# am/102012252.xml.gz
# kk_Cyrl/102012252.xml.gz


(src)="3"> አመሰግናለሁ የሚል የጽሑፍ መልእክት ለመጨረሻ ጊዜ የደረሰህ መቼ ነው ?
(trg)="1"> АЛҒЫС сөздер жазылған ашықхатты соңғы рет қашан алдыңыз ?

(src)="4"> አንተስ እንዲህ ዓይነት መልእክት ለመጨረሻ ጊዜ የላከው መቼ ነው ?
(trg)="2"> Ал өзіңіз соңғы рет қашан жазып жібердіңіз ?

(src)="5"> በኢንተርኔት መልእክት መለዋወጥ የሚቻልባቸው በርካታ መንገዶች ባሉበት በዚህ ዘመን በእጅ የተጻፉ የምስጋና መልእክቶችን መላክ እየቀረ መጥቷል ።
(trg)="3"> Электронды байланыс түрлері дамыған қазіргі заманда алғыс сөздер жазып , ашықхат беретіндер кемде - кем .

(src)="6"> ሆኖም “ አመሰግናለሁ ” የሚል በእጅ የተጻፈ መልእክት መላክ ሰዎች ላደረጉልህ ደግነት ያለህን አድናቆት የምታሳይበት ልዩ መንገድ ነው ።
(trg)="4"> Алайда адамдарға ашықхатта “ рақметімізді ” жазып жіберу — олардың жасаған жақсылықтарына деген ризашылығымызды білдірудің керемет жолы .

(src)="7"> ምስጋናህን በዚህ መንገድ እንዴት መግለጽ እንደምትችል የሚጠቁሙ አንዳንድ ሐሳቦች ከዚህ በታች ቀርበዋል ።
(trg)="5"> Төменде мұны қалай істеуге болатынын көрсететін бірнеше кеңестер ұсынылған :

(src)="8"> ሐሳብህን በእጅህ ብትጽፍ ይበልጥ ጥሩ ነው ።
(trg)="6"> Ашықхатты қолмен жазғаныңыз абзал .

(src)="10"> ስጦታ ተልኮልህ ከሆነ ስጦታው እንደደረሰህና ለምን ዓላማ ልትጠቀምበት እንዳሰብክ ጻፍ ።
(trg)="7"> Бұлай еткеніңіз адамға жеке көңіл бөліп жазғаныңызды көрсетеді .

(src)="11"> መልእክትህን ጽፈህ ስትጨርስ ምስጋናህን በድጋሚ ግለጽ ።
(trg)="8"> Алғыс білдіргіңіз келген адамның атын жазыңыз .

(src)="12"> የምስጋና መልእክት መላክህ ግለሰቡ ጥሩ ስሜት እንዲሰማው ያደርጋል ።
(src)="13"> እንግዲያው በሚቀጥለው ጊዜ አንድ ሰው በእንግድነት ሲቀበልህ ፣ በደግነት ተነሳስቶ አንድ ነገር ሲያደርግልህ ወይም ስጦታ ሲሰጥህ ያደረገውን ነገር ከፍ አድርገህ እንደምትመለከት ግለጽለት ።
(trg)="9"> Егер сыйлық алған болсаңыз , сол сыйлыққа ризашылығыңызды білдіріп , оны қалай қолданғыңыз келетінін де айтып өтіңіз .

(src)="14"> አመሰግናለሁ !
(src)="15"> ማለትን አትርሳ ።
(src)="16"> [ በገጽ 29 ላይ የሚገኝ ሣጥን / ​ ሥዕል ]
(trg)="10"> Хатыңыздың соңында тағы бір рет алғысыңызды білдіріңіз .

(src)="17"> ለውድ አክስቴ ሜሪ # 2
(src)="18"> ስለሰጠሽኝ ሰዓት በጣም አመሰግናለሁ !
(trg)="11"> Алғыс сөздер хат алушының жүрегіне жылу беріп , жүзін жадыратады .

(src)="20"> ባለፈው ሳምንት ስለተገናኘን እጅግ ደስ ብሎኛል ፤ በሰላም ቤትሽ እንደገባሽ ተስፋ አደርጋለሁ ።
(src)="21"> ዳግመኛ የምንገናኝበትን ጊዜ በናፍቆት እጠባበቃለሁ ።
(trg)="12"> Мысалы , келесі жолы сізге біреу қонақжайлылық танытса , қол ұшын берсе не сыйлық сыйласа , мұны кәдімгі нәрсе деп қарастырмайтыныңызды көрсетіңіз .

(src)="22"> ስለ አሳቢነትሽ በድጋሚ አመሰግናለሁ !
(src)="23"> # 4
(trg)="13"> “ Рақмет ” деп айтуды ұмытпаңыз !

(src)="29"> ጠቃሚ ምክሮች
(src)="30"> ● የገንዘብ ስጦታዎችን ስትጠቅስ በተዘዋዋሪ ይሁን ።
(trg)="14"> ● Ақшалай көмек алсаңыз , бұл жайлы жалпы айтып кетіңіз .

(src)="31"> ለምሳሌ ያህል ፣ የተላከልህን የገንዘብ መጠን በቀጥታ ከመጥቀስ ይልቅ “ ለላክልኝ ስጦታ አመሰግናለሁ ።
(trg)="15"> Мысалы , ақшаның сомасын жазғаннан гөрі , былай десеңіз болады : “ Жомарттықпен берген сыйлығың үшін рақмет .

(src)="32"> ገንዘቡን . . .
(src)="33"> ላደርግበት አስቤያለሁ ” ልትል ትችላለህ ።
(trg)="16"> Мен оны былай жаратпақшымын : . . . ”

(src)="34"> ● የምስጋና መልእክት በምትጽፍበት ወቅት መግለጽ የሚኖርብህ ስለ ስጦታውና ስጦታውን በማግኘትህ ስለተሰማህ የአድናቆት ስሜት ብቻ መሆን ይኖርበታል ።
(trg)="17"> ● Сізге берілген сыйлық туралы ғана сөз етіп , ризашылығыңызды білдіріңіз .

(src)="35"> ለምሳሌ ስላሳለፍከው የእረፍት ጊዜ ወይም በቅርቡ ወደ ሆስፒታል ስለሄድክበት ምክንያት በዚህ የምስጋና መልእክት ላይ ማካተት አይኖርብህም ።
(trg)="18"> Ашықхатқа жазғы демалысты қалай өткізгеніңіз жайлы не ауруханаға барғаныңыз туралы бүге - шігесіне дейін жазудың қажеті жоқ .

(src)="36"> ● ከስጦታው ጋር በተያያዘ ቅር ያለህ ነገር ቢኖር በፍጹም መጥቀስ አይኖርብህም ።
(trg)="19"> ● Егер алған сыйлығыңыз ойдағыдай болып шықпаса , бұл жайлы сөз ету орынсыз болар еді .

(src)="37"> ለምሳሌ ያህል ፣ “ ስለ ሰጠሽኝ ሸሚዝ አመሰግናለሁ ፤ ሆኖም ሸሚዙ በጣም ሰፍቶኛል ! ”
(trg)="20"> Мысалы , “ Көйлек сыйлағаның үшін рақмет !

(src)="38"> ብሎ መጻፍ ደግነት የጎደለው ነገር ነው ።
(trg)="21"> Бірақ ол маған шақ келмеді ” деп жазып жіберу әдептілікке жатпас еді .

(src)="39"> [ በገጽ 29 ላይ የሚገኝ ሣጥን ]
(trg)="22"> Киелі кітап бізді ризашылық білдіруге талпындырады .

(src)="40"> መጽሐፍ ቅዱስ አመስጋኝ እንድንሆን ያበረታታል ።
(trg)="23"> Онда : “ Ұдайы дұға етіңдер .

(src)="41"> እንዲሁም “ ያለማቋረጥ ጸልዩ ” የሚል ምክር ከሰጠን በኋላ “ ስለ ሁሉም ነገር አመስግኑ ” በማለት ይናገራል ። ​ — 1 ተሰ .
(src)="42"> 5 : 17 , 18
(trg)="24"> Барлық жағдайда Құдайға ризашылық білдіріңдер ” , — деп айтылған .

# am/102016001.xml.gz
# kk_Cyrl/102016001.xml.gz


(src)="1"> የርዕስ ማውጫ
(trg)="1"> Мазмұны

(src)="2"> © 2016 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
(trg)="2"> © 2016 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania

(src)="3"> አንድ ሰው ያለው አመለካከት ተፈታታኝ ሁኔታዎችን ለማሸነፍ ሲታገል በሚያገኘው ስኬት ላይ ተጽዕኖ አለው ?
(trg)="3"> Оң көзқарастың қиындықпен күресуге көмегі тие ме ?

(src)="4"> ምን ትላለህ ?
(trg)="4"> Сіздің жауабыңыз қандай ?

(src)="5"> አለው
(trg)="5"> Иә

(src)="6"> የለውም
(trg)="6"> Жоқ

(src)="8"> መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል ?
(trg)="7"> Жағдайға байланысты

(src)="9"> “ በመከራ ቀን ተስፋ የምትቆርጥ ከሆነ ጉልበትህ እጅግ ይዳከማል ። ” — ምሳሌ 24 : 10
(trg)="8"> Киелі кітапта былай делінген : “ Қиын шақта сағың сынса , күш - жігерің таусылар ” .

(src)="10"> 7 ስለ ይሖዋ ምሥክሮች ምን ያህል ታውቃለህ ?
(trg)="9"> 7 Ехоба куәгерлері туралы не білесіз ?

(src)="11"> 10 ለቤተሰብ
(trg)="10"> 10 ОТБАСЫҢЫЗ БЕРЕКЕЛІ БОЛСЫН

(src)="12"> እውነተኛ ጓደኛ ማግኘት የሚቻለው እንዴት ነው ?
(trg)="11"> Нағыз достарды қалай табуға болады ?

(src)="13"> 12 አገሮችና ሕዝቦች
(trg)="12"> 12 ТӨРТКІЛ ДҮНИЕГЕ САЯХАТ

(src)="14"> ሊክቴንስታይንን እንጎብኝ
(trg)="13"> Лихтенштейн

(src)="15"> 14 መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል ?
(trg)="14"> 14 ҚҰДАЙ СӨЗІНЕ ҮҢІЛЕЙІК

(src)="16"> ሰማይ
(trg)="15"> Аспан

(src)="17"> 16 ንድፍ አውጪ አለው ?
(trg)="16"> 16 ЖАРАТЫЛЫС ҒАЖАЙЫПТАРЫ

(src)="18"> ከትልፊሽ — የባሕር ውስጥ እስስት
(trg)="17"> Түсін өзгерте алатын басаяқты ұлу

(src)="19"> ሕይወት እና ሞት
(trg)="18"> ШЫНАЙЫ ДІН

(src)="20"> ስንሞት ምን እንሆናለን ?
(trg)="19"> Шынайы дінді қалай анықтауға болады ?

(src)="21"> መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠው መልስ ያስገርምህ ይሆናል ።
(trg)="20"> Бұл туралы Киелі кітапта не жазылғаны сізді қызықтыруы мүмкін .

(src)="22"> ( የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች > የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው በሚለው ሥር ይገኛል )
(trg)="21"> ( Мынаны қараңыз : КИЕЛІ КІТАП ТӘЛІМДЕРІ / КИЕЛІ КІТАП .
(trg)="22"> СҰРАҚТАР МЕН ЖАУАПТАР )

(src)="23"> ወጣቶች
(trg)="23"> ЖАСӨСПІРІМДЕР

(src)="24"> እኩዮችህ ምን ይላሉ ?
(trg)="25"> Қорғану шаралары

(src)="25"> ወጣቶች በሕይወት ውስጥ ስለሚያጋጥሟቸው ተፈታታኝ ሁኔታዎች የተናገሩትን ተመልከት ።
(trg)="26"> Жыныстық зорлықтан жапа шекпеу үшін не істеуге болатынын біліңіз .

(src)="26"> ( የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች > ወጣቶች በሚለው ሥር ይገኛል )
(trg)="27"> ( Мынаны қараңыз : КИЕЛІ КІТАП ТӘЛІМДЕРІ / ЖАСӨСПІРІМДЕР / ЖАСТАРДЫҢ САУАЛДАРЫ )

# am/102016002.xml.gz
# kk_Cyrl/102016002.xml.gz


(src)="1"> የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ
(trg)="1"> НЕГІЗГІ ТАҚЫРЫП

(src)="2"> ከሚከተሉት ውስጥ ለደስታህ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክተው የትኛው ይመስልሃል ?
(trg)="2"> Бақытыңыз мына жайттардың қайсысына байланысты ?

(src)="3"> ያለህበት ሁኔታ
(trg)="3"> Жағдайыңызға

(src)="4"> በዘር የወረስከው ነገር
(trg)="4"> Шыққан тегіңізге

(src)="5"> አመለካከትህ
(trg)="5"> Көзқарасыңызға

(src)="6"> አንዳንዶች “ ያለህበት ሁኔታ ” የሚለውን ይመርጡ ይሆናል ፤ ከዚያም . . .
(trg)="6"> КЕЙБІРЕУЛЕР жоғарыдағы сұраққа “ жағдайыма байланысты ” деп жауап берер .

(src)="7"> “ ብዙ ገንዘብ ቢኖረኝ ኖሮ . . .
(trg)="7"> Олар егер . . .
(trg)="8"> ақшам көп болса

(src)="8"> “ አስደሳች ትዳር ቢኖረኝ ኖሮ . . .
(trg)="9"> жақсы жұбайым болса
(trg)="10"> денсаулығым мықты болса

(src)="9"> “ ጥሩ ጤንነት ቢኖረኝ ኖሮ . . .
(trg)="11"> . . бақытты болар едім деуі мүмкін .

(src)="10"> ደስተኛ እሆን ነበር ” ይላሉ ።
(trg)="13"> Бұлай болғаны өте жақсы .

(src)="11"> እንደ እውነቱ ከሆነ ግን አብዛኛውን ጊዜ ከደስታ ጋር በተያያዘ ትልቁን ቦታ የሚይዘው ያለንበት ሁኔታ ወይም በዘር የወረስነው ነገር ሳይሆን አመለካከታችን ነው ።
(trg)="14"> Себебі жағдайыңызды өзгерте алмауыңыз не шыққан тегіңізге еш әсер ете алмауыңыз мүмкін .

(src)="12"> ይህ መሆኑ ደግሞ ሊያስደስተን ይገባል ።
(src)="13"> ለምን ?
(trg)="15"> Алайда өмірге қатысты көзқарасыңыздың оң не теріс болуы өз қолыңызда .

(src)="14"> ምክንያቱም በሁኔታህና በዘር በወረስከው ነገር ላይ ያን ያህል ለውጥ ማድረግ አትችልም ፤ አመለካከትህን ግን መቆጣጠር ትችላለህ ።
(trg)="16"> Киелі кітапта : “ Қуанышты жүрек жақсы шипа болар , күйреген рух сүйекті қуратар ” , — делінген .

(src)="15"> አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሳሌ “ ደስተኛ ልብ ጥሩ መድኃኒት ነው ፤ የተደቆሰ መንፈስ ግን ኃይል ያሟጥጣል ” ይላል ።
(trg)="17"> Басқа сөзбен айтқанда , кез келген адам көзқарасын өзгерту арқылы өмірін көркейте алады !

(src)="16"> በእርግጥም አመለካከትህ ለውጥ ያመጣል !
(trg)="18"> Сіз алдыңызға қойған мұрат - мақсатыңызға жетесіз бе , жоқ па ?

(src)="17"> ይህም ግብህ ላይ መድረስ እንድትችል አሊያም ተስፋ ቆርጠህ እንድትተወው ያደርግህ ይሆናል ።
(trg)="19"> Басыңызға қасірет түскенде , бұл сіздің адами қасиетіңізді шыңдай түсе ме , әлде одан айыра ма ?

(src)="18"> ወይም ደግሞ የደረሰብህ አንድ አሳዛኝ ክስተት ጥንካሬህ አሊያም ድክመትህ አፍጥጦ እንዲወጣ ያደርጋል ።
(trg)="20"> Мұның бәрі көзқарасыңызға байланысты .

(src)="19"> አንዳንድ ሰዎች ይህ ሐሳብ አይዋጥላቸው ይሆናል ።
(trg)="21"> Бұл оймен келіспейтін адамдар табылатын шығар .

(src)="20"> እንዲህ ሊሉ ይችላሉ ፦
(trg)="22"> Олар былай деуі мүмкін :

(src)="21"> ‘ ደስተኛ መስዬ በመታየት ችግሬን ምን አስደበቀኝ ? ’
(trg)="23"> “ Неге мен азабымды жасырып , сырты бүтін , іші түтін болып жүруім керек ? ”

(src)="22"> ‘ የፈለገውን ያህል ቀና አመለካከት ቢኖረኝ ያለሁበት ሁኔታ አይቀየር ። ’
(trg)="24"> “ Қанша жерден оң көзқарас танытпайын , бәрібір жағдайым жақсармайды ” .

(src)="23"> ‘ በቁሜ ከምቃዥ ሐቁን ተቀብዬ ብኖር ይሻለኛል ። ’
(trg)="25"> “ Мен өзімді алдағаннан гөрі өмірдің шындығына тура қарауды жөн көремін ” .

(src)="24"> እነዚህ ሐሳቦች እውነታ ያላቸው ይመስሉ ይሆናል ።
(trg)="26"> Жоғарыдағы сөздердің жаны бар деп ойлайтын шығармыз .

(src)="25"> ያም ሆኖ አዎንታዊ አመለካከት መያዝ ብዙ ጠቃሚ ጎኖች አሉት ።
(trg)="27"> Десе де оң көзқарас танытудың пайдасы көп .

(src)="26"> እስቲ ቀጥሎ የቀረቡትን ሁኔታዎች አስብባቸው ።
(trg)="28"> Қазір келесі беттегі мысалдарды қарастырып көрейік .

(src)="27"> አሌክስ እና ብራየን በአንድ መሥሪያ ቤት ውስጥ በተለያየ ፕሮጀክት ላይ ተመድበው ሥራቸውን በትጋት ያከናውናሉ ።
(trg)="29"> Алтынбек пен Бағлан бір мекемеде әртүрлі жобамен жұмыс істейді .

(src)="28"> አለቃቸው ሥራቸውን ከገመገመ በኋላ በሁለቱም ፕሮጀክቶች ላይ ያለውን የጎላ ድክመት ጠቀሰ ።
(trg)="30"> Екеуі жобаларын аяқтаған соң , оны бастықтары тексеріп шығып , қандай қате жібергендерін айтады .

(src)="29"> አሌክስ ፦ “ ይህ ፕሮጀክት እንዲሳካ ብዙ ጊዜና ጉልበት ባፈስስም አልተሳካልኝም ።
(trg)="31"> Алтынбек : “ Мен бұл жобаға қанша күш пен уақыт жұмсадым .

(src)="30"> በዚህ ሥራ መቼም ስኬታማ የምሆን አይመስለኝም ።
(trg)="32"> Ал бастығым болса әлі де қателерімді табуда .

(src)="31"> ምንም ያህል ብለፋ ጉድለት አያጣውም ።
(trg)="33"> Бұл жобаны мен істей алмаймын .

(src)="32"> ታዲያ ምን አደከመኝ ? ”
(trg)="34"> Қанша тер төкпейін , бәрібір қолымнан келмейді .

(src)="33"> ብራየን ፦ “ አለቃዬ የሥራዬን መልካም ጎኖች ነግሮኛል ፤ ይሁንና አንዳንድ ከባድ ስህተቶችን ሠርቻለሁ ።
(trg)="35"> Одан әрі тырысып - бағудың қажетін көріп тұрған жоқпын ” .

(src)="34"> ለሚቀጥለው የተሻለ ሥራ ለመሥራት የሚያስችለኝን ልምድ አግኝቼበታለሁ ። ”
(trg)="36"> Бағлан : “ Бастығым жұмысымның жақсы орындалған жақтарын айтып өтті .

(src)="35"> ታዲያ ምን ይመስልሃል ?
(trg)="37"> Бірақ үлкен қате жіберген жерлерім де болыпты .

(src)="36"> ከስድስት ወር በኋላ ሥራውን ለማከናወን የተሻለ ብቃት የሚኖረው ማን ነው ?
(trg)="38"> Енді жұмысымды қалай жақсарту керектігін білемін ” .

(src)="37"> አሌክስ ወይስ ብራየን ?
(trg)="39"> ҚАЛАЙ ЖАУАП БЕРЕР ЕДІҢІЗ ?

(src)="38"> አሠሪ ብትሆን ኖሮ የምትቀጥረው ወይም በድርጅትህ ውስጥ እንዲቀጥል የምትፈልገው ማንን ነው ?
(trg)="41"> Егер сіз жұмыс беруші болсаңыз , осы екеуінің қайсысын жұмысқа алар едіңіз ?

(src)="39"> አንተስ ያሰብከው ነገር ሳይሳካ ቢቀር የምትሰጠው ምላሽ እንደ አሌክስ ነው ወይስ እንደ ብራየን ?
(trg)="42"> Сәтсіздікке кезіксеңіз , осы екі жігіттің қайсысы сияқты әрекет етесіз ?

(src)="40"> አንድሬያ እና ብሪትኒ ከብቸኝነት ስሜት ጋር ይታገላሉ ።
(trg)="43"> Ажар мен Бағила жалғыздықтан жабырқап жүрген жандар .

(src)="41"> ሁለቱም ይህን ችግር ለመቋቋም የተለያየ ዘዴ ይጠቀማሉ ።
(trg)="44"> Бұл жағдаймен әрқайсысы әртүрлі күресіп жүр .