# am/102018042.xml.gz
# ins/102018042.xml.gz


(src)="1"> © 2018 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
(trg)="1"> © 2018 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania

(src)="2"> ይህ ጽሑፍ የሚሸጥ አይደለም ።
(trg)="2"> This publication is not for sale .

(src)="3"> መጽሔቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ መጽሐፍ ቅዱስን ለማስተማር ከሚታተሙት ጽሑፎች መካከል አንዱ ሲሆን ይህ የማስተማር ሥራ የሚደገፈው ደግሞ ሰዎች በፈቃደኝነት በሚያደርጉት መዋጮ ነው ።
(trg)="3"> It is provided as part of a worldwide Bible educational work supported by voluntary donations .

(src)="4"> መዋጮ ለማድረግ www.jw.org / amን ተመልከት ።
(trg)="4"> To make a donation , please visit www.jw.org .

(src)="6"> ይህ መጽሔት የሚጠቀመው የአውሮፓውያንን አቆጣጠር ነው ።
(trg)="5"> Unless otherwise indicated , Scripture quotations are from the modern - language New World Translation of the Holy Scriptures .

# am/102018043.xml.gz
# ins/102018043.xml.gz


(src)="1"> ብዙውን ጊዜ አንድ ቤተሰብ ስኬታማ ሳይሆን የቀረው ለምን እንደሆነ ሲነገር እንሰማለን ።
(trg)="1"> We hear a lot about what goes wrong in families that fail .

(src)="2"> በአንጻሩ ግን አንዳንድ ቤተሰቦች ስኬታማ ሊሆኑ የቻሉት ለምንድን ነው ?
(trg)="2"> But what goes right in those that succeed ?

(src)="3"> በዩናይትድ ስቴትስ ፣ በ1990 እና በ2015 መካከል ባለው ጊዜ ውስጥ ከ50 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች ፍቺ በእጥፍ የጨመረ ሲሆን ከ65 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች ፍቺ ቁጥር ደግሞ በሦስት እጥፍ ጨምሯል ።
(trg)="3"> Between 1990 and 2015 , the divorce rate in the United States doubled for those over the age of 50 and tripled for those over 65 .

(src)="5"> ወጣቶች ስኬታማ ለመሆን የሚያስፈልጓቸውን ችሎታዎች ሳይማሩ ያድጋሉ ።
(trg)="4"> Parents are confused : Some experts recommend giving children constant praise , while others advocate tough love .

(src)="7"> ትዳር አስደሳችና ዘላቂ ጥምረት መሆን ይችላል ።
(trg)="5"> Young people are entering adulthood without the skills they need to succeed .

(src)="8"> ወላጆች ልጆቻቸውን በፍቅር መቅጣት የሚችሉበትን መንገድ ሊማሩ ይችላሉ ።
(trg)="6"> Nevertheless , the fact is . . .
(trg)="7"> Marriage can be a rewarding and permanent bond .

(src)="9"> ወጣቶች አዋቂ ሲሆኑ የሚያስፈልጓቸውን ችሎታዎች ከልጅነታቸው መማር ይችላሉ ።
(trg)="8"> Parents can learn to discipline their children with love .

(src)="10"> ይህን ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው ?
(trg)="9"> Young people can gain the skills they need for adulthood .
(trg)="10"> How ?

(src)="11"> ይህ ንቁ !
(trg)="11"> This issue of Awake !

(src)="12"> መጽሔት ቤተሰብ ስኬታማ እንዲሆን የሚረዱ 12 ወሳኝ ነገሮችን ያብራራል ።
(trg)="12"> will discuss 12 secrets of successful families .

# am/102018044.xml.gz
# ins/102018044.xml.gz


(src)="1"> 1 ቃል ኪዳንን ማክበር
(trg)="1"> Secret 1 Commitment

(src)="2"> 2 ተባብሮ መሥራት
(trg)="2"> Secret 2 Teamwork

(src)="3"> 3 መከባበር
(trg)="3"> Secret 3 Respect

(src)="4"> 4 ይቅር ባይ መሆን
(trg)="4"> Secret 4 Forgiveness

(src)="5"> 5 የሐሳብ ልውውጥ ማድረግ
(trg)="5"> Secret 5 Communication

(src)="6"> 6 ተግሣጽ መስጠት
(trg)="6"> Secret 6 Discipline

(src)="7"> 7 በሥነ ምግባር መሥፈርቶች መመራት
(trg)="7"> Secret 7 Values

(src)="8"> 8 ምሳሌ መሆን
(trg)="8"> Secret 8 Example

(src)="9"> 9 ማንነትን ማወቅ
(trg)="9"> Secret 9 Identity

(src)="10"> 10 አመኔታ ማትረፍ
(trg)="10"> Secret 10 Trustworthiness

(src)="11"> 11 ታታሪ መሆን
(trg)="11"> Secret 11 Industriousness

(src)="12"> 12 ግብ ማውጣት
(trg)="12"> Secret 12 Goals

# am/102018045.xml.gz
# ins/102018045.xml.gz


(src)="2"> ለባለትዳሮች
(trg)="1"> FOR COUPLES

(src)="3"> ቃል ኪዳናቸውን የሚያከብሩ ባልና ሚስቶች ትዳራቸውን የሚመለከቱት ዘላቂ ጥምረት እንደሆነ አድርገው ሲሆን ይህም በመካከላቸው የመተማመን ስሜት ይፈጥራል ።
(trg)="2"> Husbands and wives who are committed to their marriage view it as a permanent bond , and that creates a sense of security between them .

(src)="4"> አስቸጋሪ ሁኔታዎች ቢፈጠሩ እንኳ የትዳር ጓደኛቸው እንደማይከዳቸው እርግጠኛ ናቸው ።
(trg)="3"> Each spouse is confident that the other will honor the union , even in difficult times .

(src)="5"> አንዳንድ ባለትዳሮች አብረው ለመኖር የሚገደዱት ማኅበረሰቡ ወይም ዘመዶቻቸው ፍቺውን ስለሚቃወሙ ነው ።
(trg)="4"> Some couples feel compelled to stay together because of social or family pressure .

(src)="6"> ሆኖም አብረው ለመኖር የሚያነሳሳቸው በፍቅርና በአክብሮት ላይ የተመሠረተውን ቃል ኪዳናቸውን ለመጠበቅ ያላቸው ፍላጎት መሆን አለበት ።
(trg)="5"> Far better , however , is a sense of commitment that is based on mutual love and respect .

(src)="7"> የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ ፦ “ ባልም ሚስቱን መተው የለበትም ። ” — 1 ቆሮንቶስ 7 : 11
(trg)="6"> BIBLE PRINCIPLE : “ A husband should not leave his wife . ” ​ — 1 Corinthians 7 : 11 .

(src)="8"> “ የጋብቻ ቃል ኪዳንህን የምታከብር ከሆነ ሊያናድድ የሚችል ነገር ቢያጋጥምህም በቀላሉ አትናደድም ።
(trg)="7"> “ If you are committed to your marriage , you allow yourself to be wronged .

(src)="9"> ይቅር ለማለትም ሆነ ይቅርታ ለመጠየቅ አትዘገይም ።
(trg)="8"> You are quick to forgive and quick to apologize .

(src)="10"> ችግሮችን እንደ ጊዜያዊ መሰናክል እንጂ ለፍቺ እንደሚያበቃ ምክንያት አድርገህ አትመለከታቸውም ። ” — ማይካ
(trg)="9"> You view problems as obstacles , not as deal breakers . ” ​ — Micah .

(src)="11"> ቃል ኪዳናቸውን የማያከብሩ ባለትዳሮች ችግሮች ሲያጋጥሟቸው ‘ በቃ ልንጣጣም አልቻልንም ’ ብለው ያስባሉ ፤ ከዚያም ከትዳሩ መገላገል የሚችሉባቸውን መንገዶች ይፈልጋሉ ።
(trg)="10"> When confronted with problems , spouses without commitment are more likely to conclude , ‘ We just weren’t made for each other ’ and look for ways to get out of the marriage .

(src)="12"> “ ብዙ ሰዎች ትዳር ውስጥ የሚገቡት ‘ ካልሆነ እንፋታለን ’ ብለው ነው ።
(trg)="11"> “ Many people go into marriage knowing that they have a ‘ fallback plan ’ ​ — divorce .

(src)="13"> ሰዎች ትዳር የሚመሠርቱት ስለመፋታት እያሰቡ ከሆነ መጀመሪያውኑ እውነተኛ ቃል ኪዳን ገብተዋል ብሎ ማሰብ ያስቸግራል ። ” — ጂን
(trg)="12"> When people enter marriage already thinking about the possibility of divorce , their commitment is lacking right from the start . ” ​ — Jean .

(src)="14"> ራስህን ፈትሽ
(trg)="13"> TEST YOURSELF

(src)="15"> በመካከላችሁ አለመግባባት በሚፈጠርበት ጊዜ . . .
(trg)="14"> When in the middle of a dispute . . .

(src)="16"> የትዳር ጓደኛህን በማግባትህ ትቆጫለህ ?
(trg)="15"> Do you find yourself regretting that you married your spouse ?

(src)="17"> ሌላ ሴት ብታገባ ኖሮ ሕይወትህ ምን ሊመስል እንደሚችል ታስባለህ ?
(trg)="16"> Do you daydream about being with someone else ?

(src)="18"> “ የአንቺስ ነገር በቃኝ ” ወይም “ ለእኔ የምትሆነኝን አላጣም ” እንደሚሉት ያሉ ሐሳቦችን ትሰነዝራለህ ?
(trg)="17"> Do you say things such as “ I’m leaving you ” or “ I’m going to find someone who appreciates me ” ?

(src)="20"> የሚከተሉትን ጥያቄዎች ከትዳር ጓደኛችሁ ጋር ተወያዩባቸው
(trg)="18"> If you answered yes to one or more of those questions , now is the time to strengthen your commitment .

(src)="21"> የጋብቻ ቃል ኪዳናችንን ችላ ማለት ጀምረን ይሆን ?
(trg)="19"> DISCUSS WITH YOUR SPOUSE
(trg)="20"> Has the level of commitment in our marriage decreased ?

(src)="22"> ከሆነ ለምን ?
(trg)="21"> If so , why ?

(src)="23"> ቃል ኪዳናችንን አክብረን ለመኖር የትኞቹን እርምጃዎች መውሰድ እንችላለን ?
(trg)="22"> What steps can we take now to strengthen our commitment ?
(trg)="23"> TIPS

(src)="24"> ጠቃሚ ምክሮች
(trg)="24"> Write an occasional love note to your spouse

(src)="25"> አልፎ አልፎ ፣ ለትዳር ጓደኛህ ያለህን ፍቅር የሚገልጽ አጭር ነገር ጽፈህ ላክላት
(trg)="25"> Show your commitment by displaying photos of your spouse on your desk at work

(src)="27"> በየቀኑ ፣ አብራችሁ በማትሆኑበት አጋጣሚ ሁሉ ለትዳር ጓደኛህ ስልክ ደውልላት
(trg)="26"> Phone your spouse each day while you are at work or apart

(src)="28"> የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ ፦ “ አምላክ ያጣመረውን ማንም ሰው አይለያየው ። ” — ማቴዎስ 19 : 6
(trg)="27"> BIBLE PRINCIPLE : “ What God has yoked together , let no man put apart . ” ​ — Matthew 19 : 6 .

# am/102018046.xml.gz
# ins/102018046.xml.gz


(src)="2"> ለባለትዳሮች
(trg)="1"> FOR COUPLES

(src)="3"> ተባብረው የሚሠሩ ባለትዳሮች አንድን አውሮፕላን ከሚያበሩ አብራሪና ረዳት አብራሪ ጋር ሊመሳሰሉ ይችላሉ ።
(trg)="2"> When there is teamwork in a marriage , a husband and wife are like a pilot and copilot with the same flight plan .

(src)="4"> እንዲህ ያሉ ባለትዳሮች ችግሮች በሚነሱበት ጊዜም እንኳ የሚያስቡት “ እኔ ” እያሉ ሳይሆን “ እኛ ” እያሉ ይሆናል ።
(trg)="3"> Even when challenges arise , each spouse thinks in terms of “ we ” rather than “ me . ”

(src)="5"> የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ ፦ “ ከዚህ በኋላ አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ሁለት አይደሉም ። ” — ማቴዎስ 19 : 6
(trg)="4"> BIBLE PRINCIPLE : “ They are no longer two , but one flesh . ” ​ — Matthew 19 : 6 .

(src)="6"> “ ትዳር አንድ ሰው ብቻውን የሚተውንበት መድረክ አይደለም ።
(trg)="5"> “ Marriage is not a solo act .

(src)="7"> ትዳርን የተሳካ ለማድረግ ባልና ሚስት ተባብረው መሥራት አለባቸው ። ” — ክሪስተፈር
(trg)="6"> Husband and wife must work together to make it successful . ” ​ — Christopher .

(src)="8"> ተባብረው የማይሠሩ ባልና ሚስት ጭቅጭቅ ሲነሳ ችግሩን ለመፍታት ጥረት ከማድረግ ይልቅ አንዳቸው ሌላውን የማጥቃት አዝማሚያ ይታይባቸዋል ።
(trg)="7"> When a conflict arises , a husband and wife who are not a team will tend to attack each other rather than the problem .

(src)="9"> ጥቃቅን አለመግባባቶች ወደ ከፍተኛ ግጭት ሊያመሩ ይችላሉ ።
(trg)="8"> Minor issues will turn into major obstacles .

(src)="10"> “ ተባብሮ መሥራት ትዳርን ስኬታማ ለማድረግ የሚያስፈልግ መሠረታዊ ነገር ነው ።
(trg)="9"> “ Teamwork is the essence of marriage .

(src)="12"> ደባል የሆኑ ሰዎች አብረው ቢኖሩም ውሳኔ በሚጠይቁ አስፈላጊ ጉዳዮች ላይ የየራሳቸውን አቋም ይወስዳሉ ። ” — አሊግዛንድራ
(trg)="10"> If my husband and I weren’t a team , we would be roommates instead of marriage mates ​ — two people who live together but who aren’t on the same page when it comes to important decisions . ” ​ — Alexandra .

(src)="13"> ራስህን ፈትሽ
(trg)="11"> TEST YOURSELF

(src)="14"> ሠርቼ የማገኘውን ገንዘብ የምመለከተው “ የራሴ ብቻ ” እንደሆነ አድርጌ ነው ?
(trg)="12"> Do I view the money I earn as “ all mine ” ?

(src)="15"> በደንብ ዘና እንዳልኩ የሚሰማኝ የትዳር ጓደኛዬ አብራኝ ከሌለች ነው ?
(trg)="13"> To relax fully , do I need to be away from my spouse ?

(src)="16"> የትዳር ጓደኛዬ ከዘመዶቿ ጋር የምትቀራረብ ብትሆንም እኔ ከእነሱ ለመራቅ እሞክራለሁ ?
(trg)="14"> Do I keep my distance from my spouse’s relatives , even though he or she is close to them ?

(src)="17"> የሚከተሉትን ጥያቄዎች ከትዳር ጓደኛችሁ ጋር ተወያዩባቸው
(trg)="15"> DISCUSS WITH YOUR SPOUSE

(src)="18"> በጥሩ ሁኔታ ተባብረን የምንሠራው በየትኞቹ አጋጣሚዎች ነው ?
(trg)="16"> In what aspect ( s ) of our marriage do we work well as a team ?

(src)="19"> ማሻሻያ ማድረግ የሚያስፈልገንስ በየትኞቹ ዘርፎች ነው ?
(trg)="17"> In what aspect ( s ) could we improve ?

(src)="20"> ይበልጥ ተባብረን ለመሥራት ምን ማድረግ እንችላለን ?
(trg)="18"> What steps can we take to improve our spirit of teamwork ?

(src)="21"> ጠቃሚ ምክሮች
(trg)="19"> TIPS

(src)="22"> እስቲ ቴኒስ እየተጫወታችሁ እንደሆነ አድርጋችሁ አስቡ ።
(trg)="20"> Imagine a tennis match with the two of you on opposite sides of the net .

(src)="24"> ታዲያ ከትዳር ጓደኛችሁ ጋር በአንድ ቡድን ውስጥ ሆናችሁ ለመጫወት ምን እርምጃዎችን መውሰድ ትችላላችሁ ?
(trg)="21"> Instead , what practical steps can you take to join your spouse so that you are both on the same team ?

(src)="25"> ‘ ማሸነፍ የምችለው እንዴት ነው ? ’
(trg)="22"> Instead of thinking , ‘ How can I win ? ’

(src)="26"> ብሎ ከማሰብ ይልቅ ‘ ማሸነፍ የምንችለው እንዴት ነው ? ’
(trg)="23"> think ‘ How can we both win ? ’

(src)="28"> “ ‘ ትክክል የሆነው ማን ነው ? ’
(trg)="24"> “ Forget about who is right and who is wrong .

(src)="30"> በትዳራችሁ ውስጥ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ሰላምና አንድነት መስፈኑ ነው ። ” — ኤታን
(trg)="25"> That isn’t as important as having peace and unity in your marriage . ” ​ — Ethan .

(src)="31"> የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ ፦ “ ስለ ራሳችሁ ፍላጎት ብቻ ከማሰብ ይልቅ እያንዳንዳችሁ ለሌሎች ሰዎች ፍላጎትም ትኩረት ስጡ ። ” — ፊልጵስዩስ 2 : 3 , 4
(trg)="26"> BIBLE PRINCIPLE : “ Look out not only for your own interests , but also for the interests of others . ” ​ — Philippians 2 : 3 , 4 .

# am/102018047.xml.gz
# ins/102018047.xml.gz


(src)="2"> ለባለትዳሮች
(trg)="1"> FOR COUPLES

(src)="5"> ከዚህ ይልቅ በመካከላቸው ስለተፈጠረው ልዩነት ይነጋገራሉ ።
(trg)="2"> Respectful spouses care about each other , even during a disagreement .

(src)="6"> የትዳር ጓደኛቸውን አመለካከት በአክብሮት ያዳምጣሉ ፤ ከዚያም ለሁለቱም የሚስማማ አስታራቂ ሐሳብ ይፈልጋሉ ። ”
(trg)="3"> “ These couples don’t get gridlocked in their separate positions , ” says the book Ten Lessons to Transform Your Marriage .

(src)="7"> የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ ፦ “ ፍቅር . . .
(trg)="4"> “ Instead , they keep talking with each other about conflicts .

(src)="8"> የራሱን ፍላጎት አያስቀድምም ። ” — 1 ቆሮንቶስ 13 : 4 , 5
(trg)="6"> BIBLE PRINCIPLE : “ Love . . . does not look for its own interests . ” ​ — 1 Corinthians 13 : 4 , 5 .

(src)="9"> “ ሚስቴን ስለማከብራት እሷ ከፍ አድርጋ የምትመለከተውን ነገር አደንቃለሁ እንዲሁም እሷንም ሆነ ትዳራችንን የሚጎዳ ምንም ነገር ማድረግ አልፈልግም ። ” — ማይካ
(trg)="7"> “ To respect my wife means that I appreciate her value and I don’t want to do anything that would damage her or our marriage . ” ​ — Micah .

(src)="10"> በትዳር ውስጥ መከባበር ከሌለ ባልና ሚስት ሲነጋገሩ ሽሙጥና ትችት ይሰነዝራሉ ፤ እንዲሁም አንዳቸው ለሌላው ንቀት እንዳላቸው ያሳያሉ ።
(trg)="8"> Without respect , conversation between spouses can become laced with criticism , sarcasm , and even contempt ​ — qualities that researchers say are early predictors of divorce .