# amh/WIy88RZuKbdZ.xml.gz
# bi/WIy88RZuKbdZ.xml.gz


(src)="1"> ዜና ርዕዮተ- ዓለማችንን እንዴት አርጎ ነው ሚቀርፀው ? ይሄ የዓለምን አህጉራዊ አቀማመጥ ያሳየናል ይሄ ደሞ ዜና በአሜሪካውያን እይታ ላይ ያለውን ተጽኖ ያሳየናል ይሄ ካርታ -- ( ጭብጨባ ) -- ይህ ካርታ የሚያሳየው በየሴኮንዱ የአሜሪካውያን የዜና አውታሮች ለዜና የሚሰጡት ቦታ ነው በሀገር ሲከፋፈል በ2007 እ . ኤ . አ ፤ ከአንድ ዓመት በፊት ይህ ሰሜን ኮሪያ የኒኩሌር ስራዋን ለማቋረጥ የተስማማችበት ወር ነበር በኢንዶኔስያ ከባድ ጎርፍ ነበር በፓሪስ የዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ድርጅት የሰው ልጅ በአካባቢው ላይ የሚፈጥረውን ተጽኖ የሚያሳይ ጥናት አወጣ አሜሪካ 79 በመቶ የሚሆነውን የዜና ሸፋን ትይዛለች አሜሪካን ብናወጣት ፤ የተቀሩት 21 በመቶዎቹን ስናያቸው ኢራቅን በብዛት እናያታለን ፤ ያ ትልቁ አረንጓዴ ነገር ነው እና ሌሎች ትናንሾቹ የሩስያ ፣ ቻይና እና ህንድ ጥምር ሽፋን ሊደርስ የቻለው አንደ በመቶ የሁሉንም ዜናዎች ብናጤናቸው እና አንድ ዜናን ብናወጣ ዓለም ይህን ትመስላለች ያዜና ምንድን ነው ? የአና ኒኮል ህልፈተ ህይወት ይህ ዜና ከኢራቅ በቀር ሁሉንም አገር አዳርሷል ከዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ድርጅት ጥናት በአስር እጥፍ ሽፋን አግኝቷል እናም ሁኔታው እየቀጠለ ነው እንደምናውቀው ብሪትኒ በጣም እየጨመረች መታለች ታድያ ስለዓለም በብዛት ለምን አንሰማም ? አንደኛው ምክንያት የዜና ድርጅቶች በሌላ አገር ያሏቸውን ቢሮዎች በግማሽ ቀንሰዋል በአንድ ግለሰብ ከሚመራው በናይሮቢ ፣ ኒው ዴልሂ እና ሙምባይ ከሚገኘው የኤ . ቢ . ሲ አነስተኛ ቢሮ በስተቀር በአፍሪካ ፣ ህንድ እና ደቡብ አሜሪካ ምንም ዓይነት የዜና ቢሮዎች አይገኙም ምንም እነኳን ቦታዎቹ ከሁለት ቢልዮን ህዝብ በላይ ቢገኝባቸውም እውነታው ግን ለብሪትኒ ሽፋን መስጠት ወጪ አይጠይቅም ይህ የዓለም ሽፋን ደሞ የባሰ የሚረብሸው ሰዎች ለዜና ብለው የሚሄዱበትን ቦታ ስናይ ነው የአገር ውስጥ ዜና ሰፊ ነው በሚያሳዝን መልኩ ለዓለም ዜና የሚሰጠው ሽፋን 12 በመቶ ብቻ ነው ድረ- ገጾችስ ? ዝነኛ የተባሉት የዜና ድረ- ገጾች ምንም የተሻሉ አይደሉም ባለፈው ዓመት ፒው እና የኮሎምቢያ ጄ ት/ ቤት 14000 ዜናዎችን አጥንተዋል የተገኙትም ከጉግል ዜና የፊት ገጽ ነበር እነሱም ሽፋን የሰጡት ለነዛው 24 ዜናዎች ነበር በተመሳሳይ መልኩ በድረ- ገጾች ይዘት ላይ የተካሄደ ጥናት እንዳሳይው ፤ በአሜሪካውያን ዘጋቢዎች ስለዓለም የሚሰሩት ዜናዎች ከአጃንስ ፕሬስ እና ከሮይተርስ የሚለቀሙ ናቸው እናም ሰዉ ሊረዳው በሚችል መንገድ እንኳን አያስቀምጡትም እና ሁሉንም ስታገናኙት ፤ ለምን የኮሌጅ ተመራቂዎች ብዙ ትምህርት ያላገኙ አሜሪካውያንን ጨምሮ ከሌሎች ተመሳሳይ ሀገራት ከ20 ዓመታት በፊት ሊያቁ የቻሉትን እነሱ ማወቅ የተሳናቸው ፍላጎት ሳይኖረን ቀርቶ መስሏችሁ ከሆነ ተሳስታችኋል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የዓለም ዜና እንከታተላለን የሚሉ አሜሪካውያን ቁጥር 50 በመቶ ደርሷል ዋናው ጥያቄ ግን ይሄን የተሳሳተ ርዕዮተ- ዓለም ለአሜሪካውያን እንመኛለን የዓለም አቀፍ ትስስር እየጨመረ በመጣበት ዘመን ? የተሻለ ማድረግ እንደምንችል አቃለሁ አለማድረጉስ ያዋጣናል ? አመሰግናለሁ !
(trg)="1"> Hao nao ol nius we i kamaot long ol niuspepa mo narafala wei emi stiarem ol lukluk we yumi gat long saed long wol tedei ?
(trg)="2"> Hem nao wol we yumi luk luk long hem .
(trg)="3"> Ol difren graon blong wol i luk olsem ia .