# am/sadiq.xml.gz
# es/cortes.xml.gz


(src)="s1.1"> በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው ፡ ፡
(trg)="s1.1"> ¡ En el nombre de Alá , el Compasivo , el Misericordioso !

(src)="s1.2"> ምስጋና ለአላህ ይገባው የዓለማት ጌታ ለኾነው ፤
(trg)="s1.2"> Alabado sea Alá , Señor del universo ,

(src)="s1.3"> እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ
(trg)="s1.3"> el Compasivo , el Misericordioso ,

(src)="s1.4"> የፍርዱ ቀን ባለቤት ለኾነው ፡ ፡
(trg)="s1.4"> Dueño del día del Juicio ,

(src)="s1.5"> አንተን ብቻ እንግገዛለን ፤ አንተንም ብቻ እርዳታን እንለምናለን ፡ ፡
(trg)="s1.5"> A Ti solo servimos y a Ti solo imploramos ayuda .

(src)="s1.6"> ቀጥተኛውን መንገድ ምራን ፡ ፡
(trg)="s1.6"> Dirígenos por la vía recta ,

(src)="s1.7"> የእነዚያን በነርሱ ላይ በጎ የዋልክላቸውን በነሱ ላይ ያልተቆጣህባቸውንና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ ( ምራን ፤ በሉ ) ፡ ፡
(trg)="s1.7"> la vía de los que Tú has agraciado , no de los que han incurrido en la ira , ni de los extraviados .

(src)="s2.1"> አ.ለ.መ
(trg)="s2.1"> ` lm .

(src)="s2.2"> ይህ መጽሐፍ ( ከአላህ ለመኾኑ ) ጥርጥር የለበትም ፤ ለፈራህያን መሪ ነው ፡ ፡
(trg)="s2.2"> Ésta es la Escritura , exenta de dudas , como dirección para los temerosos de Alá ,

(src)="s2.3"> ለነዚያ በሩቁ ነገር የሚያምኑ ሶላትንም ደንቡን ጠብቀው የሚሰግዱ ከሰጠናቸውም ሲሳይ የሚቸሩ ለኾኑት ፤
(trg)="s2.3"> que creen en lo oculto , hacen la azalá y dan limosna de lo que les hemos proveído .

(src)="s2.4"> ለእነዚያም ወደ አንተ በተወረደውና ከአንተ በፊትም በተወረደው የሚያምኑ በመጨረሻይቱም ( ዓለም ) እነርሱ የሚያረጋግጡ ለኾኑት ( መሪ ነው ) ፡ ፡
(trg)="s2.4"> creen en lo que se te ha revelado a ti y antes de ti , y están convencidos de la otra vida .

(src)="s2.5"> እነዚያ ከጌታቸው በመመራት ላይ ናቸው ፤ እነዚያም እነሱ ፍላጎታቸውን ያገኙ ናቸው ፡ ፡
(trg)="s2.5"> Ésos son los dirigidos por su Señor y ésos los que prosperarán .

(src)="s2.6"> እነዚያ የካዱት ( ሰዎች ) ብታስፈራራቸውም ባታስፈራራቸውም በነርሱ ላይ እኩል ነው ፤ አያምኑም ፡ ፡
(trg)="s2.6"> Da lo mismo que adviertas o no a los infieles : no creen .

(src)="s2.7"> አላህ በልቦቻቸው ላይ በመስሚያቸውም ላይ አትሞባቸዋል ፤ በዓይኖቻቸውም ላይ መሸፈኛ አልለ ፤ ለነሱም ታላቅ ቅጣት አላቸው ፡ ፡
(trg)="s2.7"> Alá ha sellado sus corazones y oídos ; una venda cubre sus ojos y tendrán un castigo terrible .

(src)="s2.8"> ከሰዎችም « በአላህና በመጨረሻው ቀን አምነናል » የሚሉ አልሉ ፤ እነርሱም አማኞች አይደሉም ፡ ፡
(trg)="s2.8"> Hay entre los hombres quienes dicen : « Creemos en Alá y en el último Día » , pero no creen .

(src)="s2.9"> አላህንና እነዚያን ያመኑትን ( ሰዎች ) ያታልላሉ ፤ የማያውቁ ሲኾኑ ነፍሶቻቸውን እንጅ ሌላን አያታልሉም ፡ ፡
(trg)="s2.9"> Tratan de engañar a Alá y a los que creen ; pero , sin darse cuenta , sólo se engañan a sí mismos .

(src)="s2.10"> በልቦቻቸው ውስጥ ( የንፍቅና ) በሽታ አለባቸው ፡ ፡ አላህም በሽታን ጨመረባቸው ፡ ፡ ለነርሱም ይዋሹ በነበሩት ምክንያት አሳማሚ ቅጣት አላቸው ፡ ፡
(trg)="s2.10.0"> Sus corazones están enfermos y Alá les ha agravado su enfermedad .
(trg)="s2.10.1"> Tendrán un castigo doloroso por haber mentido .

(src)="s2.11"> ለነርሱም « በምድር ላይ አታበላሹ » በተባሉ ጊዜ « እኛ አሳማሪዎች ብቻ ነን » ይላሉ ፡ ፡
(trg)="s2.11"> Cuando se les dice : « ¡ No corrompáis en la tierra ! » , dicen : « Pero ¡ si somos reformadores ! »

(src)="s2.12"> ንቁ እነርሱ አጥፊዎቹ እነሱው ናቸው ፤ ግን አያውቁም ፡ ፡
(trg)="s2.12.0"> ¡ No son ellos , en realidad , los corruptores ?
(trg)="s2.12.1"> Pero no se dan cuenta .

(src)="s2.13"> ለነሱም « ሰዎቹ እንዳመኑ እመኑ » በተባሉ ጊዜ « ቂሎቹ እንዳመኑ እናምናለን ? » ይላሉ ፡ ፡ አዋጅ ንቁ እነርሱ ቂሎቹ እነርሱው ናቸው ፤ ግን አያውቁም ፡ ፡
(trg)="s2.13.0"> Cuando se les dice : « ¡ Creed como creen los demás ! » , dicen : « ¿ Es que vamos a creer como creen los tontos ? »
(trg)="s2.13.1"> Son ellos los tontos , pero no lo saben .

(src)="s2.14"> እነዚያንም ያመኑትን በተገናኙ ጊዜ « አምነናል » ይላሉ ፡ ፡ ወደ ሰይጣኖቻቸውም ባገለሉ ጊዜ « እኛ ከናንተ ጋር ነን ፤ እኛ ( በነሱ ) ተሳላቂዎች ብቻ ነን » ይላሉ ፡ ፡
(trg)="s2.14.0"> Cuando encuentran a quienes creen , dicen : « ¡ Creemos ! »
(trg)="s2.14.1"> Pero , cuando están a solas con sus demonios , dicen : « Estamos con vosotros , era sólo una broma » .

(src)="s2.15"> አላህ በነሱ ይሳለቅባቸዋል ፤ በጥመታቸውም ውስጥ የሚዋልሉ ሲኾኑ ያዘገያቸዋል ፡ ፡
(trg)="s2.15"> Alá les devolverá la broma y les dejará que persistan en su rebeldía , errando ciegos .

(src)="s2.16"> እነዚህ እነዚያ ስህተትን በቅንነት የገዙ ናቸው ፡ ፡ ንግዳቸውም አላተረፈችም ፤ ቀጥተኞችም አልኾኑም ፡ ፡
(trg)="s2.16.0"> Ésos son los que han trocado la Dirección por el extravío .
(trg)="s2.16.1"> Por eso , su negocio no ha resultado lucrativo y no han sido bien dirigidos .

(src)="s2.17"> ( በንፍቅና ) ምሳሌያቸው እንደዚያ እሳትን እንዳነደደ ሰው በዙሪያው ያለውን ሁሉ ባበራች ጊዜም አላህ ብርሃናቸውን እንደወሰደባቸው በጨለማዎችም ውስጥ የማያዩ ኾነው እንደተዋቸው ( ሰዎች ) ብጤ ነው ፡ ፡
(trg)="s2.17.0"> Son como uno que alumbra un fuego .
(trg)="s2.17.1"> En cuanto éste ilumina lo que le rodea , Alá se les lleva la luz y les deja en tinieblas : no ven .

(src)="s2.18"> ( እነሱ ) ደንቆሮዎች ፣ ዲዳዎች ፣ ዕውሮች ናቸው ፤ ስለዚህ እነርሱ አይመለሱም ፡ ፡
(trg)="s2.18"> Son sordos , mudos , ciegos , no se convierten .

(src)="s2.19"> ወይም ( ምሳሌያቸው ) ከሰማይ እንደ ወረደ ዝናም ( ባለቤቶች ) ነው ፤ በርሱ ( በደመናው ) ውስጥ ጨለማዎች ፣ ነጎድጓድም ፣ ብልጭታም ያሉበት ሲኾን ከመብረቆቹ ሞትን ለመፍራት ጣቶቻቸውን በጆሮቻቸው ውስጥ እንደሚያደርጉ ብጤ ነው ፡ ፡ አላህም ከሓዲዎችን ከባቢ ነው ፡ ፡
(trg)="s2.19.0"> O como si viniera del cielo una nube borrascosa , cargada de tinieblas , truenos y relámpagos .
(trg)="s2.19.1"> Se ponen los dedos en los oídos contra el rayo , por temor a la muerte .

(src)="s2.20"> ብልጭታው ዓይኖቻቸውን ሊነጥቅ ይቀርባል ፡ ፡ ለነርሱ ባበራላቸው ቁጥር በርሱ ውስጥ ይኼዳሉ ፡ ፡ በነሱም ላይ ባጨለመ ጊዜ ይቆማሉ ፡ ፡ አላህም በሻ ኖሮ መስሚያቸውንና ማያዎቻቸውን በወሰደ ነበር ፤ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና ፡ ፡
(trg)="s2.20.1"> Cuando les ilumina , caminan a su luz ; pero , cuando les oscurece , se detienen .
(trg)="s2.20.2"> Si Alá hubiera querido , les habría quitado el oído y la vista .

(src)="s2.21"> እናንተ ሰዎች ሆይ ! የፈጠራችሁን እነዚያንም ከናንተ በፊት የነበሩትን ( የፈጠረውን ) ጌታችሁን ተገዙ ፤ ( ቅጣትን ) ልትጠነቀቁ ይከጀላልና ፡ ፡
(trg)="s2.21.1"> Servid a vuestro Señor , Que os ha creado , a vosotros y a quienes os precedieron .
(trg)="s2.21.2"> Quizás , así , tengáis temor de Él .

(src)="s2.22"> ( እርሱ ) ያ ለናንተ ምድርን ምንጣፍ ሰማይንም ጣራ ያደረገ ነው ፤ ከሰማይም ( ከደመና ) ውሃን ያወረደ በርሱም ከፍሬዎች ለናንተ ሲሳይን ያወጣ ነው ፡ ፡ እናንተም ( ፈጣሪነቱን ) የምታውቁ ስትኾኑ ለአላህ ባላንጣዎችን አታድርጉ ፡ ፡
(trg)="s2.22.0"> Os ha hecho de la tierra lecho y del cielo edificio .
(trg)="s2.22.1"> Ha hecho bajar agua del cielo , mediante la cual ha sacado frutos para sustentaros .

(src)="s2.23"> በባሪያችንም ላይ ካወረድነው በመጠራጠር ውስጥ ብትኾኑ ከብጤው አንዲትን ምዕራፍ አምጡ ፡ ፡ እውነተኞችም እንደኾናችሁ ከአላህ ሌላ መስካሪዎቻችሁን ጥሩ ፡ ፡
(trg)="s2.23"> Si dudáis de lo que hemos revelado a Nuestro siervo , traed una sura semejante y , si es verdad lo que decís , llamad a vuestros testigos en lugar de llamar a Alá .

(src)="s2.24"> ( ይህንን ) ባትሠሩ ፈጽሞም አትሠሩትምና ያችን መቀጣጠያዋ ሰዎችና ድንጋዮች የኾነችውን እሳት ተጠበቁ ፤ ለከሓዲዎች ተደግሳለች ፡ ፡
(trg)="s2.24"> Pero , si no lo hacéis -y nunca podréis hacerlo- , guardaos del fuego cuyo combustible lo constituyen hombres y piedras , y que ha sido preparado para los infieles .

(src)="s2.25"> እነዚያን ያመኑትንና መልካሞችንም የሠሩትን ለነርሱ ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች ያሏቸው መኾኑን አብስራቸው ፡ ፡ ከርሷ ከፍሬ ( ዓይነት ) ሲሳይን በተመገቡ ቁጥር ( ፍሬዎችዋ ስለሚመሳሰሉ ) « ይህ ያ ከአሁን በፊት የተገመብነው ነው » ይላሉ ፡ ፡ እርሱንም ተመሳሳይ ኾኖ ተሰጡት ፡ ፡ ለነሱም በውስጧ ንጹህ የተደረጉ ሚስቶች አሏቸው ፡ ፡ እነሱም በውስጧ ዘውታሪዎች ናቸው ፡ ፡
(trg)="s2.25.0"> Anuncia la buena nueva a quienes creen y obran bien : tendrán jardines por cuyos bajos fluyen arroyos .
(trg)="s2.25.1"> Siempre que se les dé como sustento algún fruto de ellos , dirán : « Esto es igual que lo que se nos ha dado antes » .

(src)="s2.26"> አላህ ማንኛውንም ነገር ትንኝንም ኾነ ( በትንሽነት ወይም በትልቅነት ) ከበላይዋ የኾነንም ምሳሌ ለማድረግ አያፍርም ፡ ፡ እነዚያ ያመኑትማ ፤ እርሱ ( ምሳሌው ) ከጌታቸው ( የተገኘ ) እውነት መኾኑን ያውቃሉ ፡ ፡ እነዚያም የካዱትማ « አላህ በዚህ ምንን ምሳሌ ሻ » ይላሉ ፡ ፡ በርሱ ( በምሳሌው ) ብዙዎችን ያሳስታል በርሱም ብዙዎችን ያቀናል ፡ ፡ በርሱም አመፀኞችን እንጅ ሌላን አያሳስትም ፡ ፡
(trg)="s2.26.1"> Los que creen saben que es la Verdad , que viene de su Señor .
(trg)="s2.26.2"> En cuanto a los que no creen , dicen : « ¿ Qué es lo que se propone Alá con esta parábola ? »

(src)="s2.27"> እነዚያ የአላህን ቃል ኪዳን ከአጠበቀባቸው በኋላ የሚያፈርሱ እንዲቀጠልም በርሱ ያዘዘውን ነገር የሚቆርጡ በምድርም ላይ የሚያበላሹ እነዚያ እነርሱ ከሳሪዎቹ ናቸው ፡ ፡
(trg)="s2.27"> Quienes violan la alianza con Alá después de haberla concluido , cortan los lazos que Alá ha ordenado mantener y corrompen en la tierra , ésos son los que pierden .

(src)="s2.28"> ሙታን የነበራችሁ ስትኾኑ ሕያው ያደረጋችሁ ከዚያም የሚገድላችሁ ከዚያም ሕያው የሚያደርጋችሁ ሲኾን ከዚያም ወደርሱ የምትመለሱ ስትኾኑ በአላህ እንዴት ትክዳለችሁ !
(trg)="s2.28"> ¿ Cómo podéis no creer en Alá , siendo así que os dio la vida cuando aún no existíais , que os hará morir y os volverá a la vida , después de lo cual seréis devueltos a Él ?

(src)="s2.29"> እርሱ ያ በምድር ያለውን ሁሉ ለእናንተ የፈጠረ ነው ፡ ፡ ከዚያም ወደ ሰማይ አሰበ ፤ ሰባት ሰማያትም አደረጋቸው ፡ ፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው ፡ ፡
(trg)="s2.29.0"> Él es Quien creó para vosotros cuanto hay en la tierra .
(trg)="s2.29.1"> Y subió al cielo e hizo de él siete cielos .

(src)="s2.30"> ( ሙሐመድ ሆይ ) ጌታህ ለመላእክት ፡ - « እኔ በምድር ላይ ምትክን አድራጊ ነኝ ፤ » ባለ ጊዜ ( የኾነውን አስታውስ ፤ እነርሱም ) « እኛ ከማመስገን ጋር የምናጠራህ ላንተም የምንቀድስ ስንኾን በርሷ ውስጥ የሚያጠፋንና ደሞችንም የሚያፈስን ታደርጋለህን ? » አሉ ፡ ፡ ( አላህ ) « እኔ የማታውቁትን ነገር አውቃለሁ » አላቸው ፡ ፡
(trg)="s2.30.0"> Y cuando tu Señor dijo a los ángeles : « Voy a poner un sucesor en la tierra » .
(trg)="s2.30.1"> Dijeron : « ¿ Vas a poner en ella a quien corrompa en ella y derrame sangre , siendo así que nosotros celebramos Tu alabanza y proclamamos Tu santidad ? »

(src)="s2.31"> አደምንም ስሞችን ሁሏንም አስተማረው ፡ ፡ ከዚያም በመላእክት ላይ ( ተጠሪዎቹን ) አቀረባቸው ፡ ፡ « እውነተኞችም እንደኾናችሁ የነዚህን ( ተጠሪዎች ) ስሞች ንገሩኝ » አላቸው ፡ ፡
(trg)="s2.31"> Enseñó a Adán los nombres de todos los seres y presentó éstos a los ángeles diciendo : « Informadme de los nombres de éstos , si es verdad lo que decís » .

(src)="s2.32"> « ጥራት ይገባህ ፤ ከአስተማርከን ነገር በስተቀር ለኛ ዕውቀት የለንም ፡ ፡ አንተ ዐዋቂው ጥበበኛው አንተ ብቻ ነህና » ( አሉ ) ፡ ፡
(trg)="s2.32.1"> No sabemos más que lo que Tú nos has enseñado .
(trg)="s2.32.2"> Tú eres , ciertamente , el Omnisciente , el Sabio » .

(src)="s2.33"> ፡ - « አደም ሆይ ስሞቻቸውን ንገራቸው » አለው ፡ ፡ ስሞቻቸውን በነገራቸውም ጊዜ « እኔ የሰማያትንና የምድርን ሩቅ ምስጢር ዐውቃለሁ ፤ የምትገልጹትንና ያንንም ትደብቁት የነበራችሁትን ዐውቃለሁ አላልኳችሁምን ? » አላቸው ፡ ፡
(trg)="s2.33.1"> ¡ Infórmales de sus nombres ! »
(trg)="s2.33.2"> Cuando les informó de sus nombres , dijo : « ¿ No os he dicho que conozco lo oculto de los cielos y de la tierra y que sé lo que mostráis lo que ocultáis ? »

(src)="s2.34"> ለመላእክትም « ለአደም ስገዱ » ባልን ጊዜ ( አስታውስ ) ፡ ፡ ሁሉም ወዲያውኑ ሰገዱ ፤ ኢብሊስ ( ዲያብሎስ ) ብቻ ሲቀር እምቢ አለ ፤ ኮራም ከከሓዲዎቹም ኾነ ፡ ፡
(trg)="s2.34.0"> Y cuando dijimos a los ángeles : « ¡ Prosternaos ante Adán ! » .
(trg)="s2.34.1"> Se prosternaron , excepto Iblis .

(src)="s2.35"> « አደም ሆይ ! አንተ ከነሚስትህ በገነት ተቀመጥ ፤ ከርሷም በፈለጋችሁት ስፍራ በሰፊው ተመገቡ ፤ ግን ይህችን ዛፍ አትቅረቡ ፤ ከበደለኞች ትኾናላችሁና » አልንም ፡ ፡
(trg)="s2.35.1"> ¡ Habita con tu esposa en el Jardín y comed de él cuanto y donde queráis . pero no os acerquéis a este árbol !
(trg)="s2.35.2"> Si no , seréis de los impíos » .

(src)="s2.36"> ከርሷም ሰይጣን አዳለጣቸው በውስጡም ከነበሩበት ( ድሎት ) አወጣቸው ፡ ፡ « ከፊላችሁም ለከፊሉ ጠላት ሲኾን ውረዱ ፤ ለናንተም በምድር ላይ እስከ ጊዜ ( ሞታችሁ ) ድረስ መርጊያና መጣቀሚያ አላችሁ » አልናቸው ፡ ፡
(trg)="s2.36.0"> Pero el Demonio les hizo caer , perdiéndolo , y les sacó del estado en que estaban .
(trg)="s2.36.1"> Y dijimos : « ¡ Descended !

(src)="s2.37"> አደምም ከጌታው ቃላትን ተቀበለ ፡ ፡ በርሱ ላይም ( ጌታው ጸጸትን በመቀበል ) ተመለሰለት ፤ እነሆ እርሱ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነውና ፡ ፡
(trg)="s2.37.0"> Adán recibió palabras de su Señor y Éste se volvió a él .
(trg)="s2.37.1"> Él es el Indulgente , el Misericordioso .

(src)="s2.38"> « ሁላችሁም ኾናችሁ ከርሷ ውረዱ ፡ ፡ ከኔም የኾነ መመሪያ ቢመጣላችሁ ወዲያውኑ መመሪያዬን የተከተለ ሰው በነሱ ላይ ፍርሃት የለባቸውም ፤ እነሱም አያዝኑም » አልናቸው ፡ ፡
(trg)="s2.38.0"> Dijimos : « ¡ Descended todos de él !
(trg)="s2.38.1"> Si . pues , recibís de Mí una dirección , quienes sigan Mi dirección no tendrán que . temer y no estarán tristes .

(src)="s2.39"> እነዚያም ( በመልክተኞቻችን ) የካዱ በአንቀጾቻችንም ያስተባበሉ እነዚያ የእሳት ጓዶች ናቸው ፡ ፡ እነርሱ በውስጧ ዘውታሪዎች ናቸው ፡ ፡
(trg)="s2.39"> Pero quienes no crean y desmientan Nuestros signos , ésos morarán en el Fuego eternamente » .

(src)="s2.40"> የእስራኤል ልጆች ሆይ ! ያችን በናንተ ላይ የለገስኳትን ጸጋዬን አስታውሱ ፡ ፡ በቃል ኪዳኔም ሙሉ ፤ በቃል ኪዳናችሁ እሞላለሁና ፤ እኔንም ብቻ ፍሩ ፡ ፡
(trg)="s2.40.1"> Recordad la gracia que os dispensé y sed fieles a la alianza que conmigo concluisteis .
(trg)="s2.40.2"> Entonces , Yo seré fiel a la que con vosotros concluí .

(src)="s2.41"> ከናንተ ጋር ያለውን ( መጽሐፍ ) የሚያረጋግጥ ሆኖ ባወረድኩትም ( ቁርኣን ) እመኑ ፡ ፡ በርሱም የመጀመሪያ ከሓዲ አትሁኑ ፡ ፡ በአንቀጾቼም ጥቂትን ዋጋ አትለውጡ ፡ ፡ እኔንም ብቻ ተጠንቀቁ ፡
(trg)="s2.41.0"> ¡ Creed en lo que he revelado en confirmación de lo que habéis recibido !
(trg)="s2.41.1"> ¡ No seáis los primeros en no creer en ello , ni malvendáis Mis signos !

(src)="s2.42"> እውነቱንም በውሸት አትቀላቅሉ ፡ ፡ እናንተም የምታውቁ ስትሆኑ እውነትን አትደብቁ ፡ ፡
(trg)="s2.42"> ¡ No disfracéis la Verdad de falsedad , ni ocultéis la Verdad conociéndola !

(src)="s2.43"> ሶላትንም ደንቡን ጠብቃችሁ ስገዱ ፡ ፡ ዘካንም ( ግዴታ ምጽዋትን ) ስጡ ፡ ፡ ( ለጌታችሁ ) ከአጎንባሾች ጋርም አጎንብሱ ፡ ፡
(trg)="s2.43"> ¡ Haced la azalá , dad el azaque e inclinaos con los que se inclinan !

(src)="s2.44"> እናንተ መጽሐፉን የምታነቡ ሆናችሁ ሰዎችን በበጎ ሥራ ታዛላችሁን ? ነፍሶቻችሁንም ትረሳላችሁን ? ( የሥራችሁን መጥፎነት ) አታውቁምን ?
(trg)="s2.44.0"> ¿ Mandáis a los hombres que sean piadosos y os olvidáis de vosotros mismos siendo así que leéis la Escritura ?
(trg)="s2.44.1"> ¿ Es que no tenéis entendimiento ?

(src)="s2.45"> በመታገስና በሶላትም ተረዱ ፡ ፡ እርሷም ( ሶላት ) በፈሪዎች ላይ እንጅ በሌላው ላይ በእርግጥ ከባድ ናት ፡ ፡
(trg)="s2.45.0"> ¡ Buscad ayuda en la paciencia y en la azalá !
(trg)="s2.45.1"> Sí , es algo difícil , pero no para los humildes ,

(src)="s2.46"> እነዚያ እነርሱ ጌታቸውን የሚገናኙ እነሱም ወደእርሱ ተመላሾች መኾናቸውን የሚያረጋግጡ በኾኑት ( ላይ እንጅ ከባድ ናት ) ፡ ፡
(trg)="s2.46"> que cuentan con encontrar a su Señor y volver a Él .

(src)="s2.47"> የእስራኤል ልጆች ሆይ ! ያችን በናንተ ላይ የለገስኳትን ጸጋዬንና እኔም በዓለማት ላይ ያበለጥኳችሁ ( አባቶቻችሁን በጊዜያቸው ከነበሩት ዓለማት ያበለጥኩዋቸው ) መኾኔን አስታውሱ ፡ ፡
(trg)="s2.47.0"> ¡ Hijos de Israel !
(trg)="s2.47.1"> Recordad la gracia que os dispensé y que os distinguí entre todos los pueblos .

(src)="s2.48"> ( ማንኛዋ ) ነፍስም ከ ( ሌላዋ ) ነፍስ ምንንም የማትመነዳበትን ፣ ከርሷም ምልጃን የማይቀበሉባትን ፣ ከርሷም ቤዛ የማይያዝበትን ፣ እነርሱም የማይረዱበትን ቀን ተጠንቀቁ ፡ ፡
(trg)="s2.48"> Temed un día en que nadie pueda satisfacer nada por otro , ni se acepte la intercesión ajena , compensación ni auxilio .

(src)="s2.49"> ከፈርዖንም ቤተሰቦች ( ከጎሶቹና ከሰራዊቱ ) ብርቱን ቅጣት የሚያቀምሱዋችሁ ወንዶች ልጆቻችሁን የሚያርዱ ሴቶቻችሁንም የሚተው ሲኾኑ ባዳንናችሁ ጊዜ ( የኾነውን አስታውሱ ) ፡ ፡ በዚሃችሁም ከጌታችሁ ታላቅ ፈተና አለበት ፡ ፡
(trg)="s2.49.0"> Y cuando os salvamos de las gentes de Faraón , que os sometían a duro castigo , degollando a vuestros hijos varones y dejando con vida a vuestras mujeres .
(trg)="s2.49.1"> Con esto os probó vuestro Señor duramente .

(src)="s2.50"> በናንተም ምክንያት ባሕሩን በከፈልን ጊዜ ( አስታውሱ ) ፡ ፡ ወዲያውም አዳንናችሁ ፡ ፡ የፈርዖንንም ቤተሰቦች እናንተ የምትመለከቱ ኾናችሁ አሰጠምናቸው ፡ ፡
(trg)="s2.50"> Y cuando os separamos las aguas del mar y os salvamos , anegando a las gentes de Faraón en vuestra presencia .

(src)="s2.51"> ሙሳንም አርባን ሌሊት በቀጠርነው ጊዜ ( የኾነውን አስታውሱ ) ፡ ፡ ከዚያም ከርሱ ( መኼድ ) በኋላ እናንተ በዳዮች ስትኾኑ ወይፈንን ( አምላክ አድርጋችሁ ) ያዛችሁ ፡ ፡
(trg)="s2.51.0"> Y cuando nos dimos cita con Moisés durante cuarenta días .
(trg)="s2.51.1"> Luego , cuando se fue , cogisteis el ternero , obrando impíamente .

(src)="s2.52"> ከዚያም ከዚህ በኋላ እናንተ ታመሰግኑ ዘንድ ከናንተ ምሕረት አደረግን ፡ ፡
(trg)="s2.52.0"> Luego , después de eso , os perdonamos .
(trg)="s2.52.1"> Quizás , así , fuerais agradecidos .

(src)="s2.53"> ሙሳንም መጽሐፍንና ( እውነትና ውሸትን ) መለያንም ትመሩ ዘንድ በሰጠነው ጊዜ ( አስታውሱ ) ፡ ፡
(trg)="s2.53.0"> Y cuando dimos a Moisés la Escritura y el Criterio .
(trg)="s2.53.1"> Quizás , así , fuerais bien dirigidos .

(src)="s2.54"> ሙሳም ለሕዝቦቹ ፡ - « ሕዝቦቼ ሆይ ! እናንተ ወይፈንን ( አምላክ አድርጋችሁ ) በመያዛችሁ ነፍሶቻችሁን በደላችሁ ፡ ፡ ወደ ፈጣሪያችሁም ተመለሱ ፤ ነፍሶቻችሁንም ግደሉ ፤ ይሃችሁ በፈጣሪያችሁ ዘንድ ለናንተ በላጭ ነው » ባለ ጊዜ ( አስታውስ ) ፡ ፡ በእናንተም ላይ ጸጸትን በመቀበል ተመለሰላችሁ ፡ ፡ እነሆ እርሱ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነውና ፡ ፡
(trg)="s2.54.1"> Habéis sido injustos con vosotros mismos al coger el ternero .
(trg)="s2.54.2"> ¡ Volveos a vuestro Creador y mataos unos a otros . !

(src)="s2.55"> « ሙሳ ሆይ ! አላህን በግልጽ እስከምናይ ድረስ ላንተ በፍጹም አናምንልህም » በላችሁም ጊዜ ( አስታውሱ ) ፡ ፡ እናንተም እየተመለከታችሁ መብረቅ ያዘቻችሁ ፡ ፡
(trg)="s2.55.1"> No creeremos en ti hasta que veamos a Alá claramente » .
(trg)="s2.55.2"> Y el Rayo se os llevó , viéndolo vosotros venir .

(src)="s2.56"> ከዚያም ታመሰግኑ ዘንድ ከሞታችሁ በኋላ አስነሳናችሁ ፡ ፡
(trg)="s2.56.0"> Luego , os resucitamos después de muertos .
(trg)="s2.56.1"> Quizás , así , fuerais agradecidos .

(src)="s2.57"> በናንተም ላይ ደመናን አጠለልን ፡ ፡ በናተም ላይ ( እንደ ነጭ ማር ያለ ) መንናን እና ድርጭትን አወረድን ፡ ፡ ከሰጠናችሁም ጣፋጮች « ብሉ ( አልን ) ፡ ፡ » አልበደሉንምም ግን ነፍሶቻቸውን ይበድሉ ነበር ፡ ፡
(trg)="s2.57.0"> Hicimos que se os nublara y que descendieran sobre vosotros el maná y las codornices : « ¡ Comed de las cosas buenas de que os hemos proveído ! »
(trg)="s2.57.1"> No fueron injustos con Nosotros , sino que lo fueron consigo mismos .

(src)="s2.58"> « ይህችንም ከተማ ግቡ ፡ ፡ ከርሷም በሻችሁት ስፍራ ሰፊን ( ምግብ ) ተመገቡ ፡ ፡ በሩንም ያጎነበሳችሁ ኾናችሁ ግቡ ፤ ( ጥያቄያችን የኃጢአታችን መርገፍ ነው ) በሉም ፡ ፡ ኃጢአቶቻችሁን ለናንተ እንምራለንና ፡ ፡ በጎ ሠሪዎችንም ( ምንዳን ) እንጨምርላቸዋለን » ባልን ጊዜ ( አስታውሱ ) ፡ ፡
(trg)="s2.58.0"> Y cuando dijimos : « ¡ Entrad en esta ciudad , y comed donde y cuando queráis de lo que en ella haya !
(trg)="s2.58.1"> ¡ Entrad por la puerta prosternándoos y decid '¡Perdón ! ' »

(src)="s2.59"> እነዚያም የበደሉት ሰዎች ከዚያ ለነሱ ከተባሉት ሌላ ቃልን ለወጡ ፡ ፡ በነዚያም በበደሉት ላይ ያመጹ በመሆናቸው ምክንያት መቅሠፍትን አወረድንባቸው ፡ ፡
(trg)="s2.59"> Pero los impíos cambiaron por otras las palabras que se les habían dicho e hicimos bajar contra los impíos un castigo del cielo por haber obrado perversamente .

(src)="s2.60"> ሙሳም ለሕዝቦቹ መጠጥን በፈለገ ጊዜ ( የኾነውን አስታውሱ ) ፡ ፡ « ድንጋዩንም በበትርህ ምታ » አልነው ፡ ፡ ( መታውም ) ከርሱም ዐሥራሁለት ምንጮች ፈለቁ ፡ ፡ ሰዎቹ ሁሉ መጠጫቸውን በእርግጥ ዐወቁ ፡ ፡ « ከአላህ ሲሳይ ብሉ ፤ ጠጡም ፤ አመጠኞችም ኾናችሁ በምድር ላይ አታበላሹ » ( አልናቸው ) ፡ ፡
(trg)="s2.60.3"> Todos sabían de cuál debían beber .
(trg)="s2.60.4"> « ¡ Comed y bebed del sustento de Alá y no obréis mal en la tierra corrompiendo ! »