# am/101996331.xml.gz
# lt/101996331.xml.gz


(src)="1"> ክራባትን የፈለሰፈው ማን ነው ?
(trg)="1"> Kas sugalvojo kaklaraištį ?

(src)="2"> በጀርመን የንቁ !
(trg)="2"> GAUTA IŠ ATSIBUSKITE !

(src)="3"> መጽሔት ዘጋቢ እንዳጠናቀረው
(trg)="3"> KORESPONDENTO VOKIETIJOJE

(src)="4"> በመላው ዓለም 600 ሚልዮን የሚያክሉ ሰዎች አዘውትረው ክራባት ያደርጋሉ ።
(trg)="4"> VISAME pasaulyje juos nuolat ryši maždaug 600 milijonų vyrų .

(src)="5"> በጀርመን አገር አንድ ወንድ በአማካይ 20 ክራባቶች ይኖሩታል ።
(trg)="5"> Vokietijoje eilinis žmogus turi apie 20 kaklaraiščių .

(src)="6"> በርካታ ወንዶች ክራባታቸውን ሲያስሩ ትንሽ በስጨት ብለው ‘ ይህን ነገር ያመጣብን ማን ይሆን ? ’
(src)="7"> ይላሉ ።
(trg)="6"> Ne vienas vyras , rišdamasis kaklaraištį , yra kiek susierzinęs klausęs : ‛ Kas gi tai sugalvojo ? ’

(src)="8"> ክራባት የመጣው ከየት ነው ?
(trg)="7"> Iš kur atsirado kaklaraištis ?

(src)="9"> የክራባት “ መገኛ ” የመሆንን ክብር ያገኘችው በቤልጅየም የምትገኘው ስቲንከርከ የተባለች ከተማ ነች ።
(trg)="8"> Į garbę už kaklaraiščio „ išradimą “ pretenduoja Belgijos miestelis Steinkerkė . 1692 metais Anglijos karinės pajėgos netikėtai užpuolė tame miestelyje buvusią Prancūzijos kariuomenę .

(src)="11"> ፍራንክፉርተር አልገማይነ ዞንታግሳይቱንግ የተባለው የጀርመንኛ ጋዜጣ እንዳለው “ [ ፈረንሳውያኑ ] ወታደሮች ልብሳቸውን በአግባቡ ለመልበስ ጊዜ አላገኙም ።
(trg)="9"> Pagal Vokietijos laikraštį Frankfurter Allgemeine Sonntagszeitung , „ [ Prancūzų ] karininkai neturėjo laiko tinkamai apsirengti .

(src)="12"> ቀልጠፍ ብለው የደንብ ልብሳቸው ክፍል የሆነውን መሐረብ መሳይ ጨርቅ ላላ አድርገው አንገታቸው ላይ ካሰሩት በኋላ ጫፉን ወደ ውስጥ ይከቱት ነበር ።
(trg)="10"> Jie greitai surišo savo uniformines kaklajuostes ant kaklo laisvu mazgu , o galus prakišo pro švarko skylutes sagoms .

(src)="13"> እነሆ ፣ የክራባት ልደት ሆነ ። ”
(trg)="11"> Vualia !
(trg)="12"> Štai ir pirmasis kaklaraištis “ .

(src)="14"> ይሁን እንጂ የእነዚህ ወታደሮች አለባበስ የመጀመሪያው አልነበረም ።
(trg)="13"> Tačiau kareivių nauja mada nebuvo visiškai beprecedentė .

(src)="15"> ስለ ክራባት ታሪክ ጥናት ያደረጉ ምሁራን እንደሚሉት የቻይናዊው የአፄ ቻንግ ወታደሮች ( ሺ ሁዋንግ ቲ ) ማዕረጋቸውን የሚያመለክት መሐረብ መሳይ ጨርቅ አንገታቸው ላይ ያስሩ ነበር ።
(trg)="14"> Kaklaraiščių praeities tyrinėtojai pažymi , kad keletą amžių prieš tai kinų imperatoriaus Čeng ( Ših Huang Ti ) kareiviai ryšėjo į skarelę panašų drabužį , apsuktą aplink kaklą , kuris rodė jų rangą .

(src)="16"> ከሁሉ በላይ ዝነኛ የሆነው ግን ለፈረንሳዩ ንጉሥ ለሉዊ አሥራ አራተኛ ይዋጉ የነበሩ ክሮአታውያን ይለብሷቸው የነበሩት የአንገት ልብሶች ናቸው ።
(trg)="15"> Tačiau galbūt pačios žinomiausios buvo kaklajuostės , kurias ryšėjo kroatai , kovoję už Prancūzijos karalių Liudviką XIV .

(src)="17"> በፓሪስ በተደረገ የድል ሰልፍ ላይ ፈረንሳውያን በክሮአታያውያኑ የአንገት ልብሶች በጣም በመማረካቸው ክራባት ብለው ጠሯቸው ።
(trg)="16"> Triumfo parado Paryžiuje metu prancūzus taip sužavėjo kroatų kaklajuostės , kad jie pavadino jas kravatais , nuo žodžio cravate — kroatas , ir patys pradėjo ryšėti kaklajuostes .

(src)="18"> ክራባት ያሉት ክሮአት ለማለት ሲሆን እነሱም የአንገት ልብስ መልበስ ጀመሩ ።
(trg)="17"> „ Nuo to laiko , — rašoma minėtame laikraštyje , — kaklaraiščių mados vis plito , nors kareiviai iš Steinkerkės buvo pirmieji , kurie surišo kaklajuostę mazgu kaip kaklaraištį . “

(src)="20"> በፈረንሳይ አብዮት ወቅት ( 1789 - 99 ) አንድ ሰው የሚከተለው የፖለቲካ ፓርቲ አንገቱ ላይ በሚያስረው ክራባት ቀለም ይታወቅ ነበር ።
(trg)="18"> Prancūzų revoliucijos metu ( 1789 — 1799 ) ant vyro kaklo užrišto „ kroato “ , arba kaklajuostės , spalva parodydavo jo politinę priklausomybę . 19 - ajame amžiuje šį papuošalą „ pastebėjo “ elegantiška Europos visuomenė .

(src)="21"> በ19ኛው መቶ ዘመን አለባበስ የሚያሳምሩ የአውሮፓ ማኅበረሰብ አባሎች “ ከክራባት ጋር መላመድ ጀመሩ ። ”
(trg)="19"> Būtent tuo metu kravatas buvo išaukštintas virš karinės ir politinės arenos ir tapo daugumos vyrų apdaro dalimi .

(src)="22"> ክራባት ከውትድርናና ከፖለቲካ ዓለም ወጥቶ የብዙሐን ወንዶቸ ማጌጫ የሆነው በዚህ ጊዜ ነበር ።
(trg)="20"> Šiandien kaklaraištis yra ne tik priimtas daugelyje viso pasaulio šalių ; tam tikrais atvejais jis netgi privalomas .

(src)="24"> [ በገጽ 29 ላይ የሚገኝ ሥዕል ]
(trg)="21"> [ Iliustracijos šaltinio nuoroda 27 puslapyje ]

(src)="25"> Historic Costume in Pictures / Dover Publications , Inc . , New York
(trg)="22"> Historic Costume in Pictures / Dover Publications , Inc . , New York

# am/101996526.xml.gz
# lt/101996526.xml.gz


(src)="1"> ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎች . . .
(trg)="1"> Jaunimas klausia :

(src)="2"> እንደ ሌሎች ወጣቶች እንድደሰት የማይፈቀድልኝ ለምንድን ነው ?
(trg)="2"> Kodėl kiti jaunuoliai nevaržomai linksminasi ?

(src)="3"> “ እኛ የምንፈልገው ለመደሰት ብቻ ነው ፣ ግን አስቸጋሪ ሆኖብናል ” በማለት 15 ዓመት የሆነው ጄሰን ያማርራል ።
(trg)="3"> „ Mes tik norime pasilinksminti , bet tai nėra taip paprasta “ , — skundėsi penkiolikmetis Džeisonas .

(src)="4"> በተለይ በወጣትነት ዕድሜ ለመደሰት መፈለግ ያለ ነገር ነው ።
(trg)="4"> VISAI normalu norėti pasilinksminti — ypač kai esi jaunas !

(src)="5"> ለብዙ ወጣቶች መደሰት ከመብላትና ከመጠጣት ያላነሰ አስፈላጊነት አለው ።
(trg)="5"> Daugumai jaunuolių linksminimasis yra toks svarbus kaip valgis ar miegas .

(src)="6"> ወጣቶች በእኩዮቻቸውና በመገናኛ ብዙሐን እየተገፋፉ በተለያዩ የመዝናኛ ዓይነቶች ይካፈላሉ ።
(trg)="6"> Skatinami bendraamžių ir masinės informacijos priemonių , jaunuoliai uoliai ieško įvairiausių pramogų .

(src)="7"> አንድ ጥናት እንደሚያመለክተው በአፍላ የጉርምስና ዕድሜ የሚገኙ ወጣቶች ከሚወዷቸው የምሽት ጊዜ ማሳለፊያዎች መካከል ጓደኞቻቸውን መጠየቅ ፣ ቴሌቪዥን መመልከት ፣ ሲኒማ ማየት ፣ ፓርቲ መሄድና መጨፈር የመጀመሪያ ምርጫዎቻቸው ሆነው ተገኝተዋል ።
(trg)="7"> Vienos apklausos duomenimis , lankymasis pas draugus , televizorius , kinas , pobūviai ir šokiai paauglių mėgstamiausių vakaro praleidimo būdų sąraše užėmė pirmąsias vietas .

(src)="8"> በተጨማሪም ማንበብ ፣ የተለያዩ ጨዋታዎች ፣ ስፖርትና ሙዚቃ ማዳመጥም ተወዳጅነት አላቸው ።
(trg)="8"> Skaitymas , žaidimai , sportas bei muzikos klausymasis irgi populiarūs .

(src)="9"> ደስታ የሚያመጡ ስንት ዓይነት እንቅስቃሴዎች እያሉ እንደ ጄሰን ያሉ አንዳንድ ወጣቶች ደስታ እንደቀረባቸው አድርገው ለምን እንደሚያማርሩ ወላጆች ግራ ሊገባቸው ይችላል ።
(trg)="9"> Kadangi galima taip įvairiai linksmintis , suaugusiesiems gali būti sunku suprasti , kodėl kai kurie jaunuoliai , tokie kaip Džeisonas , mano neturį pakankamai pramogų .

(src)="10"> ያም ሆነ ይህ ግን አንዳንድ ክርስቲያን ወጣቶች እንዲህ ብለው ሲያማርሩ ይሰማል ።
(trg)="10"> Bet būtent taip tvirtina kai kurie jaunuoliai krikščionys !

(src)="11"> ኬሲ የተባለች የይሖዋ ምሥክር ወጣት “ የትምህርት ቤት ጓደኞቻችሁ ወደ ፓርቲዎች ሲሄዱና ሌሎች የተለያዩ ነገሮችን ሲያደርጉ ስታዩ ብዙ ነገር እንደቀረባችሁ ይሰማችኋል ” ብላለች ።
(trg)="11"> Jauna Jehovos Liudytoja Keisi pasakė šitaip : „ Tu matai visus savo moksladraugius dalyvaujant vakarėliuose ir darant šį bei tą , o pati tikrai jautiesi palikta nuošaly . “

(src)="12"> ይሁን እንጂ ክርስቲያን ወጣቶች ያሉበት ሁኔታ ይህን ያህል የከፋ ነውን ?
(trg)="12"> Bet ar padėtis tikrai tokia bloga ?

(src)="13"> መጽሐፍ ቅዱስ መደሰት ይከለክላልን ?
(trg)="13"> Ar Biblija draudžia linksmai leisti laiką ?

(src)="14"> በፍጹም አይከለክልም ።
(trg)="14"> Visai priešingai .

(src)="16"> ስለዚህ ንጉሥ ሰሎሞን “ ለሁሉ ዘመን አለው ፣ . . .
(trg)="15"> Biblijoje Jehova vadinamas „ laimingu Dievu “ .

(src)="17"> ለማልቀስ ጊዜ አለው ፣ ለመሳቅም ጊዜ አለው ፤ ዋይ ለማለት ጊዜ አለው ፣ ለመዝፈንም ጊዜ አለው ” ማለቱ ሊያስደንቅ አይገባም ።
(trg)="16"> Todėl tavęs neturėtų stebinti , kad karalius Saliamonas pasakė : „ Visam kam yra savo metas , . . . metas verkti ir metas juoktis , metas raudoti ir metas šokti “ ( Ekleziasto 3 : 1 , 4 ) .

(src)="18"> እዚህ ላይ “ መሳቅ ” ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጥ ቃልና ከዚህ ቃል ጋር ተዛማጅነት ያላቸው ሌሎች ቃላት “ በዓል ማድረግ ፣ ” “ መጫወት ፣ ” “ ስፖርት መሥራት ፣ ” “ ማስደሰት ” እና “ ጥሩ ጊዜ ማሳለፍ ” የሚል ትርጉም አላቸው ። — 2 ሳሙኤል 6 : 21 ፤ ኢዮብ 41 : 5 ፤ መሳፍንት 16 : 25 ፤ ዘጸአት 32 : 6 ፤ ዘፍጥረት 26 : 8
(trg)="17"> Pats hebrajų kalbos žodis , čia verčiamas „ juoktis “ , ir jam giminingi žodžiai taip pat gali reikšti ‛ švęsti ’ , ‛ žaisti ’ , ‛ linksminti ’ ir ‛ smagiai leisti laiką ’ ( 2 Samuelio 6 : 21 , NW ; Jobo 40 : 24 ; Teisėjų 16 : 25 , Biblija , parengė K .

(src)="19"> ጥንት በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን የአምላክ ሕዝቦች ሙዚቃ እንደመጫወት ፣ እንደ መዝፈን ፣ መጨፈር ፣ ጭውውትና የተለያዩ ጨዋታዎችን እንደ መጫወት ባሉ ጤናማ እንቅስቃሴዎች ይካፈሉ ነበር ።
(trg)="18"> Burbulys , redaguota ; Išėjimo 32 : 6 , NW ; Pradžios 26 : 8 , NW ) .
(trg)="19"> Bibliniais laikais Dievo tautos žmonės užsiimdavo daugybe naudingų dalykų , pavyzdžiui , grodavo muzikos instrumentais , dainuodavo , šokdavo , kalbėdavosi ir žaisdavo žaidimus .

(src)="20"> በተጨማሪም ድግስ አዘጋጅተው የሚገባበዙባቸውና የሚደሰቱባቸው የተለዩ ጊዜያት ነበሯቸው ።
(trg)="20"> Jie taip pat turėdavo ypatingų progų puotauti bei džiaugsmingai bendrauti ( Jeremijo 7 : 34 ; 16 : 9 ; 25 : 30 ; Luko 15 : 25 ) .

(src)="21"> ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን በሠርግ ድግስ ላይ ተገኝቶ ነበር ! — ዮሐንስ 2 : 1 - 10
(trg)="21"> Net pats Jėzus Kristus dalyvavo vestuvių iškilmėse !

(src)="22"> ስለዚህ በዘመናችን ያሉ ክርስቲያን ወጣቶች ጤናማ በሆኑ ነገሮች እንዳይደሰቱ አይከለከሉም ።
(trg)="22"> Taigi šiandien krikščioniškam jaunimui nedraudžiama deramai linksmintis .

(src)="23"> እንዲያውም መጽሐፍ ቅዱስ “ አንተ ጎበዝ ፣ በጉብዝናህ ደስ ይበልህ ፣ በጉብዝናህም ወራት ልብህን ደስ ይበለው ” ይላል ።
(trg)="23"> Iš tiesų Biblijoje sakoma : „ Linksminkis , jaunikaiti , savo jaunystėje ir tegul būna linksma tavo širdis tavo jaunystės dienomis . “

(src)="24"> ይሁን እንጂ ሰሎሞን ይህን ከተናገረ በኋላ “ ዳሩ ግን ስለዚህ ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ወደ ፍርድ እንዲያመጣህ እወቅ ” የሚል ማስጠንቀቂያ አስከትሏል ።
(trg)="24"> Vis dėlto Saliamonas toliau perspėja : „ Bet žinok , kad Dievas dėl viso to pašauks tave į teismą “ ( Ekleziasto 11 : 9 ) .

(src)="25"> አዎን ፣ ለምታደርጋቸው ምርጫዎች ሁሉ በአምላክ ዘንድ በኃላፊነት ትጠየቃለህ ።
(trg)="25"> Taip , tu atsakingas Dievui už tai , ką pasirenki .

(src)="26"> ስለዚህ መዝናኛዎችን በሚመለከት “ እንደ ጥበበኞች እንጂ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንዴት እንድትመላለሱ በጥንቃቄ ተጠበቁ ” የሚለውን ምክር መከተል አስፈላጊ ነው ።
(trg)="26"> Todėl tu privalai ‛ rūpestingai žiūrėti , kaip elgiesi : kad nebūtumei tarytum neišmanėlis , bet kaip išmintingas ’ rinkdamasis pramogas .

(src)="27"> ለምን ቢባል ብዙ ወጣቶች በዚህ ረገድ መጥፎ ምርጫ እያደረጉ ነው ።
(trg)="27"> Kodėl ?
(trg)="28"> Daugelis jaunuolių šioje srityje pasirenka ne tai , kas geriausia .

(src)="28"> ደስታ ከቁጥጥር ውጭ በሚሆንበት ጊዜ
(trg)="29"> Kai pramogos tampa nebevaldomos

(src)="29"> በጥንት የመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን የሆነውን እንመልከት ።
(trg)="30"> Apsvarstyk , kas atsitiko kadaise bibliniais laikais .

(src)="30"> አንዳንድ እስራኤላውያን በመዝናኛዎች ረገድ ሚዛናቸውን ስተው ሌሊቱን ሙሉ ሲጨፍሩ ማደር ጀምረው ነበር !
(trg)="31"> Kai kurie izraelitai visiškai prarado pusiausvyrą dėl pramogų ir per naktis keldavo audringus pobūvius !

(src)="31"> ነቢዩ ኢሳይያስ እንዲህ ብሏል : - “ ስካርን ለመከተል በጥዋት ለሚማልዱ ፣ የወይን ጠጅም እስኪያቃጥላቸው እስከ ሌሊት ድረስ ለሚዘገዩ ወዮላቸው !
(trg)="32"> Pranašas Izaijas pasakė : „ Vargas jums , kurie keliatės rytmetį , kad girtuokliautumėt ir gertumėt iki vakarui , kad būtumėt įkaitę nuo vyno !

(src)="32"> መሰንቆና በገና ከበሮና እምቢልታም የወይን ጠጅም በግብዣቸው አለ ። ”
(trg)="33"> Arfa ir kanklės , bubinėlis ir vamzdis , taip pat ir vynas yra jūsų pokyliuose . “

(src)="33"> አንድ ላይ ሆኖ መብላት ፣ መጠጣትና መጨፈር በራሱ ስህተት አይደለም ።
(trg)="34"> Ne , nebuvo bloga susieiti ir vaišintis , klausytis muzikos bei šokti .

(src)="34"> ይሁን እንጂ ኢሳይያስ ስለ እነዚህ ፈንጠዝያ አሳዳጆች “ የእግዚአብሔርን ሥራ ግን አልተመለከቱም ” ብሏል ። — ኢሳይያስ 5 : 11 , 12
(trg)="35"> Bet Izaijas sako šiems puotautojams : „ Jūs neatsižvelgiate į Viešpaties veiksmą “ ( Izaijo 5 : 11 , 12 ) .

(src)="35"> በዘመናችን ያሉ ብዙ ወጣቶችም ይህንኑ የሚመስል ነገር ያደርጋሉ ።
(trg)="36"> Daug jaunuolių šiandieną elgiasi taip pat — jie negalvoja apie Dievą ieškodami pasilinksminimų .

(src)="36"> በሚዝናኑበት ወቅት ስለ አምላክ ፈጽሞ አያስቡም ።
(src)="37"> አንዳንዶች የአምላክን የጽድቅ ሕግጋት በድፍረት በመተላለፍ “ ለደስታ ” ሲሉ ከጋብቻ ውጭ የጾታ ግንኙነት ይፈጽማሉ ፣ የሰው ንብረት ያጠፋሉ ፣ አደንዛዥ ዕፆች ይወስዳሉ እንዲሁም ብዙ ቅጥ የለሽ ተግባራት ይፈጽማሉ ።
(trg)="37"> Kai kurie įžūliai ignoruoja Dievo normas praktikuodami priešvedybinį seksą , įsitraukdami į vandalizmą , vartodami narkotikus ir kitaip neprotingai elgdamiesi dėl „ pramogos “ .

(src)="38"> በሌላ በኩል ደግሞ ወጣቶች ሆን ብለው ክፉ ለማድረግ የማይነሱባቸው ጊዜያት አሉ ።
(trg)="38"> O kitais atvejais jaunuoliai iš tikrųjų nesistengia būti blogi .

(src)="39"> ይሁን እንጂ የልከኝነት ገደባቸውን መጠበቅ ያቅታቸዋል ።
(trg)="39"> Bet jie nesielgia santūriai ir nevengia kraštutinumų ( Patarlių 23 : 20 ; 1 Timotiejui 3 : 11 , Brb red . ) .

(src)="40"> በዚህም ምክንያት የሚያደርጓቸው ነገሮች ከቁጥጥር ውጭ ይሆኑባቸዋል ። — ከ1 ቆሮንቶስ 10 : 6 - 8 ጋር አወዳድር ።
(trg)="40"> Taigi jiems susirinkus linksmai praleisti laiką padėtis gali pasidaryti nevaldoma .
(trg)="41"> ( Palygink 1 Korintiečiams 10 : 6 - 8 . )

(src)="41"> በቅርቡ ንቁ !
(trg)="42"> Neseniai Atsibuskite !

(src)="42"> “ በአሁኑ ጊዜ በዓለማዊ ፓርቲዎች ምን ዓይነት ነገሮች ይደረጋሉ ? ”
(trg)="43"> korespondentas paklausė kai kurių jaunuolių : „ Kas šiandien daroma pasaulietiškuose vakarėliuose ? “

(src)="43"> የሚል ጥያቄ ለአንዳንድ ወጣቶች አቅርቦ ነበር ።
(trg)="44"> Viena paauglė atsakė : „ Vartojami narkotikai , girtaujama .
(trg)="45"> Tikrai taip būna . “

(src)="44"> አንዲት ወጣት ልጃገረድ “ ይጠጣል ፣ አደንዛዥ ዕፆች ይወሰዳሉ ።
(trg)="46"> Jaunuolis Endrius apie kai kuriuos dažnai dalyvaujančius pobūviuose vaikinus iš savo mokyklos pasakė : „ Jie tik ir giriasi , kiek daug išgėrė . “

(src)="45"> እነዚህ ነገሮች በብዛት ይፈጸማሉ ” ብላለች ።
(trg)="47"> Džeisonas pareiškė netgi šitaip : „ Pasaulietiškuose vakarėliuose beveik visada vyksta kažkas blogo . “

(src)="47"> ጄሰን “ መጥፎ ነገር የማይፈጸምበት ዓለማዊ ፓርቲ ኖሮ አያውቅም ” እስከማለት ደርሷል ።
(trg)="48"> Kadangi „ girtavimai “ bei „ orgijos “ smerkiami Biblijoje , dievobaimingi jaunuoliai vengia sambūrių , kuriuose dedasi tokie dalykai .

(src)="49"> ጉዳት የሌላቸው መስለው የሚታዩ መዝናኛዎች እንኳን አደገኞች ሊሆኑ ይችላሉ ።
(trg)="49"> Pavojai gali slypėti netgi iš pažiūros nekenksminguose pasilinksminimuose .

(src)="50"> ለምሳሌ በርካታ የሆኑ የጊዜያችን ፊልሞች እርቃነ ሥጋ የሚያሳዩ ፣ ሩካቤ ሥጋ ሲፈጸም የሚታይባቸውና የሚዘገንኑ የኃይል ድርጊቶች የሚፈጸምባቸው ናቸው ።
(trg)="50"> Pavyzdžiui , daugelyje šiomis dienomis populiariausių filmų rodomas nuogumas , seksas ir pasibjaurėtinas smurtas .

(src)="51"> ከፍተኛ ተወዳጅነት ያተረፉ ዘፈኖች የብልግና ግጥሞች አሏቸው ።
(trg)="51"> Populiariausių dainų žodžiai dažnai esti pornografiniai .

(src)="52"> የሮክ ሙዚቃ ትርዒቶች በአብዛኛው ዕፅ የሚጨስባቸው ፣ ግርግር የሚበዛባቸውና ዓመፅ የሚፈጸምባቸው ቦታዎች ናቸው ።
(trg)="52"> Roko koncertai paprastai būna svaiginimosi narkotikais , visiškos sumaišties ir smurto scenos .

(src)="53"> *
(trg)="53"> *

(src)="54"> ወላጆች አይቻልም በሚሉበት ጊዜ
(trg)="54"> Kai tėvai sako „ ne “

(src)="55"> በዚህ ረገድ ልብ ሊባል የሚገባው መሠረታዊ ሐቅ ምንድን ነው ?
(trg)="55"> Kokia esmė ?

(src)="56"> ክርስቲያን ከሆንክ እኩዮችህ የሚያደርጓቸውን ነገሮች በሙሉ ማድረግ አትችልም ።
(trg)="56"> Jeigu esi krikščionis , tu tiesiog negali daryti viso to , ką daro tavo bendraamžiai .

(src)="57"> ኢየሱስ ተከታዮቹ ‘ የዓለም ክፍል እንደማይሆኑ ’ ተናግሯል ።
(trg)="57"> Juk Jėzus pasakė , kad jo pasekėjai ‛ nėra iš pasaulio ’ , tai yra skiriasi nuo kitų žmonių .

(src)="58"> ይህ ማለት ደግሞ ከሌሎች ሰዎች የተለየን መሆን አለብን ማለት ነው ።
(trg)="58"> Jei tavo tėvai yra dievobaimingi , jie gerai supranta šį faktą .

(src)="59"> ወላጆችህ ፈሪሃ አምላክ ያላቸው ከሆኑ ይህን ሐቅ አሳምረው ያውቃሉ ።
(trg)="59"> Taigi norėdami apsaugoti tave , tėvai kartais gali atkalbinėti nuo ko nors ar griežtai uždrausti ką nors — tai , ką kitiems jaunuoliams leidžiama daryti .

(src)="61"> ይህን መቀበል ሁልጊዜ ቀላል አይሆንም ።
(trg)="60"> Ne visada lengva su tuo sutikti .

(src)="62"> አንዲት ወጣት ልጃገረድ “ ማንም ሰው መደሰት ይፈልጋል !
(trg)="61"> „ Žmonės nori pasilinksminti ! — atkakliai tvirtino viena paauglė . — Mūsų tėvai linksminosi , kai buvo jauni , bet kartais atrodo , tarsi jie norėtų laikyti mus užrakintus . “

(src)="63"> ወላጆቻችንም ቢሆኑ በወጣትነታቸው ይደሰቱ ነበር ።
(trg)="62"> Gali būti nelengva klausyti tėvų patarimo šiais klausimais , net jeigu jūsų požiūriai iš esmės sutampa .

(src)="64"> አሁን ግን እኛ ልጆቻቸው ተዘግተን እንድንቀመጥ የሚፈልጉ ይመስላል ” ብላለች ።
(trg)="63"> Vienas sportiškos išvaizdos jaunuolis — pavadinsime jį Tomu — prisimena : „ Aš norėjau žaisti krepšinį mokyklos komandoje .

(src)="67"> እንድጫወት ይገፋፉኝ የነበሩ ሰዎች በርካታ ስለነበሩ ነገሩ አሳስቦኝ ነበር ።
(trg)="64"> Daug žmonių įkalbinėjo mane žaisti ir tai man kažkaip nedavė ramybės .
(trg)="65"> Bet tada pasikalbėjau su tėvais . “

(src)="68"> በዚህ ጊዜ ወላጆቼን አማከርኩ ” ይላል ።
(trg)="66"> Tomo tėvai nurodė , kuo pavojingos „ blogos draugijos “ , ir priminė , kiek daug laiko atimtų jo sporto užsiėmimai .

(src)="70"> “ ነገሩ በዚህ ቆመ ” በማለት ያሬድ በሐዘን ይናገራል ።
(trg)="67"> „ Štai ir viskas “ , — liūdnai sako Tomas .

(src)="71"> የወላጆቹን ምክር ቢከተልም ሳይጫወት መቅረቱ አሁንም ያሳዝነዋል ።
(trg)="68"> Jis paklaũsė tėvų patarimo , bet vis dar apgailestavo negalįs žaisti krepšinio .

(src)="72"> ‘ ብዙ ነገር እየቀረብኝ ነው ! ’
(trg)="69"> ‛ Aš lieku nuošaly ! ’

(src)="73"> አንተም በተመሳሳይ ያለህበት ሁኔታ ምንም ዓይነት ቢሆን የትምህርት ቤት ጓደኞችህ ስላሳለፉት ጊዜ በጉራ ሲናገሩ ቅር ሊልህ ይችላል ።
(trg)="70"> Kokia bebūtų tavo padėtis , kartais ir tu gali nusiminti , kai tavo moksladraugiai didžiuojasi linksmai praleidę laiką .

(src)="74"> ‘ ሌሎች ይህን ያህል እንዲደሰቱ የሚፈቀድላቸው ለምንድን ነው ? ’
(trg)="71"> ‛ Kodėl kiti jaunuoliai nevaržomai linksminasi ? ’ — galbūt klausi .

(src)="75"> ብለህ ትጠይቅ ይሆናል ።
(trg)="72"> Na kaip tu gali nugalėti jausmą , kad lieki nuošaly ?