን በነሱ ላይ ያልተቆጣህባቸውንና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ ( ምራን ፤ በሉ ) ፡ ፡
(trg)="s1.7"> 그 길은 당신께서 축복을 내리신 길이며 노여움을 받은 자나방황하는 자들이 걷지않는 가장 올바른 길이옵니다
(src)="s2.1"> አ.ለ.መ
(trg)="s2.1"> 알리프 람 밈
(src)="s2.2"> ይህ መጽሐፍ ( ከአላህ ለመኾኑ ) ጥርጥር የለበትም ፤ ለፈራህያን መሪ ነው ፡ ፡
(trg)="s2.2"> 의심할 바 없는 이 성서는 하나님을 공경하는 자들의 이정 표요
(src)="s2.3"> ለነዚያ በሩቁ ነገር የሚያምኑ ሶላትንም ደንቡን ጠብቀው የሚሰግዱ ከሰጠናቸውም ሲሳይ የሚቸሩ ለኾኑት ፤
(trg)="s2.3"> 보이지 않는 하나님의 영역을믿고 예배를 드리며 그들에게 베 풀어 준 양식을 선용하는 사람들 의 이정표이며
(src)="s2.4"> ለእነዚያም ወደ አንተ በተወረደውና ከአንተ በፊትም በተወረደው የሚያምኑ በመጨረሻይቱም ( ዓለም ) እነርሱ የሚያረጋግጡ ለኾኑት ( መሪ ነው ) ፡ ፡
(trg)="s2.4"> 그대에게 계시된 것과 그 이 전에 계시된 것과 또한 내세를 믿는 사람들의 이정표이며
(src)="s2.5"> እነዚያ ከጌታቸው በመመራት ላይ ናቸው ፤ እነዚያም እነሱ ፍላጎታቸውን ያገኙ ናቸው ፡ ፡
(trg)="s2.5"> 그들이 바로 주님의 안내를 받아 영화를 누릴 사람들이라
(src)="s2.6"> እነዚያ የካዱት ( ሰዎች ) ብታስፈራራቸውም ባታስፈራራቸውም በነርሱ ላይ እኩል ነው ፤ አያምኑም ፡ ፡
(trg)="s2.6"> 믿음을 부정하는 사람들은 그대가 그들에게 경고하던 또는 경고하지 아니하던 믿으려 하지 아니하매
(src)="s2.7"> አላህ በልቦቻቸው ላይ በመስሚያቸውም ላይ አትሞባቸዋል ፤ በዓይኖቻቸውም ላይ መሸፈኛ አልለ ፤ ለነሱም ታላቅ ቅጣት አላቸው ፡ ፡
(trg)="s2.7"> 하나님께서 그들에게 벌을 내리사 그들의 마음을 봉하고 그들 의 귀를 붕하고 그들의 눈을 봉 하여 버릴 것이라
(src)="s2.8"> ከሰዎችም « በአላህና በመጨረሻው ቀን አምነናል » የሚሉ አልሉ ፤ እነርሱም አማኞች አይደሉም ፡ ፡
(trg)="s2.8"> 사람들 중에는 하나님과 내세를 믿는척 말하는 무리가 있으나 실로 그들은 신앙인들이 아니거늘
(src)="s2.9"> አላህንና እነዚያን ያመኑትን ( ሰዎች ) ያታልላሉ ፤ የማያውቁ ሲኾኑ ነፍሶቻቸውን እንጅ ሌላን አያታልሉም ፡ ፡
(trg)="s2.9"> 믿는 척 하나님을 속이는 것 은 스스로를 배반하는 것과 같으 나 그들이 알지 못할 뿐이라
(src)="s2.10"> በልቦቻቸው ውስጥ ( የንፍቅና ) በሽታ አለባቸው ፡ ፡ አላህም በሽታን ጨመረባቸው ፡ ፡ ለነርሱም ይዋሹ በነበሩት ምክንያት አሳማሚ ቅጣት አላቸው ፡ ፡
(trg)="s2.10"> 그들 마음에는 병이 있나니하나님께서 그 병을 더하게 하시 매 그들은 고통스러운 벌을 받을 것이라 이는 고들이 스스로를 배 반했기 때문이라
(src)="s2.11"> ለነርሱም « በምድር ላይ አታበላሹ » በተባሉ ጊዜ « እኛ አሳማሪዎች ብቻ ነን » ይላሉ ፡ ፡
(trg)="s2.11"> 이 세상에서 해악을 퍼뜨리지 말라는 말씀이 있었을 때 그들은 평화를 심는 사람들이라 말하 더라
(src)="s2.12"> ንቁ እነርሱ አጥፊዎቹ እነሱው ናቸው ፤ ግን አያውቁም ፡ ፡
(trg)="s2.12"> 실로 그들은 해악을 퍼뜨리면서도 깨닫지 못하노라
(src)="s2.13"> ለነሱም « ሰዎቹ እንዳመኑ እመኑ » በተባሉ ጊዜ « ቂሎቹ እንዳመኑ እናምናለን ? » ይላሉ ፡ ፡ አዋጅ ንቁ እነርሱ ቂሎቹ እነርሱው ናቸው ፤ ግን አያውቁም ፡ ፡
(trg)="s2.13"> 그 사람들이 믿는 것처럼 믿으라 그들에게 말씀이 있었을 때 어리석은 자들이 믿는 것처럼 믿으란 말이뇨 라고 그들은 대답 하도다 보라 실로 그들이 어리석 은 자들이면서 그들은 깨닫지 못 하노라
(src)="s2.14"> እነዚያንም ያመኑትን በተገናኙ ጊዜ « አምነናል » ይላሉ ፡ ፡ ወደ ሰይጣኖቻቸውም ባገለሉ ጊዜ « እኛ ከናንተ ጋር ነን ፤ እኛ ( በነሱ ) ተሳላቂዎች ብቻ ነን » ይላሉ ፡ ፡
(trg)="s2.14"> 그들이 믿는 사람들을 만났을 때는 저회들도 믿음이 있나이 다 라고 말하고 사탄과 함께 있을때는 저희는 당신과 함께 있나니 실로 우리는 조롱을 했을 뿐입니 다 라고 말하더라
(src)="s2.15"> አላህ በነሱ ይሳለቅባቸዋል ፤ በጥመታቸውም ውስጥ የሚዋልሉ ሲኾኑ ያዘገያቸዋል ፡ ፡
(trg)="s2.15"> 하나님이 그들을 조롱하사 그들을 암흑속에서 버리시니 그들은 장님처럼 방황하노라
(src)="s2.16"> እነዚህ እነዚያ ስህተትን በቅንነት የገዙ ናቸው ፡ ፡ ንግዳቸውም አላተረፈችም ፤ ቀጥተኞችም አልኾኑም ፡ ፡
(trg)="s2.16"> 그들은 진실을 팔고 허위를사니 그들의 장사가 홍할리 없으 며 인도받지 못하리라
(src)="s2.17"> ( በንፍቅና ) ምሳሌያቸው እንደዚያ እሳትን እንዳነደደ ሰው በዙሪያው ያለውን ሁሉ ባበራች ጊዜም አላህ ብርሃናቸውን እንደወሰደባቸው በጨለማዎችም ውስጥ የማያዩ ኾነው እንደተዋቸው ( ሰዎች ) ብጤ ነው ፡ ፡
(trg)="s2.17"> 그들을 비유하사 그들이 불을 켜 놓았으나 하나님께서 그들 주변의 빛을 거두어 가시고 그들 을 암흑속에 버리나니 그들은 보 지도 못하고
(src)="s2.18"> ( እነሱ ) ደንቆሮዎች ፣ ዲዳዎች ፣ ዕውሮች ናቸው ፤ ስለዚህ እነርሱ አይመለሱም ፡ ፡
(trg)="s2.18"> 귀머거리 벙어리 장님이 되어 돌아오지 못하노라
(src)="s2.19"> ወይም ( ምሳሌያቸው ) ከሰማይ እንደ ወረደ ዝናም ( ባለቤቶች ) ነው ፤ በርሱ ( በደመናው ) ውስጥ ጨለማዎች ፣ ነጎድጓድም ፣ ብልጭታም ያሉበት ሲኾን ከመብረቆቹ ሞትን ለመፍራት ጣቶቻቸውን በጆሮቻቸው ውስጥ እንደሚያደርጉ ብጤ ነው ፡ ፡ አላህም ከሓዲዎችን ከባቢ ነው ፡ ፡
(trg)="s2.19"> 그들을 비유하사 하늘에서 폭풍우가 몰아치고 암흑이 되어 천둥과 번개가 진동하니 죽음이 두려워 그들은 귀를 막으매 하나 님께서 이 불신자들을 포위하시노라
(src)="s2.20"> ብልጭታው ዓይኖቻቸውን ሊነጥቅ ይቀርባል ፡ ፡ ለነርሱ ባበራላቸው ቁጥር በርሱ ውስጥ ይኼዳሉ ፡ ፡ በነሱም ላይ ባጨለመ ጊዜ ይቆማሉ ፡ ፡ አላህም በሻ ኖሮ መስሚያቸውንና ማያዎቻቸውን በወሰደ ነበር ፤ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና ፡ ፡
(trg)="s2.20"> 번개가 그들의 시력을 할퀴 어 가니 그들에게 빛을 비출때에 는 걷다가 그들을 암흑으로 덮칠 때는 멈추어 서도다 또한 하나님 의 뜻에 따라 그들의 청각과 시력도 앗아 가시니 실로 하나님은 모든 일에 전지 전능하심이라
(src)="s2.21"> እናንተ ሰዎች ሆይ ! የፈጠራችሁን እነዚያንም ከናንተ በፊት የነበሩትን ( የፈጠረውን ) ጌታችሁን ተገዙ ፤ ( ቅጣትን ) ልትጠነቀቁ ይከጀላልና ፡ ፡
(trg)="s2.21"> 인간들이여 주님을 경배하 라 그분께서 너회들을 창조하셨 고 또 너회 선조들을 창조하셨나 니 경배함으로 말미암아 의로운 사람들 가운데 있게 되리라
(src)="s2.22"> ( እርሱ ) ያ ለናንተ ምድርን ምንጣፍ ሰማይንም ጣራ ያደረገ ነው ፤ ከሰማይም ( ከደመና ) ውሃን ያወረደ በርሱም ከፍሬዎች ለናንተ ሲሳይን ያወጣ ነው ፡ ፡ እናንተም ( ፈጣሪነቱን ) የምታውቁ ስትኾኑ ለአላህ ባላንጣዎችን አታድርጉ ፡ ፡
(trg)="s2.22"> 그대들을 위해 대지를 침상 으로 하늘을 천정으로 두셨도다 하늘로부터는 비를 내리게하여 생 과를 맺게하고 이를 그대들의 양 식으로 내려 주셨노라 하나님께 우상을 비유하지 말가 그대들은 이를 알지 않느뇨
(src)="s2.23"> በባሪያችንም ላይ ካወረድነው በመጠራጠር ውስጥ ብትኾኑ ከብጤው አንዲትን ምዕራፍ አምጡ ፡ ፡ እውነተኞችም እንደኾናችሁ ከአላህ ሌላ መስካሪዎቻችሁን ጥሩ ፡ ፡
(trg)="s2.23"> 만약 너희가 하나님의 종에 게 계시한 것에 관하여 의심 한 다면 그와 같은 말씀의 한 구절이 라도 가져을 것이며 너희들이 사 실이라고 고집한다면 하나님외에 증인들을 대어보라
(src)="s2.24"> ( ይህንን ) ባትሠሩ ፈጽሞም አትሠሩትምና ያችን መቀጣጠያዋ ሰዎችና ድንጋዮች የኾነችውን እሳት ተጠበቁ ፤ ለከሓዲዎች ተደግሳለች ፡ ፡
(trg)="s2.24"> 만일 너희가 그렇게 하지 못하고 또한 그렇게도 할 수 없다 면 지옥을 두려워 하라 그곳에는 인간과 돌들이 불에 이글거리고 있으며 불신자들을 위해 준비된 곳이라
(src)="s2.25"> እነዚያን ያመኑትንና መልካሞችንም የሠሩትን ለነርሱ ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች ያሏቸው መኾኑን አብስራቸው ፡ ፡ ከርሷ ከፍሬ ( ዓይነት ) ሲሳይን በተመገቡ ቁጥር ( ፍሬዎችዋ ስለሚመሳሰሉ ) « ይህ ያ ከአሁን በፊት የተገመብነው ነው » ይላሉ ፡ ፡ እርሱንም ተመሳሳይ ኾኖ ተሰጡት ፡ ፡ ለነሱም በውስጧ ንጹህ የተደረጉ ሚስቶች አሏቸው ፡ ፡ እነሱም በውስጧ ዘውታሪዎች ናቸው ፡ ፡
(trg)="s2.25"> 믿음으로 선을 행하는 이들 에게 기쁜소식을 진하라 그들을 위해 천국이 있고 그 밑에는 강물이 흐르니라 그들에게 일용할 양 식이 주어질 때면 이것은 이전에 도 저희에게 베풀어졌던 것이옵니다 라고 그들은 말하도다 또한 그들에게는 그와 유사한 것들이 주 어지리니 그곳에 순결한 동반자기 있어 그 안에서 영생하리라
(src)="s2.26"> አላህ ማንኛውንም ነገር ትንኝንም ኾነ ( በትንሽነት ወይም በትልቅነት ) ከበላይዋ የኾነንም ምሳሌ ለማድረግ አያፍርም ፡ ፡ እነዚያ ያመኑትማ ፤ እርሱ ( ምሳሌው ) ከጌታቸው ( የተገኘ ) እውነት መኾኑን ያውቃሉ ፡ ፡ እነዚያም የካዱትማ « አላህ በዚህ ምንን ምሳሌ ሻ » ይላሉ ፡ ፡ በርሱ ( በምሳሌው ) ብዙዎችን ያሳስታል በርሱም ብዙዎችን ያቀናል ፡ ፡ በርሱም አመፀኞችን እንጅ ሌላን አያሳስትም ፡ ፡
(trg)="s2.26"> 실로 하나넘께서는 모기나 또는 그 이상의 것으로 비유하길 서슴치 아니하시매 믿는자는 그 비유가 주님으로부터 온 진리임을믿으나 불신자들은 말하기를 하나님은 그 비유를 들어 무엇을 원하느뇨 라고 하니 이에 가로되 그것으로 많은 불신자들을 방황케도 하고 또 많은 믿는자들을 인도하 시노라 실로 하나님은 이단자들만을 방황케 하시니라
(src)="s2.27"> እነዚያ የአላህን ቃል ኪዳን ከአጠበቀባቸው በኋላ የሚያፈርሱ እንዲቀጠልም በርሱ ያዘዘውን ነገር የሚቆርጡ በምድርም ላይ የሚያበላሹ እነዚያ እነርሱ ከሳሪዎቹ ናቸው ፡ ፡
(trg)="s2.27"> 이들은 하나닙의 계율을 어 긴자요 하나님이 명령하여 결합하라 하였으나 거역한 자이며 지상 에서 해악을 퍼뜨리는 사람들이니저들은 스스로를 멸망케 하도다
(src)="s2.28"> ሙታን የነበራችሁ ስትኾኑ ሕያው ያደረጋችሁ ከዚያም የሚገድላችሁ ከዚያም ሕያው የሚያደርጋችሁ ሲኾን ከዚያም ወደርሱ የምትመለሱ ስትኾኑ በአላህ እንዴት ትክዳለችሁ !
(trg)="s2.28"> 생명이 없었던 너희에게 생 명을 부여하사 다시 생명을 앗아 가고 또 부활케하여 그분곁으 로 돌아가게 하시는 하나님을 어 떻게 거역한단 말이뇨
(src)="s2.29"> እርሱ ያ በምድር ያለውን ሁሉ ለእናንተ የፈጠረ ነው ፡ ፡ ከዚያም ወደ ሰማይ አሰበ ፤ ሰባት ሰማያትም አደረጋቸው ፡ ፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው ፡ ፡
(trg)="s2.29"> 또한 그분은 너회들을 위해 삼라만상을 창조하시고 다시 하늘로 승천하시어 일곱천을 형성하신분으로 진실로 그분은 모든 것을 아시노라
(src)="s2.30"> ( ሙሐመድ ሆይ ) ጌታህ ለመላእክት ፡ - « እኔ በምድር ላይ ምትክን አድራጊ ነኝ ፤ » ባለ ጊዜ ( የኾነውን አስታውስ ፤ እነርሱም ) « እኛ ከማመስገን ጋር የምናጠራህ ላንተም የምንቀድስ ስንኾን በርሷ ውስጥ የሚያጠፋንና ደሞችንም የሚያፈስን ታደርጋለህን ? » አሉ ፡ ፡ ( አላህ ) « እኔ የማታውቁትን ነገር አውቃለሁ » አላቸው ፡ ፡
(trg)="s2.30"> 주님께서 천사에게 지상에 대리인을 두리라 하시니 천사들이가로되 이 세상을 해치고 살상을 하려 하십니까 저희들은 당신을 찬미하고 당신을 경배하나이다 이에 하나님이 가라사대 실로 나는 너회들이 알고 있는 모든 것을 다알고 있노라
(src)="s2.31"> አደምንም ስሞችን ሁሏንም አስተማረው ፡ ፡ ከዚያም በመላእክት ላይ ( ተጠሪዎቹን ) አቀረባቸው ፡ ፡ « እውነተኞችም እንደኾናችሁ የነዚህን ( ተጠሪዎች ) ስሞች ንገሩኝ » አላቸው ፡ ፡
(trg)="s2.31"> 아담에게 모든 사물의 이름을 가르쳐 주신 후 천사들 앞에 제시하며 말씀하시길 만일 너회가옳다면 너회가 이것들의 이름을 말해보라하니
(src)="s2.32"> « ጥራት ይገባህ ፤ ከአስተማርከን ነገር በስተቀር ለኛ ዕውቀት የለንም ፡ ፡ አንተ ዐዋቂው ጥበበኛው አንተ ብቻ ነህና » ( አሉ ) ፡ ፡
(trg)="s2.32"> 하나님이여 영광을 받으소서저회는 당신이 가르쳐준 것 외에 는 아무것도 모르나니 실로 당신 은 아심과 지혜로 충만 하심이라
(src)="s2.33"> ፡ - « አደም ሆይ ስሞቻቸውን ንገራቸው » አለው ፡ ፡ ስሞቻቸውን በነገራቸውም ጊዜ « እኔ የሰማያትንና የምድርን ሩቅ ምስጢር ዐውቃለሁ ፤ የምትገልጹትንና ያንንም ትደብቁት የነበራችሁትን ዐውቃለሁ አላልኳችሁምን ? » አላቸው ፡ ፡
(trg)="s2.33"> 하나님이 이르시길 아담아 그들에게 이름들을 일러주라 하 시니 그가 그들에게 그 이름들을 일러주매 그분께서 천사들에게 이 르시길 내가 천지에 있는 보이지 않는 것과 너회가 드러내거나 감 추고 있는 모든 것을 알고 있다고 너희에게 얘기하지 않했느뇨
(src)="s2.34"> ለመላእክትም « ለአደም ስገዱ » ባልን ጊዜ ( አስታውስ ) ፡ ፡ ሁሉም ወዲያውኑ ሰገዱ ፤ ኢብሊስ ( ዲያብሎስ ) ብቻ ሲቀር እምቢ አለ ፤ ኮራም ከከሓዲዎቹም ኾነ ፡ ፡
(trg)="s2.34"> 하나님이 천사들에게 명령 하여 아담에게 엎드려 절하라 하 니 모두가 엎드려 절을 하나 이 블리스만 거절하며 거만을 부렸으 니 그는 불신자들중에 있었노라
(src)="s2.35"> « አደም ሆይ ! አንተ ከነሚስትህ በገነት ተቀመጥ ፤ ከርሷም በፈለጋችሁት ስፍራ በሰፊው ተመገቡ ፤ ግን ይህችን ዛፍ አትቅረቡ ፤ ከበደለኞች ትኾናላችሁና » አልንም ፡ ፡
(trg)="s2.35"> 하나님이 말씀하사 아담아 아 내와 함께 천국에 거주하며 그대 들이 원하는 양식을 먹되 이 나무 에 접근하지 말라 그렇지 않으면 죄지은자 가운데 있게 되니라 .
(src)="s2.36"> ከርሷም ሰይጣን አዳለጣቸው በውስጡም ከነበሩበት ( ድሎት ) አወጣቸው ፡ ፡ « ከፊላችሁም ለከፊሉ ጠላት ሲኾን ውረዱ ፤ ለናንተም በምድር ላይ እስከ ጊዜ ( ሞታችሁ ) ድረስ መርጊያና መጣቀሚያ አላችሁ » አልናቸው ፡ ፡
(trg)="s2.36"> 사탄이 그들을 유혹하여 그 곳으로부터 나가게 하매 하나님이말씀하사 서로가 서로의 적이되어지상에서 얼마 동안 안주하여 살 라 했노라
(src)="s2.37"> አደምም ከጌታው ቃላትን ተቀበለ ፡ ፡ በርሱ ላይም ( ጌታው ጸጸትን በመቀበል ) ተመለሰለት ፤ እነሆ እርሱ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነውና ፡ ፡
(trg)="s2.37"> 이때 아담은 주님으로부터 말씀을 들었으며 하나님은 그를 용서 하였으니 진실로 그분은 관 용과 자비로 충만하심이라
(src)="s2.38"> « ሁላችሁም ኾናችሁ ከርሷ ውረዱ ፡ ፡ ከኔም የኾነ መመሪያ ቢመጣላችሁ ወዲያውኑ መመሪያዬን የተከተለ ሰው በነሱ ላይ ፍርሃት የለባቸውም ፤ እነሱም አያዝኑም » አልናቸው ፡ ፡
(trg)="s2.38"> 하나님이 그들에게 말씀하사모두 세상으로 내려가 살라 복음 을 내려 보낼 것이라 이를 따르는사람은 두려움도 슬픔도 없을 것 이라
(src)="s2.39"> እነዚያም ( በመልክተኞቻችን ) የካዱ በአንቀጾቻችንም ያስተባበሉ እነዚያ የእሳት ጓዶች ናቸው ፡ ፡ እነርሱ በውስጧ ዘውታሪዎች ናቸው ፡ ፡
(trg)="s2.39"> 하나님의 말씀을 불신하고 거역하는 사람은 불지옥의 주인이되어 그 속에서 영원히 기거할 것이라
(src)="s2.40"> የእስራኤል ልጆች ሆይ ! ያችን በናንተ ላይ የለገስኳትን ጸጋዬን አስታውሱ ፡ ፡ በቃል ኪዳኔም ሙሉ ፤ በቃል ኪዳናችሁ እሞላለሁና ፤ እኔንም ብቻ ፍሩ ፡ ፡
(trg)="s2.40"> 이스라엘 자손들이여 내가 너회에게 베푼 은총을 기억하고 나에게 한 약속을 이행하라 내가 너희와의 약속을 이행하리라 그 리고 나만을 두려워 하라
(src)="s2.41"> ከናንተ ጋር ያለውን ( መጽሐፍ ) የሚያረጋግጥ ሆኖ ባወረድኩትም ( ቁርኣን ) እመኑ ፡ ፡ በርሱም የመጀመሪያ ከሓዲ አትሁኑ ፡ ፡ በአንቀጾቼም ጥቂትን ዋጋ አትለውጡ ፡ ፡ እኔንም ብቻ ተጠንቀቁ ፡
(trg)="s2.41"> 내가 계시한 것을 믿고 이전에 내려보낸 계시를 믿으라 이를 불신하는 우두머리가 되지 말것이며 나의 계시를 어떠한 것과도 교환하지 말고 나만을 두려워하라
(src)="s2.42"> እውነቱንም በውሸት አትቀላቅሉ ፡ ፡ እናንተም የምታውቁ ስትሆኑ እውነትን አትደብቁ ፡ ፡
(trg)="s2.42"> 진리를 부정으로 왜곡하지 말고 진리를 숨기지 말라 너회는 알고 있지 않느뇨
(src)="s2.43"> ሶላትንም ደንቡን ጠብቃችሁ ስገዱ ፡ ፡ ዘካንም ( ግዴታ ምጽዋትን ) ስጡ ፡ ፡ ( ለጌታችሁ ) ከአጎንባሾች ጋርም አጎንብሱ ፡ ፡
(trg)="s2.43"> 예배를 드리고 이슬람세를 받칠 것이며 다같이 고개속여 하 나님을 경배하라
(src)="s2.44"> እናንተ መጽሐፉን የምታነቡ ሆናችሁ ሰዎችን በበጎ ሥራ ታዛላችሁን ? ነፍሶቻችሁንም ትረሳላችሁን ? ( የሥራችሁን መጥፎነት ) አታውቁምን ?
(trg)="s2.44"> 선을 행하라 너회 백성들에 게 일렀으되 너회 자신들은 망각 하고 있느뇨 성서를 낭독하면서도모른단 말이뇨
(src)="s2.45"> በመታገስና በሶላትም ተረዱ ፡ ፡ እርሷም ( ሶላት ) በፈሪዎች ላይ እንጅ በሌላው ላይ በእርግጥ ከባድ ናት ፡ ፡
(trg)="s2.45"> 인내와 예배로써 구원하라 실로 그것은 겸손한 마음이 없는 사람에게는 힘든 일이라
(src)="s2.46"> እነዚያ እነርሱ ጌታቸውን የሚገናኙ እነሱም ወደእርሱ ተመላሾች መኾናቸውን የሚያረጋግጡ በኾኑት ( ላይ እንጅ ከባድ ናት ) ፡ ፡
(trg)="s2.46"> 주님을 만날 수 있다고 확신하는 사람은 주님께로 돌아가니라
(src)="s2.47"> የእስራኤል ልጆች ሆይ ! ያችን በናንተ ላይ የለገስኳትን ጸጋዬንና እኔም በዓለማት ላይ ያበለጥኳችሁ ( አባቶቻችሁን በጊዜያቸው ከነበሩት ዓለማት ያበለጥኩዋቸው ) መኾኔን አስታውሱ ፡ ፡
(trg)="s2.47"> 이스라엘 자손들이여 내가 너회들에게 베푼 나의 은총을 기 억하라 내가 그대들을 선택 했노 라
(src)="s2.48"> ( ማንኛዋ ) ነፍስም ከ ( ሌላዋ ) ነፍስ ምንንም የማትመነዳበትን ፣ ከርሷም ምልጃን የማይቀበሉባትን ፣ ከርሷም ቤዛ የማይያዝበትን ፣ እነርሱም የማይረዱበትን ቀን ተጠንቀቁ ፡ ፡
(trg)="s2.48"> 그날을 두려워 하라 그날은 어느 누구도 다른 사람에게 도움 을 주지 못하며 어떤 중재도 수라되지 아니하며 어떠한 보상도 받 을 수 없으니 그들은 어떠한 도움도 받지 못하니라
(src)="s2.49"> ከፈርዖንም ቤተሰቦች ( ከጎሶቹና ከሰራዊቱ ) ብርቱን ቅጣት የሚያቀምሱዋችሁ ወንዶች ልጆቻችሁን የሚያርዱ ሴቶቻችሁንም የሚተው ሲኾኑ ባዳንናችሁ ጊዜ ( የኾነውን አስታውሱ ) ፡ ፡ በዚሃችሁም ከጌታችሁ ታላቅ ፈተና አለበት ፡ ፡
(trg)="s2.49"> 하나님께서 너희를 파라오의압박으로부터 구하였음을 상기하 라 그들은 너희를 구속하고 남성 들을 학살 하였으며 여성들은 그 들을 위해 봉사하도록 하였으니 이것이야말로 주님이 내리신 시련이라
(src)="s2.50"> በናንተም ምክንያት ባሕሩን በከፈልን ጊዜ ( አስታውሱ ) ፡ ፡ ወዲያውም አዳንናችሁ ፡ ፡ የፈርዖንንም ቤተሰቦች እናንተ የምትመለከቱ ኾናችሁ አሰጠምናቸው ፡ ፡
(trg)="s2.50"> 바다를 둘로 쪼개어 너회들 을 구하고 너회들의 안면에서 파 라오족을 익사케 했나니
(src)="s2.51"> ሙሳንም አርባን ሌሊት በቀጠርነው ጊዜ ( የኾነውን አስታውሱ ) ፡ ፡ ከዚያም ከርሱ ( መኼድ ) በኋላ እናንተ በዳዮች ስትኾኑ ወይፈንን ( አምላክ አድርጋችሁ ) ያዛችሁ ፡ ፡
(trg)="s2.51"> 모세에게 사십일방을 명하여은거하게 하였을 때 그대들은 송 아지를 택하여 우상을 숭배하였으 매 너회들은 우매하였노라
(src)="s2.52"> ከዚያም ከዚህ በኋላ እናንተ ታመሰግኑ ዘንድ ከናንተ ምሕረት አደረግን ፡ ፡
(trg)="s2.52"> 그 후에도 하나님은 그대들 을 용서하여 주었나니 이에 감사 하라
(src)="s2.53"> ሙሳንም መጽሐፍንና ( እውነትና ውሸትን ) መለያንም ትመሩ ዘንድ በሰጠነው ጊዜ ( አስታውሱ ) ፡ ፡
(trg)="s2.53"> 하나님께서 모세에게 성서와 식별서를 내렸나니 이것으로 너 회가 인도될 것이라
(src)="s2.54"> ሙሳም ለሕዝቦቹ ፡ - « ሕዝቦቼ ሆይ ! እናንተ ወይፈንን ( አምላክ አድርጋችሁ ) በመያዛችሁ ነፍሶቻችሁን በደላችሁ ፡ ፡ ወደ ፈጣሪያችሁም ተመለሱ ፤ ነፍሶቻችሁንም ግደሉ ፤ ይሃችሁ በፈጣሪያችሁ ዘንድ ለናንተ በላጭ ነው » ባለ ጊዜ ( አስታውስ ) ፡ ፡ በእናንተም ላይ ጸጸትን በመቀበል ተመለሰላችሁ ፡ ፡ እነሆ እርሱ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነውና ፡ ፡
(trg)="s2.54"> 모세가 그의 백성에게 이르 되 백성들이여 송아지를 숭배하 여 자신들을 우롱했노라 주님께 회개하고 속죄하라 주님의 은총이있어 너회들을 용서할 것이라 진 실로 그분은 관용과 자비로 충만 하시니라
(src)="s2.55"> « ሙሳ ሆይ ! አላህን በግልጽ እስከምናይ ድረስ ላንተ በፍጹም አናምንልህም » በላችሁም ጊዜ ( አስታውሱ ) ፡ ፡ እናንተም እየተመለከታችሁ መብረቅ ያዘቻችሁ ፡ ፡
(trg)="s2.55"> 모세야 하나님의 형상을 볼 때까지는 믿을 수 없도다 라고 말한 것을 기억하라 그때 천등과 번개가 그들을 불태워 버렸음을 너 회는 지켜보지 아니했느뇨
(src)="s2.56"> ከዚያም ታመሰግኑ ዘንድ ከሞታችሁ በኋላ አስነሳናችሁ ፡ ፡
(trg)="s2.56"> 그런데도 너회가 죽은 후 내가 너희를 부활시 켰으니 이에 감사하라
(src)="s2.57"> በናንተም ላይ ደመናን አጠለልን ፡ ፡ በናተም ላይ ( እንደ ነጭ ማር ያለ ) መንናን እና ድርጭትን አወረድን ፡ ፡ ከሰጠናችሁም ጣፋጮች « ብሉ ( አልን ) ፡ ፡ » አልበደሉንምም ግን ነፍሶቻቸውን ይበድሉ ነበር ፡ ፡
(trg)="s2.57"> 하나님께서 구름으로 그늘을만들고 만나와 쌀와를 보내며 그 대들에게 준 양식 가운데 좋은 것을 먹으라 했거늘 나를 속이지 못하고 스스로 자신들을 우매하게 하였을 뿐이라
(src)="s2.58"> « ይህችንም ከተማ ግቡ ፡ ፡ ከርሷም በሻችሁት ስፍራ ሰፊን ( ምግብ ) ተመገቡ ፡ ፡ በሩንም ያጎነበሳችሁ ኾናችሁ ግቡ ፤ ( ጥያቄያችን የኃጢአታችን መርገፍ ነው ) በሉም ፡ ፡ ኃጢአቶቻችሁን ለናንተ እንምራለንና ፡ ፡ በጎ ሠሪዎችንም ( ምንዳን ) እንጨምርላቸዋለን » ባልን ጊዜ ( አስታውሱ ) ፡ ፡
(trg)="s2.58"> 하나님이 말한 것을 상기하 라 이 마을로 들어가 그대들이 원 하는 대로 먹되 엎드려 문으로 들 어가 겸손히 회개하라 하나님이 그대들의 죄를 용서하고 선행을 베푸는 사람에게는 보상을 증가할 것이라
(src)="s2.59"> እነዚያም የበደሉት ሰዎች ከዚያ ለነሱ ከተባሉት ሌላ ቃልን ለወጡ ፡ ፡ በነዚያም በበደሉት ላይ ያመጹ በመሆናቸው ምክንያት መቅሠፍትን አወረድንባቸው ፡ ፡
(trg)="s2.59"> 그러나 그 우매한 사람들은 그들에게 계시된 말씀을 변조하였 으니 하나님께서 그 우매한 사람 들에게 하늘로부터 혹사병을 보내 도다 . 이는 그들이 계속 죄를 범했기 때문이라
(src)="s2.60"> ሙሳም ለሕዝቦቹ መጠጥን በፈለገ ጊዜ ( የኾነውን አስታውሱ ) ፡ ፡ « ድንጋዩንም በበትርህ ምታ » አልነው ፡ ፡ ( መታውም ) ከርሱም ዐሥራሁለት ምንጮች ፈለቁ ፡ ፡ ሰዎቹ ሁሉ መጠጫቸውን በእርግጥ ዐወቁ ፡ ፡ « ከአላህ ሲሳይ ብሉ ፤ ጠጡም ፤ አመጠኞችም ኾናችሁ በምድር ላይ አታበላሹ » ( አልናቸው ) ፡ ፡
(trg)="s2.60"> 상기하라 모세가 그의 백성 을 위해 물을 구하매 하나님이 모 세에게 네 지팡이로 그 바위를 때 리라 하니 그곳으로부터 열두개의 샘이 솟아나와 각 부족들은 그들 이 마실곳을 알았도다 하나님이 주신 양식을 먹고 마시되 현세에 서 해악을 퍼뜨리지 말라
(src)="s2.61"> ሙሳ ሆይ ፡ - « በአንድ ( ዓይነት ) ምግብ ላይ በፍጹም አንታገሥም ፤ ስለዚህ ጌታህን ከዚያ ምድር ከምታበቅለው ሁሉ ከቅጠላቅጠል ከዱባዋም ከስንዴዋም ከምስርዋም ከሽንኩርቷም ለኛ ያወጣ ዘንድ ለኛ ለምንልን » ባላችሁም ጊዜ ( የኾነውን አስታውሱ ፡ ፡ ሙሳም ፡ - « ያንን እርሱ ዝቅተኛ የኾነውን በዚያ እርሱ በላጭ በኾነው ነገር ለውጥን ትፈልጋላችሁን ? ወደ ከተማ ውረዱ ፤ ለናንተም የጠየቃችሁት ነገር አላችሁ » አላቸው ፡ ፡ በነርሱም ላይ ውርደትና ድኽነት ተመታባቸው ፡ ፡ ከአላህም በኾነ ቁጣ ተመለሱ ፡ ፡ ይህ እነርሱ በአላህ ታምራቶች ይክዱና ነቢያትንም ያለ ሕግ ይገድሉ ስለነበሩ ነው ፡ ፡ ይህ በማመጻቸውና ወሰን የሚያልፉ በመኾናቸው ነው ፡ ፡
(trg)="s2.61"> 그들이 모세에게 말하기를 모세여 음식 한가지로만 살 수 없 나니 목초와 오이 마늘과 아다스 그리고 양파를 하나님께 구원하여 주소서 모세 가로되 그것들보다 더 좋은것을 주셨는데 너회는 이 하찮은 것과 바꾸려 하느뇨 아무 곳이나 자 보아라 너회가 구한 것을 얻을지니 이에 하나님은 그들 을 보잘 것 없고 처량한 족속으로만들었으며 그들은 하나님의 노여움을 샀도다 . 그들은 하나님의 말씀을 부인하고 예언자들을 무차별살해했으니 이들은 불신자들이라
(src)="s2.62"> እነዚያ ያመኑ እነዚያም ይሁዳውያን የኾኑ ፣ ክርስቲያኖችም ፣ ሳቢያኖችም ( ከእነርሱ ) በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ መልካምንም ሥራ የሠራ ለነርሱ በጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው አላቸው ፡ ፡ በነርሱም ላይ ፍርሃት የለባቸውም ፤ እነሱም አያዝኑም ፡ ፡
(trg)="s2.62"> 꾸란을 믿는 자들이나 구약 을 믿는자들이나 그리스도인과 천사들을 믿는 사비안들이나 하나님과 내세를 믿고 선행을 행하는 자에게는 주님의 보상이 있을 것이 며 그대들에게는 두려움도 슬픔도없을 것이라
(src)="s2.63"> ከበላያችሁም የጡርን ተራራ ያነሳን ኾነን የጠበቀ ቃልኪዳናችሁን በያዝን ጊዜ ( የኾነውን አስታውሱ ) ፡ ፡ « ያንን የሰጠናችሁን በኀይል ያዙ ፤ በውስጡ ያለውንም ነገር ( ከእሳት ) ትጠበቁ ዘንድ አስታውሱ » ( አልን ) ፡ ፡
(trg)="s2.63"> 너회 유대인과 구약성서에 있는대로 약속을 했으며 뚜르산을너회들 위로 을렸노라 너회에게 내려준 것을 확고히 잡을 것이며 그 안의 뜻을 생각하라 의로운 사람들이 될 것이라
(src)="s2.64"> ከዚያም ከዚህ በኋላ ( ኪዳኑን ) ተዋችሁ ፡ ፡ በናንተም ላይ የአላህ ችሮታና እዝነቱ ባልነበረ ኖሮ በእርግጥ ከጠፊዎቹ በኾናችሁ ነበር ፡ ፡
(trg)="s2.64"> 그러나 너회는 이를 볼신했 나니 하나님이 너희에게 은총과 자비를 베풀지 않으셨다면 너희는명망하는 자 중에 있을 것이라
(src)="s2.65"> እነዚያንም ከእናንተ ውስጥ በቅዳሜ ቀን ( ዐሣን በማጥመድ ) ወሰን ያለፉትንና ለነሱ « ወራዳዎች ስትኾኑ ዝንጀሮዎች ኹኑ » ያልናቸውን በእርግጥ ዐወቃችሁ ፡ ፡
(trg)="s2.65"> 너회 가운데 안식일을 위반 한 자들이 있음을 너회가 알고 하나님이 그들에게 이르길 그대들은원숭이가 되어 저주를 받을 것이 라
(src)="s2.66"> ( ቅጣቲቱንም ) ለነዚያ በስተፊትዋ ለነበሩትና ለነዚያም ከበኋላዋ ላሉት ( ሕዝቦች ) መቀጣጫ ለፈራህያንም መገሰጫ አደረግናት ፡ ፡
(trg)="s2.66"> 그리하여 하나님은 그 세대 의 백성과 그들의 후손들에게 벌 을 내렸으며 하나님을 두려워 하 는 사람들에게는 교훈을 주었노라
(src)="s2.67"> ሙሳም ለሕዝቦቹ ፡ - « አላህ ላምን እንድታርዱ ያዛችኋል » ባለ ጊዜ ( አስታወሱ ) ፡ ፡ « መሳለቂያ አድርገህ ትይዘናለህን ? » አሉት ፡ ፡ « ከተሳላቂዎች ከመኾን በአላህ እጠበቃለሁ » አላቸው ፡ ፡
(trg)="s2.67"> 모세가 그의 백성에게 이르 되 하나님께서 너회들에게 명령했노라 암송아지 한 마리를 잡아 바치라고 하니 당신은 우리들을 조 룽하는가 라고 그들이 웅답하더라이때 모세 가로되 주여 이같은 몽매한 자가 되지 않도록하여주소서
(src)="s2.68"> « ለኛ ጌታህን ጠይቅልን ፤ እርሷ ምን እንደኾነች ( ዕድሜዋን ) ያብራራልን » አሉ ፡ ፡ « እርሱ እርሷ ያላረጀች ጥጃም ያልኾነች በዚህ መካከል ልከኛ የኾነች ጊደር ናት ይላችኋል ፤ የታዘዛችሁትንም ሥሩ » አላቸው ፡ ፡
(trg)="s2.68"> 그들이 말하길 그것이 어떤 소인지 당신의 주님께 간청하여 설명하여 달라 하니 가로되 그 소는 늙지도 않고 어리지도 않는 중간의 것이라 너회들은 명받은대로행하라
(src)="s2.69"> « ለኛ ጌታህን ጠይቅልን ፤ መልኳ ምን እንደኾነ ለኛ ይግለጽልን » አሉ ፡ ፡ « እርሱ እርሷ መልኳ ደማቅ ተመልካቾችን የምታስደስት ዳለቻ ላም ናት ይላችኋል » አላቸው ፡ ፡
(trg)="s2.69"> 그것은 또 무슨 색깔인지 당신의 주님께 청하여 설명하여 달 라하니 가로되 그 소는 맑고 노 란색이며 보는이를 감탄케 하노라
(src)="s2.70"> « ለኛ ጌታህን ጠይቅልን ፤ እርሷ ምን እንደኾነች ይግለጽልን ፤ ከብቶች በኛ ላይ ተመሳሰሉብን ፡ ፡ እኛም አላህ የሻ እንደኾነ በእርግጥ ተመሪዎች ነን » አሉ ፡ ፡
(trg)="s2.70"> 그들이 말하길 그것이 어떤 소인지 당신의 주님께 청하여 설 명하여 달라 실로 그 암소들이 우리에게는 닮아보이도다 진실로 우리는 하나님의 뜻이라면 그것을 알게 되리라
(src)="s2.71"> « እርሱ እርሷ ያልተገራች ምድርን ( በማረስ ) የማታስነሳ እርሻንም የማታጠጣ ( ከነውር ) የተጠበቀች ልዩ ምልክት የሌለባት ናት ይላችኋል » አላቸው ፡ ፡ « አሁን በትክክል መጣህ » አሉ ፤ ሊሠሩ ያልተቃረቡም ሲኾኑ አረዷት ፡ ፡
(trg)="s2.71"> 가로되 그 소는 땅을 일구고물을 대도록 길들여지지 아니한 흠이 없는 건전한 것이라 하니 이제 당신은 사실을 설명 하였소 라고 말하며 마지 못하여 그 소를 회생 하였더라
(src)="s2.72"> ነፍስነም በገደላችሁና በርሷም ( ገዳይ ) በተከራከራችሁ ጊዜ ( አስታውሱ ) ፡ ፡ አላህም ትደብቁት የነበራችሁትን ሁሉ ገላጭ ነው ፡ ፡
(trg)="s2.72"> 너회가 한 인간을 살인하고 서 이 사실을 감추려할 때 하나님께서는 너회가 숨긴 것을 들추어 내시니라
(src)="s2.73"> « ( በድኑን ) በከፊሏም ምቱት » አልን ፤ እንደዚሁ አላህ ሙታንን ያስነሳል ፤ ታውቁም ዘንድ ታምራቶችን ያሳያችኋል ፡ ፡
(trg)="s2.73"> 그 소의 일부를 가지고 그 시체를 때리라하여 하나님께서 죽은 자를 소생시켜 그분의 예증 을 그처럼 밝히시니 너회는 이해 하게 되리라
(src)="s2.74"> ከዚያም ከዚህ በኋላ ልቦቻችሁ ደረቁ ፤ እርሷም እንደ ድንጋዮች ወይም በድርቅና ይበልጥ የበረታች ናት ፡ ፡ ከድንጋዮችም ከርሱ ጂረቶች የሚፈሱለት አልለ ፡ ፡ ከነርሱም በእርግጥ የሚሰነጠቅና ከርሱ ውሃ ( ምንጭ ) የሚወጣው አልለ ፡ ፡ ከነርሱም አላህን ከመፍራት የተነሳ ወደ ታች የሚወርድ አልለ ፡ ፡ አላህም ከምትሠሩት ነገር ዘንጊ አይደለም ፡ ፡
(trg)="s2.74"> 그런후에도 너회의 마음은 바위처럼 아니 그보다 단단하게 굳어졌노라 바위가 쪼개져 강이 흐르고 그 강이 갈라져 물이 흘러나오며 하나님이 두려워 바위도 무너지도다 하나님은 그들이 행하는 모든 것을 알고 계시니라
(src)="s2.75"> ( አይሁዶች ) ከነሱ የኾኑ ጭፍሮች የአላህን ቃል የሚሰሙና ከዚያም ከተረዱት በኋላ እነርሱ እያወቁ የሚለውጡት ሲኾኑ ለናንተ ማመናቸውን ትከጅላላችሁን ?
(trg)="s2.75"> 너회들은 그들이 너회와 더 불어 믿음을 같이 하기를 바라느 뇨 그들의 무리가 하나님의 말씀 을 듣고 이해 하면서도 그 말씀을왜곡하도다
(src)="s2.76"> እነዚያንም ያመኑትን ባገኙ ጊዜ « አምነናል » ይላሉ ፡ ፡ ከፊላቸውም ወደ ከፊሉ ባገለለ « ጊዜ አላህ በናንተ ላይ በገለጸላቸሁ ነገር እጌታችሁ ዘንድ በርሱ እንዲከራከሩዋችሁ ትነግሩዋቸዋላችሁን ? አታውቁምን ? » ይላሉ ፡ ፡
(trg)="s2.76"> 보라 그들이 믿는 사람들을 만났을때는 우리도 믿나이다 라고말하고 그들이 각각 만났을때는 하나님 앞에서 증거가 되도록 하 나님이 너회들에게 계시한 것을 그들에게 얘기해야 되느뇨 너회 들은 이해하지 못하는 자들이 아 니더뇨 하더라
(src)="s2.77"> አላህ የሚደብቁትንና የሚገልጹትን የሚያውቅ መኾኑን አያውቁምን ?
(trg)="s2.77"> 그들이 숨기는 것과 말하는 것을 하나님께서 알고 계신다는 것을 그들은 모르고 있단 말이뇨
(src)="s2.78"> ከነሱም መጽሐፉን የማያውቁ መሃይማናን አሉ ፡ ፡ ግን ከንቱ ምኞቶችን ( ይመኛሉ ) ፤ እነርሱም የሚጠራጠሩ እንጂ ሌላ አይደሉም ፡ ፡
(trg)="s2.78"> 그들 중에는 글을 알지못하 여 그 성서를 알지 못하매 단지 추측만을 했을 뿐이라
(src)="s2.79"> ለነዚያም መጽሐፉን በእጆቻቸው ለሚጽፉና ከዚያም በርሱ ጥቂትን ዋጋ ሊገዙበት « ይህ ከአላህ ዘንድ ነው » ለሚሉ ወዮላቸው ፡ ፡ ለነርሱም ከዚያ እጆቻቸው ከጻፉት ወዮላቸው ፡ ፡ ለነሱም ከዚያ ከሚያፈሩት ( ኃጢኣት ) ወዮላቸው ፡ ፡
(trg)="s2.79"> 그들 손으로 그 성서를 써서 이것이 하나님으로부터 온 것이니 값싸게 사소서 라고 말하는 그들 에게 재앙이 있을 것이며 그것을 쓴 그들의 손에도 재앙이 올 것이 며 그로써 금전을 모으는 자들에 게 큰 재앙이 있을 것이라
(src)="s2.80"> « እሳትም የተቆጠሩን ቀኖች እንጂ አትነካንም » አሉ ፡ ፡ « አላህ ዘንድ ቃል ኪዳን ይዛችኋልን ? ( ይህ ከኾነ ) አላህም ኪዳኑን አያፈርስም ፤ በእውነቱ በአላህ ላይ የማታውቁትን ትናገራላችሁ » በላቸው ፡ ፡
(trg)="s2.80"> 그들은 불의 재앙이 몇일간 을 제외하고는 오지 않을 것입니 다 라고 말하니 일러 가로되 하나님께서 그렇게 약속했느뇨 실로 하나님께서는 그분의 약속을 어기지 않으시니 너회는 하나님에 관 해 알지 못하는 것을 말하려 하느뇨
(src)="s2.81"> አይደለም ( ትነካችኋለች ) ፤ መጥፎን ( ክሕደትን ) የሠራ በርሱም ኃጠኣቱ የከበበችው ሰው እነዚያ የእሳት ጓዶች ናቸው ፡ ፡ እነርሱ በውስጧ ዘውታሪዎች ናቸው ፡ ፡
(trg)="s2.81"> 사악을 저지르는 자 죄악이 그를 포섭하니 그는 불지옥의 주 인이 되어 그곳에서 영원히 기거 하리라
(src)="s2.82"> እነዚያም ያመኑት በጎ ሥራዎችንም የሠሩት እነዚያ የገነት ጓዶች ናቸው ፡ ፡ እነርሱ በውስጧ ዘላለም ዘውታሪዎች ናቸው ፡ ፡
(trg)="s2.82"> 그러나 믿음으로 선행을 행 하는자는 천국의 주인이 되어 그 곳에서 영생하리라
(src)="s2.83"> የእስራኤል ልጆችንም ጥብቅ ኪዳን አላህን እንጂ ሌላን አታምልኩ ፤ በወላጆችም በጎን ሥራ ( አድርጉ ) ፤ በዝምድና ባለቤቶችም ፣ በየቲሞችም ( አባት የሌላቸው ልጆች ) በምስኪኖችም ( በጎ ዋሉ ) ፤ ለሰዎችም መልካምን ተናገሩ ፤ ሶላትንም ደንቡን ጠብቃችሁ ስገዱ ፤ ዘካንም ስጡ በማለት በያዝንባቸው ጊዜ ( አስታውሱ ) ፡ ፡ ከዚያም ከናንተ ጥቂቶች ሲቀሩ ሸሻችሁ እናንተም ( ኪዳንን ) የምትተዉ ናችሁ ፡ ፡
(trg)="s2.83"> 이스라엘 백성에게 약속을 하사 하나님 외에는 어떤 것도 경배하지 말며 부모와 친척에게 고아와 불우한 자들에게 자선 을 베풀고 사람에겐 겸손하며 예 배를 드리고 인슬람세를 바치라 했거늘 너희중 소수를 제외하고는외면하며 등을 돌리도다
(src)="s2.84"> ደሞቻችሁን አታፍስሱ ነፍሶቻችሁንም ( ከፊላችሁን ) ከአገሮቻችሁ አታውጡ የምንል ስንኾን የጠበቀ ቃል ኪዳናችሁን በያዝንባችሁ ጊዜ ( አስታውሱ ) ፡ ፡ ከዚያም ( በኪዳኑ ) አረጋገጣችሁ ፤ እናንተም ትመሰክራላችሁ ፡ ፡
(trg)="s2.84"> 하나님이 너희에게 성약을 하사 너회 백성들의 피를 흘려서 도 않되며 백성들의 일부를 너희 주거지로부터 추방해서도 아니된 다 하였거늘 너회는 엄숙히 약속 한 증인들이 아니더뇨
(src)="s2.85"> ከዚያም እናንተ እነዚያ ነፍሶቻችሁን የምትገድሉ ከናንተም የኾኑ ጭፍሮችን በኃጢአትና በመበደል በነርሱ ላይ የምትረዳዱ ስትኾኑ ከአገሮቻቸው የምታወጡ ምርኮኞችም ኾነው ቢመጡዋችሁ የምትበዡ ናችሁ ፡ ፡ እርሱ ( ነገሩ ) እነርሱን ማውጣት በእናንተ ላይ የተከለከለ ነው ፡ ፡ በመጽሐፉ ከፊል ታምናላችሁን ? በከፊሉም ትክዳላችሁን ? ከእናንተም ይህንን የሚሠራ ሰው ቅጣት በቅርቢቱ ሕይወት ውርደት እንጂ ሌላ አይደለም ፡ ፡ በትንሣኤ ቀንም ወደ ብርቱ ቅጣት ይመለሳሉ ፡ ፡ አላህም ከምትሠሩት ሥራ ሁሉ ዘንጊ አይደለም ፡ ፡
(trg)="s2.85"> 그런후에도 서로 살생을 하 고 주거지로부터 추방을 하며 죄 악과 앙심을 조성하고 포로가 될 때는 보석금을 갈취하도다 실로 그들을 추방하는 것은 불법이며 성서의 일부만 믿고 일부를 불신 하는 자 그들을 위한 현세의 보 상은 무엇이겠느뇨 실로 이생에서 치욕이 있을 뿐이며 심판의 날 엄 한 응벌이 있을 것이라 실로 하나 님께서는 너회가 행하는 모든 것 을 알고 계심이라
(src)="s2.86"> እነዚህ እነዚያ ቅርቢቱን ሕይወት በመጨረሻይቱ አገር የገዙ ናቸው ፡ ፡ ከነሱም ቅጣቱ አይቀልላቸውም ፤ እነሱም አይርረዱም ፡ ፡
(trg)="s2.86"> 그들은 내세를 팔아 현세를 사는 자들이니 그들의 죄는 경감 되지 않으며 어떤 도움도 없을 것 이라
(src)="s2.87"> ሙሳንም መጽሐፍን በእርግጥ ሰጠነው ፡ ፡ ከበኋላውም መልክትኞችን አስከታተልን ፡ ፡ የመርየምን ልጅ ዒሳንም ግልጽ ታምራቶችን ሰጠነው ፡ ፡ በቅዱሱ መንፈስም አበረታነው ፡ ፡ ነፍሶቻችሁ በማትወደው ነገር መልክተኛ በመጣላችሁ ቁጥር ( ከመከተል ) ትኮራላችሁን ? ከፊሉን አስተባበላችሁ ፤ ከፊሉንም ትገድላላችሁ ፡ ፡
(trg)="s2.87"> 하나님은 모세에게 성서를 주었고 그를 이어 예언자들을 오 게 하였으며 마리아의 아들 예수 에게 권능를 주어 성령으로그를 보호케 하였노라 너회들이 바라 지 않는 한 선지자가 왔을 때 너 회들은 자태를 부리고 일부는 거 짓을 일삼고 일부는 살인을 행한 다 말이뇨
(src)="s2.88"> « ልቦቻችንም ሽፍኖች ናቸው » አሉ ፤ አይደለም አላህ በክሕደታቸው ምክንያት ረገማቸው ጥቂትንም ብቻ ያምናሉ ፡ ፡
(trg)="s2.88"> 이때 그들은 저희의 마음이 굳었나이다 라고 대답하도다 그러나 하나님께서 그들의 불신함에 저주를 내리시니 그들이 믿지 않 기 때문이라
(src)="s2.89"> ከነሱም ጋር ያለውን ( መጽሐፍ ) አረጋጋጭ የኾነ መጽሐፍ ከአላህ ዘንድ በመጣላቸው ጊዜ ( ከመምጣቱ ) በፊት በነዚያ በካዱት ላይ ይረዱበት የነበሩ ሲኾኑ ያወቁት ነገር በመጣላቸው ጊዜ በርሱ ካዱ ፡ ፡ የአላህም ርግማን በከሓዲዎች ላይ ይኹን ፡ ፡
(trg)="s2.89"> 그들에게 하나님으로부터 성서가 도래하였을 때 이는 이미 확증된 것이거늘 이것은 불신자 들에 대한 승리라 그러나 그들이 알고 있는 그분이 왔을 때 그들은그것을 불신하였나니 이들 불신 자들에 하나님의 저주가 있을 것 이라
(src)="s2.90"> ነፍሶቻቸውን በርሱ የሸጡበት ነገር ከፋ ! ( እርሱም ) አላህ ከባሮቹ በሚሻው ሰው ላይ ከችሮታው ( ራእይን ) ማውረዱን በመመቅኘት አላህ ባወረደው ነገር መካዳቸው ነው ፡ ፡ በቁጣ ላይም ቁጣ ( የተረጋገጠባቸው ሲኾኑ ) ተመለሱ ፡ ፡ ለከሓዲዎችም አዋራጅ ቅጣት አላቸው ፡ ፡
(trg)="s2.90"> 자기의 영혼을 파는 사람과 하나님이 계시한 것을 불신하는 자들에게 하나님이 원하는 그분 의 종에게 그분의 은혜가 내려지 는 것을 시기하는 자들 위에 재앙이 있을 것이라 그들은 분노에 분노를 초래하였으니 불신자들에 게는 수치스러운 징벌이 있을 것 이라
(src)="s2.91"> አላህም ባወረደው ( ሁሉ ) ለእነርሱ « እመኑ » በተባሉ ጊዜ « በኛ ላይ በተወረደው ( መጽሐፍ ብቻ ) እናምናለን » ይላሉ ፡ ፡ ከርሱ ኋላ ባለው ( ቁርአን ) እርሱ ከነሱ ጋር ላለው ( መጽሐፍ ) አረጋጋጭ እውተኛ ሲኾን ይክዳሉ ፡ ፡ « አማኞች ከኾናችሁ ከአሁን በፊት የአላህን ነቢያት ለምን ገደላችሁ ? » በላቸው ፡ ፡
(trg)="s2.91"> 하나님이 내린 계시를 믿으 라 했을 때 우리에게 계시된 것 을 믿나이다 라고 대답하되 그 이후의 것은 그것이 사실임을 확 증하면서도 불신하도다 그들이 믿는 자들이라면 그 이전의 선지 자들을 왜 살해 하였는가 그들에 게 물어보라
(src)="s2.92"> ሙሳም በታምራቶች በእርግጥ መጣላችሁ ፡ ፡ ከዚያም ከበኋላው እናንተ በዳዮች ስትኾኑ ወይፈንን ( አምላክ አድርጋችሁ ) ያዛችሁ ፡ ፡
(trg)="s2.92"> 모세가 예증들을 갖고 너희 에게 왔으나 그가 없는 동안 너 회는 송아지를 숭배했나니 너회는우매한 자들이라
(src)="s2.93"> የጡርንም ጋራ ከበላያችሁ ያነሳን ስንኾን ( በኦሪት ሕግ እንድትሠሩ ) ኪዳናችሁን በያዝን ጊዜ ( አስታውሱ ) ፡ ፡ « የሰጠናችሁን በኀይል ያዙ ፤ ስሙም ፤ » ( አልን ) ፡ ፡ « ሰማን አመጽንም » አሉ ፡ ፡ የወይፈኑንም ውዴታ በክሕደታቸው ምክንያት በልቦቻቸው ውስጥ ተጠጡ ፡ ፡ « አማኞች እንደኾናችሁ እምነታችሁ በርሱ የሚያዛችሁ ነገር ከፋ ! » በላቸው ፡ ፡
(trg)="s2.93"> 하나님이 너희와 성약을 한 것과 너회들 위로 시나이 산을 솟게하고 너회에게 내려준 것을 지 키며 그 율법에 귀를 기울이라 했을때 우리는 들었으나 당신이 우 리에게 명령한 것은 거절하도다 라고 말하니 그들은 자신들의 불 신으로 말미암아 그들의 마음속에암송아지 가루의 물을 마셔야만 했더라 일러가로되 너희가 어떤 믿음을 가졌다 해도 너회의 믿음 에는 저주가 있으리라